General Inforamation about ICT

መግቢያ

ግብርና ቢሮን በዘመናዊ የመረጃ መረብ የተሳሰረና የኮምፒዩተር ቴክኖሎጅዎችን የሚጠቀም ተቋም በማድረግ የሁለተኛውን የእድገትና ትራንሰፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት የጎላ ሚና እንዲኖረው በሰው ሃይልና በማቴሪያል ማጠናከር ይገባል፡፡

የስራ ሂደቱ በስሩ የሲስተም ማስተዳደር፣ የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የሶፍትዌር ልማት፣ የዳታ ማስተዳደር፣ የጅአይኤስ፣ የሶሺዮ-ኢኮኖሚክስና ስታቲስቲክስ ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነዚህን ክፍሎች በአንድ ላይ በማካተት የተደራጀ በመሆኑ ዳይሬክቶሬቱ ከግብዓት እስከ ውጤት የተሳሰረና መረጃን በአግባቡ ለማሳለጥ፣ ወቅታዊ፣ ታማኒና የተናበበ መረጃ ለተገልጋዩ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴከኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማቱና የሶፍትዌር ልማቱ የተለያዩ የመረጃ ማሰባሰቢያና ማደራጃ ዘዴዎችን በመጠቀም ማለትም መልክዓ-ምድራዊና መልክዓ-ምድራዊ ያልሆኑ /sPatial and non-spatial/ መረጃዎችንና ልዩ ልዩ የሶሺዮ-ኢኮኖሚክስ ጥናቶችን በአንድ ቦታና ማዕከል/ ቋት/ በማሰባሰብና በተስማሚ ቴክኖሎጂ (Automation) በመጠቀምና በማደራጀት የቢሮውን የመረጃ አቅርቦትና የመረጃ ልውውጥ ጥራት ያለው፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ የደንበኛውን ውጣ ውረድና ቅብብሎሽ እንዲቀንስ በማድረግ መረጃን በቀላሉ መጠቀም የሚያስችል አደረጃጀት ተፈጥሯል፡፡

በመሆኑም ባሳለፍነው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በዳይሬክቶሬቱ የሰው ሃይል የማàላት፤ አግባብነትና ጥራት ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እንዲገዙና በወቅቱ እንዲገቡ፤ በቢሮው የሚገኙ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጤንነትን ለመጠበቅ የሚያስችል አንቲቫይረስ ግዥ የመፈፀምና ተከታትሎ የማደስ፤ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ተከታታይነት ያላቸው የጥገናና የእንክብካቤ ሥራዎችን የማከናወን፤የኔትወርክ ጥገናና አድሚኒስትሬሽን ስራ ማካሄድ፡ሲሰተም የማስተዳደር እንዲሁም የተፋሰስ መረጃዎችን በጂ.ፒ.ኤስ የማሰባሰብ፤ በመስኖ የለማ መሬት በጂ.ፒ.ኤስና በጂ.አይ.ኤስ ታግዞ የማሰባሰብና መረጃን የማደራጀት፤ በቢሮው የሚገኙ ፕሮጀክቶችን የመደገፍ፤ ተሳትፎአዊ የማህበረሰብ ማኔጅመንት የሚዘጋጅላቸውን ደኖች መረጃ የማደራጀት እንዲሁም የዞን፡የወረዳና ማዕከላት ባለሙያዎችን አቅም የማሳደግ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ዳይሬክቶሬቱ የቢሮውን አሰራር ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከማድረግ አንፃርና አሰራሩን ወጪና ጊዜ ቆጣቢ በማድረግ በኩል እንዲሁም የቢሮውን መረጃ በአግባቡና ዘመናዊ በሆነ መንገድ አደራጅቶ ተደራሽ ከማድረግ ጋር ተያይዞ አመርቂ ስራ ያልተሰራ በመሆኑ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡     

ስለሆነም የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎረሜሽን ዕቅድ ዘመን አካል የሆነውን የ2010 በጀት ዓመት ለዘመናዊ አሰራርና ለቴክኖሎጂ ቅድሚያ በመስጠት የቢሮውን አሰራር ማሻሻልና ማሳደግ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር በመሆኑ ዳይሬክቶሬቱ አመታዊ ዕቅድ በሚከተለው አግባብ አዘጋጅaል፡፡

1.1የኢንፎርሜሽን ኮሙ/ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ራዕይ (Vision)

በ2017 የግብርናው ዘርፍ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመራና ተዓማኒነትና ወቅታዊ የግብርና መረጃ ተደራጅቶ ማየት፡፡

1.2 የኢንፎርሜሽን ኮሙ/ ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ተልዕኮ(Mission)

የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዘመናዊና ተዓማኒነት ያለውን መረጃ መጠቀም፤ ዘመናዊ አሰራርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሻሻል፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አቅሙ የጎለበተ ሰራተኛና አመራር እንዲሁም ዘመናዊ የግብርና ስርዓት መፍጠር፡፡

 1.3.  የኢንፎርሜሽን ኮሙ/ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት እሴቶችና የአሰራር

         መርሆዎች (Value and principles)

           1.3.1.. እሴቶችና የአሰራር መርሆዎች (Value and principles)

የዳይሬክቶሬቱን ዓላማ በማሳካትና የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት የሚከተሉትን እሴቶች በማጐልበት ይጠቀምባቸዋል፡-

 • ልጣፋና ውጤታማ አገልግሎነትን እናረጋግጣለን፣
 • ደንበኞች እርካታ ቅድሚያ እንሰጣለን፣
 • ርጥ ተሞክሮን እናስፋፋለን፣
 • ኢኮቴ ዕድገት ጋር እንራመዳለን፣
 • ልጽነትን፣ ተጠያቂነትን፣ አሳታፊነትን እናረጋግጣለን፣
 • ድናዊ የስራ መንፈስን እናሰፍናለን፣
 1. የእቅዱ ዓላማ፡

የእቅዱ ዋና ዓላማ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን በመከተል የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ ሲሆን ዝርዝር ዓላማዎቹም፡፡

 • ፈጣንና ዘላቂነት ያለው የግብርና ልማት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለማፋጠን የሚያስችሉ ዘመናዊ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን መዘርጋት፤
 • በየደረጃው ያለውን የግብርና አመራርና ባለሙያ የዘመናዊ አሰራርና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል፡
 • ዘመናዊ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከግብርና ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ማሰባሰብ፤ ማደራጀት፤መተንተን እና ለውሳኔ ሰጪ አካላት ተደራሽ ማደረግ                                                                                           
 • የግብርናን ተቋም ዕርስ በዕርስ በማስተሳሰር ለተገልጋዩ ቀልጣፋና አውቶሜት የተደረገ የዌብ ቤዝድ መረጃ አገልግሎት መስጠት
 • ልዩ ልዩ የአቅም ግንባታ ተግባራትን ማከናወን
 • ማንኛውም የክልሉን ግብርና ቢሮ መረጃ የሚፈልግ ህጋዊ አካል፣ ባለሀብት፣ አመራር ወዘተ… የማግኘት እድሉ እንዲኖረው አስተማማኝ የመረጃ ቋት ማደራጀት፡፡
 • ከተለመደው ፈጣን ያልሆነ የ Hard Copy መረጃ ልውውጥ መላቀቅ እንችል ዘንድ በተዋረድ እስከ ቀበሌ ድረስ የ ICT አቅም ግንባታ (የኮምፒተር አቅርቦት፣ የክህሎት ስልጠና፣ ኢንተርኔት አገልግሎት ወዘተ…) እንዲሟላ ማስቻል 

2.1.በዕቅድ  ትግበራ  ወቅት  የምንከተላቸው  መሠረታዊ  ስልቶች

የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዳሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ  አመርቂ ተግባራትን በማከናወን በግብረናው ዘርፍ የሚመዘገበውን ዕድገት ለመደገፍና የበኩሉን አስተዋፆ ለማድረግ መሰረታዊ የአሰራር አቅጣጫዎችን አዘጋጅቶ መግባት ይኖርበታል፡፡በዚህም መሰረት ዳሬክቶሬቱ ያቀዳቸውን ተግባራት ለማከናወን የሚከተላቸው መሰረታዊ የአሰራር አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

ዘመናዊ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን መዘርጋትና መተግበር በዕውቀት ላይ መመስረትና በቂ የፋይናንስ አቅምን ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም ዳይሬክቶሬቱ ስራውን ለማገዝ ከሚችሉ በቢሮውና ከቢሮው ውጪ ከሚገኙ ፕሮጀክቶችና ደጋፊ አካላት እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲዎችና ፌደራል ተቋማት ጋር በቅርበትና በትብብር ይሰራል፡፡

 • የግብርናን ምርትና ምርታማነትን የሚያግዙና አስተዋፆ የሚያደርጉ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ያደረጋል፡፡
 • የግብርና ምርትና ምርታማነት ሊለኩ የሚችሉና መነሻ ሁነው ሊያገልግሉ የሚችሉ መረጃዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የማሰባሰብ፡ የማደራጀት፤ የመተንተንና ተደራሽ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡
 • ለስራው ተገቢነት ያላቸውን ባለሙያዎች በመመደብ ከሚመለከታቸው  ዳይሬክቶሬቶች ጋር በጋራ በመሆን ሥራዎች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡
 • ከዞን፣ወረዳና ማዕከላት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ጋረ በቅርበት ይሰራል፡፡

2.2.የእቅዱ ስትራቴጂክ  ግቦች

 • የግብርናውን ዘርፍ ዕድገት የሚያፋጥኑ ዘመናዊ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን አቅርቦትና አጠቃቀም ማሳደግ
 • የግብርና ቢሮን አመራርና ፈፃሚ ባለሙያዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሻሻል
 • ዘመናዊ የመረጃ አሰባሰብ፤ አደረጃጀት፤ ትንተናና ተደራሽነትን ማሻሻል
 • በተቋሙ የሚገኙ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የአገልግሎት ጊዜ ማሻሻል
 • የዳይሬክቶሬቱን ፈፃሚ ባለሙያዎች አቅም ማጎልበት

3.ዋና  ዋና  ግቦች እና  ግቦችን  ለማሳካት የሚፈጸሙ  ተግባራት

  ግብ 1. የግብርናውን  ዘርፍ  ዕድገት የሚያፋጥኑ  ዘመናዊ  አሰራሮችንና  ቴክኖሎጂዎችን አቅርቦትና  

         አጠቃቀም ማሳደግ

 ዝርዝር ተግባር፡-

 • የቢሮውን ሲስተም ማስተዳደር፣ የዳታቤዝ ሲስተሙን ማስተዳደር፣ የኔትወርክ አስተዳደር ሥራ መስራት
 • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሀርድ ዌርና የሶፍትዌር ጥገና ማካሄድ፣የኔት ወርክ ጥገናና አድምኒስትሬሽን ስራ ማካሄድ
 • በቢሮው ውስጥ  ሪሴፕሽን ላይ LAN IP TV በመጠቀም የቢሮውን ስራ ለዕይታ ማብቃት፣
 • ለኮሌጆች የኔት ወርክ ዲዛይን ስራ ማካሄድ እና በጀት ተገኝቶ ኢንስታሌሽኑ ሲሰራ የምክር ግልጋሎት መስጠት
 • የቢሮውን የዌየብ ሳይት ማስተዳደር
 • በመደበኛ እና በፕሮጀክት ለሚገዙ የኤለክትሮኒክስ እቃዎች  እስፔስፍኬሽን ሰነድ ማዘጋጀት ፤ የጨራታ ሰነድ የመገምገም እንዲሁም  የኢንስፔክሽን ሥራ መስራት፣ እንዲሁም በዚሁ አግባብ ገቢ መሆናቸውን መከታተል፤
 1.  ግብ 2. የግብርና ቢሮን አመራርና ፈፃሚ ባለሙያዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀም  ማሻሻል

  • በየደረጃው ያለውን የክልል፣የዞን አመራርና ፈጻሚ ባለሙያ ኮምፒዩተር የመጠቀም አቅም ሊያሳድግ የሚችል ስልጠና መስጠት፣ እንዲሁም ለኮሌጆች እና ለዞን የአይቲ ባለሙያዎች  ድጋፍ መስጠት
  • በየደረጃው ያለውን የግብርና ፈጻሚ ባለሙያ ጂ.አይ.ኤስ የመጠቀም አቅም ማሻሻል
  • በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጁ መረጃዎችን የመጠቀም አቅም ማሻሻል
  • በዳይሬክቶሬቱና በአጋር አካላት የሚዘጋጁ ሶፍትዌሮች ላይ ስልጠና መስጠት እና ማስተባበር
  • ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ መረጃ ስፓሻል እና ስፓሻል ያልሆኑ መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የማደራጀትና የመተንተን ዘዴዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፤
  • በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎች ተከታታይነት ያለው የድጋፍና ክትትል ስራ ማከናወን

ግብ 3. ዘመናዊ የመረጃ አሰባሰብ፤ አደረጃጀት፤ ትንተናና ተደራሽነትን ማሻሻል

 • ለግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ስራዎች መረጃ ማሰባሰብና ማደራጀት የሚያስችል ዳታቤዝ ማዘጋጀት
 • ለክልል፡ ለዞንና ለወረዳ የግብርና ባለሙያዎች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት፤ ስልጠና ለወሰዱ ባለሙያዎችም ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
 • የቆላ እና የደጋ ፍራፍሬ ልማት ፖቴንሻልና ክላስተር ወረዳዎችን መለየት
 • የግብርና ቢሮ መሰረተ ልማት መረጃዎችን ስርጭትና ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ መረጃ ማደራጀትና ማሰራጨት
 • የክልሉን የደን ሽፋን  የሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖሎጅን በመጠቀም መረጃ ከተፈጥሮ ሃብት ጋር በመሆን ማሰባሰብ እና ማደራጀት
 • በክልሉ ከሚገኘው የደን ሽፋን ውስጥ የማህበራት፤ የመንግስትና ሌሎች ጥብቅ ደኖችን ስርጭታና ያሉበትን ሁናታ የሚያሳይ መረጃ ማደራጀትና ማሰራጨት
 • ከምዕራብ አማራ የተመረጡ አስር ወረዳዎች ላይ የባህር ዛፍ ሽፋንና ዲከረንስን ሽፋን የሚያሳይ መረጃን በሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖሎጂ የተጠናውን ጥናት ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት
 • የግብርና መረጃዎችን ማደራጀትና ለተጠቃሚ ማድረስ
 • የቢሮውን መረጃዎች በማደራጀት አንድ ዓመታዊ የመረጃ ሰነድ/መጽሔት  ማዘጋጀት
 • በክፍሉ የሚከናዎኑ ተግባራትን መረጃ አደራጅቶ መያዝ እና ለተጠቃሚ ምቹ ማድረግ
 • ለክፍሉ ተግባራት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን እንዲሟሉ ማድረግ
 • ሌሎች ተጨማሪ ስራዎችን ማከናወን

  ግብ 4. የዳይሬክቶሬቱን ፈፃሚ ባለሙያዎች አቅም ማጎልበት

 • በዳይሬክቶሬት አስተባባሪውና በፈፃሚ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ ማካሄድ
 • ልምዱን መቀመርና መጠቀም ዞኖች  እንዲጠቀሙበት በስርኩላር መልክ ማውረድ
 • ለፈፃሚ ባለሙያዎች ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስልጠናዎች በማፈላለግ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ
 • ከተለያዩ የቢሮ አይሲቲ ባለሙያዎች ጋር በአካል በመገናኘት የልምድ ልውውጥ ማካሄድ እና አጫጭር ስልጠናዎችን በማፈላለግ እና ፕሮፖዛል በማዘጋጀት የራስን አቅም ማሻሻል፣

5.እቅዱን  ለመተግበር  ሊያጋጥሙ  የሚችሉ  ተግዳሮቶች

 • የበጀት እጥረት
 • የሰው ኃይል እጥረት
 • በጋራ ከዳይሬክቶሬቶች ጋር ለሚሰሩት ሥራ የተፈለገውን ያህል ትብብር አለመኖር፣