Human Resource Management directorate

  1. የሠው ኃይል ሥራ አመራር ደጋፊ የሥራ ሂደት በቢሮው የሚያዘውን እቅድ ለማሣካትና በክልሉ የመንግስት ሠራተኞች መተዳደሪያ ደንቦችና መመሪዎችን መሠረት በማድረግ ለሠራተኛው ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር እና ሠራተኛውን ለማነሣሣት ሊያግዙ የሚችሉ ምደባዎች የቅጥር፣ የደረጃ እድገት፣ ዝውውር ፣የአጭርና የረዥም ጊዜ ሥልጠናዎች በተቀመጠው የአሠራር መመሪያ መሠረት ፍትሀዊነትን በማረጋገጥ መፈፀም የሚጠበቅበት ሲሆን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን ለማሣካት በበጀት አመቱ የታቀደውን ዕቅድ ለማሣካት ልዩ ትኩረት በመስጠት የነበሩትን የአመለካከት፣ የአሠራርና የክህሎት ችግሮችን በመለየት የተገልጋዩን እርካታና አመኔታ በማረጋገጥ አገልግሎት አሠጣጡን ፍትሃዊ እና ተደራሽ ለማድረግ የ2009 ዓመታዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

በአሁኑ ስዓትም በአዲሱ የስራ ምዘናና የደረጃ አወሳሰን ጥናት መሠረት 13 ባለሙያዎችን የያዘ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በማደራጀት ቢሮው ያስቀመጠውን የአምስት አመቱ የዕድገትና ትራስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲሁም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ያቀደውን ዓመታዊ እቅድ ሊያሣካ የሚችል ብቁና ጥራት ያለው የሰው ሀብት እንዲሟላ በማድረግ ላይ ነው፡፡

የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀምና በአገራችን እንዲመዘገቡ የሚፈለገውን ተከታታይ ዕድገት ለማምጣት የሰው ሃብት ልማትን ማሳደግ የተለየ ትኩረት ተሰጦት የሚሰራ ተግባር በመሆኑ ከአሁን በፊት ሰፊ ስራ ሲከናወን የቆየ ቢሆንም በዚህ ዓመትም የአጭርና የረዥም ጊዜ በእቅድ በመያዝ ተከናውኗል፡፡

በመሆኑም ከቢሮው የፑል አገልግሎት የሚያገኙ ተቋማትን ጨምሮ በ2009 በጀት ዓመት የታቀደውን የዕቅድ አፈጻጸም እንደሚከተለው የቀረበ ሲሆን ከተያዘው ዕቅድ አንጻር ያለው አፈጻጸም በመቶኛ ሲገለጽ በማነስ ወይም በመብለጥ የሚታየው ሥራዎች አገልግሎቱ ሲጠየቅ የሚሰሩ መሆናቸውን ግንዛቤ ሊያዝ ይገባል፡፡

2. ዓላማ

የቢሮውን ተልዕኮና ዓላማ ሊያሳካ የሚችል ብቁና ጥራት ያለው የሰው ሀብት እንዲሟላ ለማድረግ ነው፡፡

3. በበጀት ዓመቱ ለመፈፀም የተቀመጡ ግቦች

ግብ 1 የተገልጋዩችን እርካታና አመኔታ ማሻሻል

ግብ 2 የአጭርና የረዥም ጌዜ ስልጠናዎች በመስጠት የሠራተኛውን ብቃትና ተነሳሽነት ማሳደግ

ግብ 3 የሰራተኛውን ስምሪት ከደንብና መመሪያ አንፃር እንዲፈጸም ክትትል ማድረግ

4.  የቁልፍ ተግባር አፈጻጸም

4.1  የልማት ሠራዊት ግንባታ

  • የሰው ሃይል አጠቃቀም

በዳይሬክቶሬቱ ስር ሴት 11 ወንድ 2 በድምሩ 13 ሙያተኞች ያሉ ሲሆን  በትምህርት ዝግጅት ሲታይ 6 የመጀመሪያ ዲግሪ 3 ዲፕሎማ እና ሌሎች ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ናቸው፡፡

  • አደረጃጀት

የተደራጀ የልማት ሠራዊት ከመፍጠር አንጻር በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በአሰራር፣ በአደረጃጀትና በግብዓት አቅርቦት የሚታዩትን ችግሮች በመለየት እርስ በእርስ በመማማር በውይይትና በግምገማ  ዕቅዱን ለመተግበር ርብርብ በማድረግ ውጤት ለማስመዝገብ፣ በዳይሬክቶሬቱ የሚገኙ ሠራተኞች የልማት ሠራዊትን  የስራ መሣሪያና ማሰለጫ  እንዲያደርጉት ጥረትና ክትትል ተደርጓል፡፡ በዚህም መሠረት በዳይሬክቶሬቱ 2 የ1ለ5  እና 1 የልማት ቡድን እንዲደራጅ የተደረገ ሲሆን በዚህም ተግባራትን በየዕለቱ መረጃ በመለዋወጥ፣ ግምገማ በማድረግና በመማማር ሥራዎችን በቅልጥፍና በውጤታማነት ለመፈፀም የሚሰሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው፡፡

ከአሰራር አንጻር ቀደም ብለው የወጡና በዚህ ዓመትም ተሻሽለው ያሉ ደንቦችና የአሰራር መመሪያዎች በሁሉም ፈጻሚ ዘንድ እውቅና አግኝተው እንዲፈጽሟቸውና ለሥራ አጋር እንዲሆኑ የማስቻል፣ የቡድን ሥራዎችን በጋራ የመስራት ልምድ እየተሻሻለ እንዲመጣና በአቅምና በክህሎት ደረጃ የመረዳዳት መንፈስ እንዲሻሻል፣ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ተገልጋይን በወቅቱ ውሣኔ እንዲያገኙ የማድረግ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡