ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ክስተት በክልላችን ያለው ገጽታ፤

ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ክስተት በክልላችን ያለው ገጽታ፤

ፈጣን  ሁሉን  አውዳሚ ተምች  ክስተት  በክልላችን   ያለው  ገጽታ

የአማራ  ክልል  ግብርና  ቢሮ  በ2010/11  4.4 ሚን ሄ/ር በማልማት  110 ሚ/ን  ኩ/ል  ለማምረት  አቅዶ  በመንቀሳቀስ  ላይ  ይገኛል  ፡፡ እቅዱንም  ለማሳካት በርካታ  የቅ/ዝግጅት  ስራዎችን  ወደ ማጠናቀቅ በመቃረብ  ወደ  ተግባር  ምዕራፍም  ተገብቷል ፡፡

ከመþር ስራ ባሻገር በመስኖ ልማትም በ2010 ዓም 1 039 000 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን ከ824 384 ሄክታር መሬት በላይ ማልማት ተችሏል፡፡ ከዚህም 144 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡ ሆኖም ግን በመስኖ ልማቱ ላይ ትልቅ ፈተና ተደቅኖበታል፡፡ ይþውም መጤ የአሜሪካ ተምች ነው ፡፡ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ የሚያደርገው በመስኖ ልማቱ ላይ ብቻ ተወስኖ ያለመቅረቱ ነው፡፡ በመስኖ እየለሙ ያሉ ሰብሎችን በከፍተኛ ደረጃ እያጠቃ ሲሆን የተምቹ የህይወት ኡደት የሚያቋርጥ ባለመሆኑ በቀጣይ የመþር ሰብል ልማትም ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መሆኑ ነው፡፡ ይህንን ጉዳይ ደግሞ በየደረጃው ያለ አመራር ባለሙያና አርሶአደር በውል የተገነዘቡት አይመስልም፡፡ ስለዚህ አሁን እያደረሰ ያለውን ጉዳትም ለመቀነስና ለቀጣይ የከመþር ሰብልም ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል የተቀናጀ ጥረት ከወዲሁ ማድረግ ያስፈልጋል  

 1. ይህ ተባይ  ምን በመባል  ይታወቃል  ?

አነሳሱና በሀገርና  በክልል ደረጃ መቸና እንዴት ተከሰተ  ? 

 • የተባዩ ምንነትና ስርጭቱ

 

 • ስሙ የአሜሪካ ተምች (Fall armyworm) ይባላል፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ክልላችን በቀናት ውስጥ ሰብሎችን የማውደም አቅም ስላለውና  በቀላሉ ለመግባባት የሚያስችል ስም መሰየም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱና ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ማለት ተሰይሟል፡፡

የተባዩ እሳት እራት መነሻው ደቡብ አሜሪካ  እና ካርቢያን ሃገራት  ናቸው ፡፡ ከአሜሪካ ወደ አፍሪካ የገባበት መንገድ በግልፅ ባይታወቅም ወደ አህጉራችን  በገቡ እፅዋት ችግኞች  አማካይነት ሳይሆን እንዳልቀረ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ እንዲሁም  ለእንቅስቃሴ ምቹ የነፋስ ሁኔታ ካለ አትላንቲክ ውቂያኖስን በማቋረጥ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ገብቶ ሊሆን እንደሚችል መላምት አለ፡፡ በአህጉራችን በ2008 ዓ.ም  አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ በቆሎ በሚያመርቱ  የናይጀሪያ፣ሳወቶሚ፣ ቤኒን እና  ቶጎ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶባቸዋል፡፡

ከፈጣን የመዛመት ባህሪው የተነሳ  ባለፈው አመት ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች በሀገራችን በበልግ ወቅት በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በመከሰት በበቆሎ አምራች አርሶ አደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶባቸዋል ፡፡ ከአንዱ ማሳ ወደ ሌላኛው ማሳ ፤ ቀበሌ ፤ ወረዳ  ፤ዞን  ፤ክልል ለመሸጋገር  የሚወስድበት ጊዜ በጣም አጭር ነው፡፡ ምክንያቱም እንቁላሉን የምትጥለው ቢራቢሮ  እስከ 500 ኪ/ሜ የመበረር አቅም ስላላት ነው፡፡በዚህም ምክንያ ተባዩ በ2009 ዓ.ም በደቡብ ክልል በተከሰተ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ወደ ክልላችን በመሸጋገር ግንቦት  10 ቀን 2009 ዓ.ም አካባቢ  በምእራብ ጎጃም ዞን ብር ሸለቆ አካባቢ በገቦ በቆሎ ሰብል ላይ ክስተቱ ታየ፡፡ቀጥሎም በቀናት ውስጥ በአዊ ዞን አየሁ እርሻ ልማት፤ደቡብ አቸፈር፤ሜጫ እያለ እያለ በ6 ዞኖች፤በ54 ወረዳዎችና በ699 ቀበሌዎች  ተዛምቶ የጥቃት ዘመቻውን ከፍቶ በተደረገው መጠነ ሰፊ ርብርብ በባህላዊ መንገድ 62 504 ሄክታር፤ በኬሚካል ደግሞ 36 135 ሄክታር በድምሩ 98 699 ሄክታር መከላከል የተቻለ ሲሆን ተባዩ ከተከሰተበት የማሳ ስፋት አንጻር 89.8 % ያህሉ ከጉዳት ተጠብቋል፡፡ ሆኖም ግን ተባዩ ራሱን ደብቆ በመቆየት የመራባት አቅም ስላለው ይþውና በመስኖ ልማቱ ላይ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል

 1. በመስኖ ልማት ላይ ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች የተከሰተባቸው ዞኖችና ወረዳዎች

በክልላችን በ10 ዞኖች በ31 ወረዳዎች ባሉ 96 ቀበሌዎች በተበታተነና በክላስተር በሚባል ደረጃ ክስተት እንዳለ በአሰሳና በክትትል ማረጋገጥ ተችሏል። በዝርዝር ሲታይ ሰ/ጎንደር ዞን (ጎንደር ዙሪያ፣ታች አርማጭሆ)፣ ደ/ጎንደር ዞን (ደራ፣ ፋርጣ፣ ፎገራና ሊቦ ከምከም)፣ ምዕ/ጎጃም ዞን(ጃቢ ጠህናን ፣ወምበርማና ሜጫ ቆጋ መስኖ)፣ ሰ/ሸዋ ዞን (ቀወት ፣ኤፍራታና ግድም፣ ጣርማ በር፣አንፃኪያ ገምዛ ና ሸዋ ሮቢት)፣ ምስ/ጎጃም ዞን (ደብረ ኤሊያስና ማቻከል ወረዳዎች)፣ አዊ ዞን(ጓንጓ፣አየሁ ጓጉሳ፣ቻግኒ ከተማ ፣ዚገም)፣ ደ/ወሎ (ተሁለደሬ)፣ ሰ/ወሎ (በጉባላፍቶና ቆቦ /ቆቦ ጊራና/)፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ(ባቲ፣ ደዌ ሃርዋና ጅሌ ጥሙጋ)፣ባህርዳር ከተማ አስተዳዳርና በሌሎችም ወረዳዎች ክስተቱ እየተስፋፋ ይገኛል።

 1. ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች ክስተት ስፋት፣ የጉዳት መጠንና የተሰራ የመከላከል ስራ

በቀበሌና በወረዳ በኩል እየተሰራ ያለው የአሰሳ ስራችን በዝርዝር ሲገመገም በጣም አዝጋሚና ውጤታማ ባለመሆኑ ተባዩ ሲከሰት በወቅቱ ባለመታየቱ በጥቂት አርሶ አደሮች ማሳ ላይ እስከ100% ጉዳት አድርሶባቸዋል ። ለአብነትም በአዊ ዞን አየሁ ጓጉሳ ወረዳ በ0.25 ሄ/ርደ/ወሎ& ሰ/ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ እስከ 100% የደረሰ ጉዳት ታይቷል። በምርት ዘመኑ ፈጣን ሁሉን አውዳሚ ተምች በአዲስ መልኩ የተከሰተባቸውን ወረዳዎች ጨምሮ በ2,948 ሄ/ር በበቆሎ ሰብል ላይ እንደተከሰተ ተረጋግጧል፤እስካሁን ባለ መረጃ ቆጋን ጨምሮ በ11 ዞን 17,124 ሄ/ር በቆሎ የተዘራ ሲሆን 8,266 /48.3%/አሰሳ ተካሂዷል'

 • የመከላከሉ ስራ በተመለከተ የተባዩ ክስተት ከተረጋገጠበት የበቆሎ ማሳ ውስጥ በባህላዊ በ267ሄ/ር በኬሚካል 1,303 ሄ/ር በድምሩ 1,571 ሄ/ር ከተከሰተበት ማሳ /53%/ ላይ የመካከል ስራ ተሰርቷል፤
 • አፈፃፀም በጥቅሉ ሲታይ ዝቅተኛ በመሆኑ በቀጣይ የመከላከል ስራ ያልተሰራባቸው ማሳዎች ለቀጣይ ስነ ህይወት ውህደቱን ለማስቀጠል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። 
 • የቀጣይ ወራት ሙቀት መጨመርና በክልሉ የበቆሎ ማሳ በመስኖና በመþር በስፋት የሚዘራበት ወቅት በመሆኑ ተባዩ የመከሰት ሰፊ እድልይኖረዋል።

 

 1. መከላከያ ዘዴዎች
  1. አሰሳ፡-
   ሰብልን ከጉዳት ለመከላከል ከሁሉ አስቀድሞ መሰራት ያለበት የእለት ተግባር የተባይ አሰሳ መሆን አለበት፡፡የአሜሪካ ተምች በሰብል ላይ የሚያደርሰው ጉዳት አስከፊ በመሆኑ የነፍሳት ተባይ አሰሳ ማድረግ ወሳኝ ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ የአገዳና ሌሎች  ሰብሎች  አምራች አርሶ አደሮች  ማሳቸውን በወቅቱ በመጎብኘት ነፍሳት ተባዩ ከተከሰተ በመጀመሪያው የዕድገት ደረጃ ላይ የመከላከል ርምጃ መውሰዱ ውጤታማ መሆን ያስችላል፡፡
  2. ባህላዊ መከላከያ ዘዴዎች

 

 • በመዝራት በ|ላ የሚመጣውን የአሜሪካ ተምች ወረርሽኝ ማምለጥ ይቻላል፡፡
 •   ፈጥኖ ደራሽ የሰብል ዘሮች ካሉ ጥቅም ላይ ማዋል፡፡
 • ፈረቃ መጠቀም
 • የአሜሪካ  ተምች ወረርሽኝ ባለባቸው አካባቢዎች ደጋግሞ በማረስ ወይም በመከስከስ የሙሽሬውን ቁጥር መቀነስ
 • ተምች ክስተትበግጦሽ  መሬት ከሆነ  በጨፈቃ መጨፍጨፍ፤ ግንድ/ ድንጋይ ጨፈቃላይ ጭኖ  መጎተት፣
 •   መንዳት፤ ወደ ማሳ እንዳይገባ ቦይ በመስራት ቦይ ውስጥ ሲገባ  መጨፍጨፍ፣
 • በመነስነስ ማቃጠል
 • አደር ማሳ ክስተቱ አነስተኛ ከሆነ በእጅ በመልቀም እንቁላሉን እና ትሉን መግደል
 •   በአርሶ አደሩ የሚተገበሩ የመከላከያ ዘዴዎች ማከናዎን፡
  1. -ነፍሳት ተባይመርዝ መጠቀም
 • ሰብል ቡቃያ  በነፍሳት ተባዩ  5% ጥቃት ከደረሰበት ወይም ከተዘራ እስከ 30 ቀናት ውስጥ አዳጊው የበቆሎ ቡቃያ ተክል  ክፍል 20%  ጥቃት ከደረሰበት የፀረ ነፍሳት ተባይ መርዝ መርጨት አለበት
 • ሰብል ቡቃያ  በነፍሳት ተባዩ  በአንድ አዳጊ የማሽላ ቡቃያ ተክል  ከ1-2 ትሎች/ ዕጭ  እና በአንድ ተክል ራስ 2 ትሎች ከታየ  የፀረ ነፍሳት ተባይ መርዝ መርጨት አለበት
 • ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ የፀረ ነፍሳት ተባይ መርዞች፡-ሴቪን 80% WP በውሃ የሚበጠበጥ ዱቄት 1.5 ኪ.ግ /ሄ/ር.ዱርስባን 48% EC በውሃ የሚበጠበጥ ፈሳሽ 1.0ሊትር/ ሄ/ር  ማላታዩን 50% EC በውሃ የሚበጠበጥ ፈሳሽ 2.0ሊትር/ሄ/ር. ካራቴ 5% EC በውሃ የሚበጠበጥፈሳሽ 300 ሚ.ሊ/ሄ/ር.በመቀም መከላከል ይቻላል'

 

 • ማጠቃለያ ቅድሚያ ለመስኖ ሰብል ትኩረት በመስጠት አውዳሚ ተምችን በመከላከል በቀጣይ በመþር ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለባህላዊ መከላከል ቅድሚያ ሰጥተን ካልተቻለ በኬሚካል በመከላከል ያቀድነውን የምርት ግብ ለማሳካት ሁሉም የሚመለከ ተው አካል ተቀናጅቶ ሊሰራ ይገባዋል በማለት ይክልሉ ግብርና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ወቅታዊ መልእክቱን ያስተላልፋል

 

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

                    ስልክ ቁጥር            0582265501

          0582205856

Facbook =         amhara agricalture bureau

Website=         www.amhboard.gov.et

Email=         agri@amhara.gov.et

 

 • አስቀድመን በመከላከል በምርት ላይ ሊደርስ  የሚችለውን ጉዳት   ለመቀነስ እንረባረብ!!”
 • ቀን :- መጋቢት 2010 ዓ.ም

 

publicrelation