Reform implementation support ion & monitoring directorate

መግቢያ

በቢሮዉ ውስጥ የተጀመረው ጠንካራ የልማት ሰራዊት የመፍጠር እና የመገንባት ተግባር ተቋማዊ መልክ ይዞ ዘላቂነት ባለው መንገድ እንዲከናወን ማድረግ እና የተሟላ ቁመና ያለው የግብርና ሰራዊት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ በልማት ቡድን እና በ1ለ5 አደረጃጀት ውስጥ የሚታዩትን የክህሎት፣ የአመለካከት እና የስነምግባር ክፍተቶች በመሙላት የተፈጠረው የልማት ሰራዊት አደረጃጀት ወጤታማ እንዲሆን እና ሁሉም የተቋሙ ተግባሮች በተፈጠረው አደረጃጀት አማካኝነት ተፈፃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ለነገ የማይባል ስራ ነዉ።

የተፈጠሩት አደረጃጀቶች ከላይ እስከ ታች የተገናኙ እና የልማት ሰራዊቱ አና አመራሩ አንድ ወጥ በሆነ የግንኙነት እና የትስስር ማዕቀፍ ውሰጥ እንዲገቡ ማድረግ  ወቅታዊ በመሆኑ በየደረጃው ያለው አመራር የርብርብ ማእከል የልማት ሰራዊት መፍጠር እና ተግባሮችን በተደራጀው የልማት ሰራዊት አማካኝነት በመፈፀም ትክክለኛ የግንባታ አቅጣጫ እንዲከተል እና ወጥነት ያለው አመራር እንዲሰጥ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የተደራጀው የልማት ሰራዊት በየቀኑ እና በየሳምንቱ የሚያደርገውን ውይይት እና የሪፖርት ስርዓት ጊዜ እና ወጭ ቆጣቢ በሆነ መንገድ እንዲፈፅመው ማድረግ ተገቢ በመሆኑ እና በአፈፃፀም ወቅት የጎላ አስተዋፅኦ የነበራቸውን ግንባር ቀደም ፈፃሚዎችን በየጊዜው መለየት እና መገንባት ተገቢ በመሆኑ ይህንን ስራ የሚገልጽ የ11 ወር ሪፖርት እንደሚከተለዉ ቀርቧል።

በዚህ  የ11 ወር  በለውጥ  ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት  የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፤

1.ድጋፍና ክትትልን በሚመለከት

 • የድጋፍ ሥራ የሚያስፈልግበት ዋናው አላማ ተቋሙ የሚተገብረውን የለውጥ ሥራዎች እንቅስቃሴ በመከታተልና በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን መሠረት በማድረግ ጥንካሬዎች እንዲቀጥሉ እና ክፍተት በታየባቸው አፈፃፀሞች የእውቀትና የክህሎት ሽግግር በማድረግ ወደ ተቀራረበ አፈፃፀም እንዲመጡ ለማገዝ ነው፡፡
 • በቢሮዉ ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች በየወሩ በቼክ ሊስት በለዉጥና መልካም አስተዳደር አፈፃፀም ዙሪያ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል፤
 • ለ10ሩ ዞን ግ/መምሪያዎች፤ ለ3ቱ ግብርና ኮሌጆች፤ ለ6ቱ ማዕከላት በቼክ ሊስት በየሩብ አመቱ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል፤
 •  በቢሮ ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች፣ ዞኖች፤ ኮሌጆች እና ማዕከላትን በድጋፍና ክትትል የነበሩ ጥንካሬዎችን የበለጠ እንዲሻሻሉ እና መስተካከል ለሚገባቸው ችግሮች የመፍትሄ ሀሳቦችን በማቅረብ እንዲታረሙ እገዛ የሚሰጥ ግብረ መልስ ይሰጣል፡
 • እስከታች መዋቅር ያላቸው ዳይሬክቶሬቶች ቼክ ሊስት በማዘጋጀት፤ ሪፖርት በመቀበል እና ግብረ-መልስ በመስጠት የተሻለ አፈጻጸም እንዳላቸው በድጋፍና ክትትል ወቅት ታይቷል፡፡
 1. ለዉጥ  ሰራዊት  ግንባታ አፈፃፀምን በተመለከተ፤
 • ተቋሙ ውጤታማ መሆን የሚችለው የሰው ኃይላቸውን በማደራጀት ለአንድ አላማ መሳካት በጋራ ማሰለፍ ሲችሉ ነው፡፡ ይህ ሲባል ሰራዊት ስለተደራጀ ብቻ ለዉጥ ማምጣት ይችላል ማለት አይደለም፤ የተደራጀው የለውጥ ሀይል ድህነትን በማሸነፍ ሂደት ውጤታማ የሚሆነው በሚሰራው ስራ ላይ የተሟላ ግንዛቤና እውቀት ሲኖረው ነው፡፡ ስለሆነም ከአላማ ፈፃሚ እስከ ድጋፍ ሰጭ ሰራተኛ ድረስ የተደራጀ ሰው ሀይል በየተሰማራበት መስክ በባለቤትነት ስሜት የተቋሙን ስትራቴጂክ እና ዓመታዊ ዕቅድ የሚፈጽም ሠራዊት ሲፈጠር መሆኑ ይታወቃል፡፡
 • በዚህም መሠረት በተቋሙ በተፈጠረው አደረጃጀት በ1ለ5 በየቀኑ የመረጃ ልውውጥ እና በልማት ቡድን ዕቅድን መሠረት አድርጎ ሣምንታዊ አፈጻጸም ግምገማ እየተደረገ መሆኑ።

 

 

 • የእርስ በርስ መማማር በየሣምንቱ ማድረግ ላይ ከዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬት መሻሻል መኖሩ፤
 • በዚህም መሰረት እንደተቋም የህዝብ ክንፍ የተለየ እና ከህዝብ ክንፉም ጋር የምክክር መድረክ እየተካሄደ ያለ መሆኑ በድጋፍና ክትትል ታይቷል፡፡
 1. የዉጤት ተኮር ዕቅድ (BSC)አፈፃፀምን በተመለከተ፤
 • የቢሮዉ ስትራቴጅያዊ፣ ዓመታዊ እንዲሁም የዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ ለማዘጋጀት የክህሎትና የአመለካከት ችግሮች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ መሆኑ፤
 • ሠራዊቱ የውጤት ተኮር ሥርዓት ፅንሰ ሀሳብን በመረዳት ከተቋሙ ስትራቴጅክ ዕቅድ እስከ ግለሰብ ወርሃዊ ዕቅድ ድረስ ማቀድ ተችሏል፡፡
 • ዕቅድን መሰረት በማድረግም በስድስት ወር እና በወር ውጤት የመሙላት እና ግብረ-መልስ የመስጠት ልምዱ እየዳበረ መጥቷል፡፡
 • ከዚህ በተጨማሪም የፈፃሚዎች ግማሽ አመትና የወሩ ዕቅድ ከዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ ጋር ትስስር እንዲኖረው በማድረግ በአግባቡ ትኩረት ሰጥቶ እየተዘጋጀ መሆኑ፣
 • ስትራቴጅውን በሠራተኛው ዘንድ የማስረጽ (Spritual cascading) በጥንካሬ የታየበት መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
 • በቢሮዉ ለሚገኙ ሰራተኞች ከሃምሌ 1/2008 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2009 ዓ.ም ለሰራተኞች የ6 ወር ዉጤት የተሞላ ሲሆን ከፍተኛ ያገኙ 20 መካከለኛ ያገኙ 188 ዝቅተኛ 4 በአጠቃላይ የ212 ሰራተኞች በወቅቱውጤት ተሞልŸል፡፡
 • በስድስት ወሩ የተመረጡ ግንባር ቀደሞች ወ 16 ሴ 4 ድምር 20 ባለሙያዎች ግንባር ቀደም ሆነዉ ተመርጠዋል፡፡
 1. መልካም አስተዳደር ተግባራትን አፈፃፀም በተመለከተ፤

መልካም አስተዳደር ህግ፣ ደንብና መመሪያ የሚከበርበት፣ የህዝብ ተሣትፎ የሚረጋገጥበት፣ አገልግሎቶች ወይም አሰራሮች ለሁሉም ግልጽ የሚሆኑበት፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የሰፈነበት እንዲሁም የዜጎች የተለያዩ አገልግሎቶችን በአግባቡ መልስ የሚያገኙበት ሥርዓት የተዘረጋበት አስተዳደርን የሚያመለከት ነው፡፡

በመሆኑም በየደረጃው የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግር በመለየት ተቋሙ ተገልጋዮች ላይ የሚከሰቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አንድ በአንድ ነቅሶ በማውጣት በአጭር፣በመካከለኛና በረዥም ጊዜ የሚፈቱትን በመለየት ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡

 • በዚህ ረገድ ሲታይ እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ ዕቅድሁሉም ዳይሬክቶሬቶች ያቀዱ መሆኑን፤
 • በመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዕቅዱ በተቀመጠው ጊዜ መፍታትና አፈጻጸሙን በመገምገም እየተሠራ መሆኑ፤
 • በለውጥ እና በመልካም አስተዳደር አፈጻጸም ዙሪያ በቢሮው ያሉ ዳይሬክቶሬቶች የሚገኙበት ደረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል።
 • የተሻለ አፈጻጸም ያላቸዉ ዳይሬክቶሬቶች፦
 1. የግብዓቶች እና የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት፤
 2. አትክልትና ፍራፍሬ መስኖ ልማት ዳይሬክቶሬት፤
 3. የተፈጥሮ ሀብት ል/ጥ/አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት
 4. የውስጥ ኦዲት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት፤
 • መካከለኛ አፈጻጸም ያላቸው ዳይሬክቶሬቶች፤
 1. ሰብል ልማት ዳይሬክቶሬት፤
 2. በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፤
 3. ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት፤
 4. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት፤
 5. የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት፤
 6. የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፤
 7. የኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት፣
 • በሪፎርም ተግባራት ወደ ሥራ ያልገባ ዳይሬክቶሬት
 1. የአነስተኛ መስኖ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት
 2. የአቅም ግንባታ ሥራ
 • በድጋፍና ክትትል የተለዩ ክፍተቶችን መሠረት በማድረግ በቢሮ ለሚገኙ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጥቷል።
 • ሥልጠናው በዋናነት ትኩረት ያደረገው
  • በልማት ሠራዊት ግንባታ፤
  • በምርጥ ተሞክሮ ቅመራ፤
  • በመልካም አስተዳደር፤
  • በዜጎች ቻርተር ፅንሰ ሃሣብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
 • በስልጠናው የተሣተፉ ወንድ 55 ሴት 62 በጠቅላላ ለ117 ሠራተኞች ስልጠና ተሰጥቷል
 1. የሪፖርት ግንኙነትን በተመለከተ
 •  በለውጥና በመልካም አስተዳደር አፈጻጸም ዙሪያ፦
  • ሣምንታዊ ሪፖርት ለዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ይላካል፤
  • በማስጀመሪያ ምዕራፍ፣ በትግበራና በማጠቃለያ ምዕራፍ አፈፃፀም ቢሮዉ ያለበትን ሁኔታ የሚገልጽ ወርሃዊ ሪፖርት ለሲቪል ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ይላካል፤
 1. የታዩ ክፍተቶች
  • በአመራሩ ይሁን በፈጻሚው በለውጥ መሣሪያዎች ዙሪያ የአቅም ክፍተት መኖሩ፣ ሪፎርሙን የሀገራዊ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አካል አድርጎ አለመዉሰድና
   • የተቋሙ ሰራተኞች በተቋሙ ፖሊሲ፣ ስትራቴጅ፣ አዋጅ፣ ተልዕኮና ራዕይ፣ ደንብና ልዩ ልዩ መመሪያዎች ዙሪያ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ ተቀራራቢ አቅም ከመፍጠር አኳያ ውስንነት መኖሩን፤
   • ከኪራይ ሰብሳቢነት የፀዳ አመለካከት በመያዝ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ሰራተኛው በተደራጀ አግባብ እንዲታገልና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች ሙሉ በሙሉ እንዲፈቱ ከማድረግ አኳያ ውስንነት መኖሩ፤
   • የተቋሙን ሰራተኞች ከተሳሳተ አመለካከትና ተግባር ከማፅዳት አኳያ ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም አሁንም ከሚፈለገው ውጤት አንፃር ውስንነቶች ያሉ መሆኑ
   • ፡-
    • ከስራ ዘግይቶ የመግባትና ቀድሞ የመውጣት የመንግስትን የስራ ሰዓት ማባከን የሚስተዋል መሆኑ ፡፡
   • በዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ በተቀመጠው ጊዜ መሰረት አለማገልገል፤
   • የተቋሙን ስትራቴጅ ሁሉም ፈፃሚ አካላት ተገንዝበውት የዕለት ተዕለት ስራቸው እንዲያደርጉትና ትስስሩንም የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ በኩል ውስንነት አለው፡፡
   • የBSC እቅድ በተገቢው ሁኔታ አቅዶ የመስጠት ውስንነት መኖሩ
   • እቅዱ ሲታቀድ አሣታፊ ያለማድረግና በዕቅድ የሚመራ ፈፃሚን በመፍጠር የለውጥ ሀሳብን እውን ማድረግ ላይ ክፍተት መኖሩን፡፡
   • የሚቀመሩ ተሞክሮዎችን በአግባቡ እንዲሰፉ ከማድረግ እና የሰፉ ተሞክሮዎች ያመጡትን ውጤት በተጨባጭ ገምግሞ መረጃ ከመያዝ አኳያ ውስንነት ያለ መሆኑ፤
   • ማኔጅመንት ካውንስሉ በየ15 ቀኑ የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸምን መገምገም ላይ መቆራረጥ መኖሩ፤
   • በልማት ቡድን ደረጃ በየሩብ ዓመቱ ሂስ ግለሂስ ያለማድረግ፤
   • የቅርብ ሃላፊዎችን የማቀድና የመመዘን ክህሎት ማሳደግ ወዘተ ግሽበትን ለመከላከል ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፡፡
   • የሰራተኞችን ውጤት በወቅቱ (ከጥር1-15 እና ከሃምሌ1-15) ሞልቶ ለሰው ሃይል ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት በማስረከብ ከሰራተኞች ማህደር ጋር እንዲያያዝ ማድረግ ላይ ክፍተት መኖሩ፤
 2. የተገኙ ለውጦች፤
 • የተቋሙን ፖሊሲና ስትራቴጅ፣ ራዕይና ተልኮውን፣ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ፣ የበጀት ዓመት ዕቅድ፣ የተቋሙን አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያና ሌሎች አሰራሮችን በውል ተገንዝቦና አውቆ የመምራት እንዲሁም ፈጣን ውሳኔ ከመስጠትን አኳያ በክልል እናበዞን ተቋማት ለሰራተኞቸው ግንዛቤ በመፍጠር የቅድመ ዝግጅት ስራ አከናውነዋል፡፡ የተሰጡ ሥልጠናዎችን ለአብነት ስንመለከት፡-
 • በቼክ ሊስት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ ሪፖርት ማዘጋጀት ፤ ግብረ- መልስ መስጠት፤ የተግባሮችን አፈፃፀም በአካል ተገኝቶ መከታተል፤ ምርጥ ልምድ መቀመርና ማስፋትና የተቀራረበ አፈፃፀም መኖሩ አበረታች መሆኑ፤
 • በየደረጃው የሚገኙ ፈፃሚዎች በዕቅድ የመመራት ባህል እየዳበረ መምጣቱ
 • ዳይሬክተሮች /ቡድን መሪዎች/ የሠራተኞችን ብቃት ለማሳደግ የመደገፍና የማማከር ሚናቸውን ለመወጣት የሚያደርጉት ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻሻለ መሆኑ፡፡
 • አመራሩ ከመቸዉም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ለለዉጡ በሰጠዉ ከፍተኛ ትኩረት እስከታችኛዉ መዋቅር ድረስ የሚታየዉ መነሳሳት አበረታች መሆኑ፤
 • እስከታች ድረስ መዋቅር ያላቸዉ ዳይሬክቶሬቶች ድጋፍና ክትትል ሲያደርጉ የሪፎርም ተግባራትን በቼክ ሊስታቸዉ በማካተት የሚደግፉበት አሰራር በየጊዜዉ መሻሻል ማሳየቱ፤
 • ሰራተኛ የሪፎርም ተግባራትን ለመፈፀም ያለዉ ተነሳሽነት ከቀን ወደ ቀንእያደገ መምጣቱ፤
 • በዞኖች የተቋቋመዉ የለወጥ አስተግባሪ ቡድን የሪፎርም ተግባራትን በባለቤትነት ይዞ ለመፈፀም እየሰራ ያለዉ ስራ ጅምሩ አበረታች መሆኑ፤

በአጠቃላይ የለውጥ ሠራዊት ግንባታ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማሳኪያ ቁልፍ መሳሪያ አድርጎ በእምነትና በባለቤትነት መንፈስ በመያዝ  በኩል ውስንነት የሚታይበት ነው፡፡  ስለዚህ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ዝርዝር የተግባር አፈፃፀም ላይ ግልጽነት በመፍጠር ሁሉም አመራርና ፈጻሚ  አደረጃጀቶችን በመጠቀም የልማትና መልካም አስተዳደር ግቦችን ርብርብ በማድረግ ውጤት ማስመዝገብ አስፈላጊና ለነገ የማይባል ሥራ ነው፡፡