የግብርና ሰሞንኛ በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሪክቶሬት የሚዘጋጅ የቢሮ ውስጥ የዜና መጽሄት ህዳር 2011 ቁ.54 የሰሜን ሸዋ አርሶ አደሮች ስራቸው በሜካናይዝድ ግብርና መደገፍ እንደሚገባው ጥያቄ አቀረቡ

የግብርና ሰሞንኛ በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሪክቶሬት የሚዘጋጅ የቢሮ ውስጥ የዜና መጽሄት ህዳር 2011 ቁ.54 የሰሜን ሸዋ አርሶ አደሮች ስራቸው በሜካናይዝድ ግብርና መደገፍ እንደሚገባው ጥያቄ አቀረቡ

(በሽፈራው ተስፋዬ መንክር)
በሰሜን ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ዘርሶ አደሮች በሰው ጉልበትና በበሬ ጫንቃ የሚያካሂዱት የእርሻ ስራ ጊዜ ያለፈበት፤ጊዜና ጉልበት አባካኝ በመሆኑ ወደ ሜካናይዝድ ግብርና ለመቀየር መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥያቄ አቀረቡ፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ህዳር 13 ቀን 2011 ዓ›ም በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ የገበሬዎች በዓል አዘጋጅቱዋል፡፤ በበአሉ ላይ የእርሻና እንስሳት ሀብት ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴንን ጨምሮ በርካታ የፌዴራል፤የክልል፤የዞን፤ የወረዳና የቀበሌ አመራርና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
እንግዶቹ በሞረትና ጅሩ ወረዳ በሶስት ቀበሌዎች በመዘዋወር በኩታ ገጠም ማሳ የተካሄደ የስንዴ ልማት ጎብኝተዋል፤ በእንዋሬ ከተማ የመሰብሰቢያ አዳራሽም የዞኑ አጠቀላይ የልማት እንቅስቃሴ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ውይይቱን የእርሻና እንስሳት ልማት ሚስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን ፤የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው፤የአማራ ክልለ ግብርና ቢሮ ሐላፊ ዶክተር ቦሰና ተገኝ እና የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ መርተውታል፡፡ በግብርና ቢሮ በሚዘጋጀው‹‹ የግብርና ሰሞንኛ ›› የቢሮ መጽሄት በቀ. 53 ካቀረብንላችሁ ዘገባ ቀጣዩ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የሞረትና ጅሩ አርሶ አደሮች ካቀረቧቸዉ የ‹ይሟላልን› ጥያቄዎቻቸዉ ዉስጥ በእለቱ የተጎበኘዉ፣ ከስፋቱ አኳያ በእግር ተዘዋዉሮ ለመጎብኘት ፍጹም የማይታሰብ፤ በመኪናም ሆኖ እንኳን የአንድ ኩታ ገጠም ማሳ ከአንደኛዉ ጫፍ ተነስቶ ሌላኛዉ ጫፍ ለመድረስ ብዙ ጊዜ የሚፈጅ መሆኑን ጎብኝዎቹ እንዳዩትና እንደተገነዘቡላቸዉ በመጥቀስ አርሶ አደሮቹ ይህንን የማሳ ሰብል በሰዉ ጉልበት ለመሰብሰብ እጅግ አስቸጋሪ፤ አድካሚና ላልተገባገ ወጪ የሚዳርጋቸዉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የሞረትና ጅሩ ወረዳ አርሶ አደሮች በማሳ የተጎበኘዉ ሰብል በእንደዚያ ሁኔታ በኩታ ገጠም የለማበት ዋናዉ ምክንያት ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ መሆኑን ጠቅሰዉ በገዢዎቹ የዱቄት ፋብሪካዎች ተመራጭና ጥራት ያለዉ ምርት ለማቅረብ የሚቻለዉ በኮምባይነር ታጭዶና ተወቅቶ ሲቀርብ ጥራቱን መጠበቅ እንደሚያስችለው ጠቅሰዋል፤ ይሄዉ የተባለዉ መሳሪያ እድዲቀርብላቸዉ በተደጋጋሚ ለመንግስት አካላት ቢያሳዉቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸዉም በምሬት ተናግረዋል፡፡ በሰዉ ጉልበት የሚካሄደዉ አጨዳና ዉቂያ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስወጣቸዉ ከመሆኑ በተጨማሪ ጥራቱን እንደሚያጓድልባቸዉ ነዉ አርሶ አደሮቹ የተናገሩት ፡፡ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የመበላሸት አጋጣሚም ሊከሰት እንደሚችል በመጠቆም የ‹‹ኮምባይነር ይቅረብልን›› ጥያቄያቸዉን ለሚኒስትሩና አብረዉ ለታደሙት የመንግስት ሀላፊዎች አሰምተዋል፡፡
‹ የምናመርተዉን ምርት እያዘዋወረ ተደራሽ ለማድረግ ከትልልቅ ከተሞች የሚያስተሳስር መንገድ ይሰራልን› የሚለዉም ሌላዉ ከአርሶ አደሮቹ የቀረበ ጥያቄ ነበር፡፡ ‹ገበያን መሰረት ያደረገና ለገበያ አልሞ የሚያመርት አርሶ አደር መፍጠር› የሚለዉ የግብርና ፖሊሲ‹ ከተፃፈበት ወረቀት መሬት ይዉረድ1› የሚል አንድምታ ያለዉ ጥያቄ ከወደ ጅሩዎች ተሰንዝሯል፡፡ የመንገድ ጥያቄያቸዉ ምርትን ከወረዳዉ ለማዉጣትና በቀላሉ የግብርና ግብዐቶችን ማጓጓዝ ከማስቻሉም ባሻገር አርሶ አደሮቹ ‹ በመንገድ ዳር ያሉ የአበባ እህሎች በአቧራ ጉዳት እንዳይደርስባቸዉና ጥራታቸዉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስብን ያስችላል›› ብለዋል
የሞረትና ጅሩ ወረዳ አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎችን ለመተግበር ዝግጁነታቸዉን በመግለጽ ምርታቸዉን ተረክቦ የሚያቀነባብር የዱቄት ፋብሪካ እንዲከፈትላቸዉ ጥያቄም አቅርበዋል፡፡ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ምርምር አስፈላጊ ጠቃሚም መሆኑን ከመግለፅ ባሻገር በዞኑ የምርምር ማዕከል ይከፈትልንም ጥያቄም አቅርበዋል፡፡
ከላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች በርካታ የመናገር ዕድል ያገኙ ሁሉ ተቀባብለዉታል፡፡ አንድ የወረዳዋ አርሶ አደር ‹አስታዋሽ ባጣዉ ህዝብ ስም ሺ ጊዜ እንኳን ደህና መጣችሁ እላለሁ!› በሚለዉ የምጸት አነጋገር ጀምረዉ ‹ይወገድ ሰቆቃ› በሚል ርዕስ ባዘጋጁት ግጥም ችግራቸዉን አቅርበዋል፡፡
‹ዛሬ የተነሱትና የሚነሱት ጥያቄዎች አዲስ አይደሉም፤ በየአመቱ የሚነሱ ናቸዉ፣ ከማንሳት ባሻገረው ምንም ለዉጥ የለም፤ ባለፈዉ አመት ጠቅላይ ሚኒስትሩ (የቀድሞው፤አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ) እዚህ ወረዳ ለተመሳሳይ ጉብኝት በመጡበት ጊዜ ያቀረብናቸዉ ችግሮቻችን በዚህ አመት(በ2011) እንደሚቀርፉልን ቃል ገብተዉልን ነበረ፤-ግን አልተፈፀመልንም፡፡ ባለፈዉ አመት ለግብርና ሚኒስትሩ (የቀድሞው ዶክተር እያሱ በርሄ) በተመሳሳይ ያቀረብናቸዉ ችግሮቻችንን በዚህ አመት እንደሚፈታ ቃል ገብተዉልን የነበረ ቢሆንም ዘንድሮም አልተፈታልንም›› በማለት የወረዳዉ አርሶ አደር ተስፋ ወደ ማጣት መግባቱን አንድ አርሶ አደር ተናግረዋል፡፡
አርሶ አደሮቹ በምርት ዘመኑ የግብአት አቅርቦ ችግር እንደገጠማቸውና ችግሩ የዘወትር መሆኑን የተናገሩት ‹‹እንደተለመደው›› በሚል ቃል ነው፡፡ የግብአት አቅርቦት ችግር ዉስጥ ሁነዉ ይሄንን ስራ ማከናወናቸዉን የገለጹት ሌላው አርሶ አደር የፈለገዉን ዘር በሚፈልግበት ወቅት ሊቀርብ ባለመቻሉ አርሶ አደሩ ሌላ ሰብል ለማምረት መገደዱንና ለአብነት ያህል የምስር ሰብልን ጠቅሰዋል፡፡ ዝግጅት ያልተደረገበት እና ከዕቅድ ውጭ የተዘራው የምስር ሰብል በበሽታ በመጠቃቱ የተጠበቀዉን ምርት ማግኘት እንደማይቻል ጠቅሰዉ አርሶ አደሩ ለዚህ ሰብል ልማት ያፈሰሰዉ ጉልበት እንዳለ ሆኖ በብድር ወስዶ የተጠቀመዉ የማዳበሪያ ገንዘብ እንዴት አድርጎ፣ ከየት አምጥቶ ነዉ የሚከፍለዉ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡
( በሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በተካሄደው የገበሬዎች በአል በአርሶ አደሮቹ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾችና ማጠቃለያ በሚቀጥለው የዜና መጽሄት ቁ.55 ይቀርባል፡፡)

publicrelation