የግብርናና የሚዲያ አካላት የንቅናቄ መድረክ ጥሪን ይመለከታል

የግብርናና የሚዲያ አካላት የንቅናቄ መድረክ ጥሪን ይመለከታል

ቁጥር፡ ህ/ግ/70/1/1/4
ቀን፡ 29/08/2011 ዓ.ም
ለ15ቱ የዞን ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት
ባሉበት

ጉዳዩ ፡- የግብርናና የሚዲያ አካላት የንቅናቄ መድረክ ጥሪን ይመለከታል
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በክልሉ ከሚገኙ የሚዲያ አካላት ጋር በቢሮው ዕቅድና አፈጻጸም፣ የሕዝብ ግንኙነት ተግባራት፣ በሚዲያው ሚና እና ቀጣይ የክረምት የግብርና ልማት ስራዎች ዙሪያ ሰፊ የጋራ ውይይት ለማድረግ #የግብርናና ሚዲያ አካላት የንቅናቄ መድረክ; ግንቦት 4 ቀን 2011 ዓ.ም በደቡብ ጎንደር ዞን በደብረ ታቦር ከተማ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የመምሪያው ኃላፊ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ጥዋት በ2፡30 እንዲገኙ እየጋበዝን ስም ዝርዝራቸውንና የደሞዛቸውን መጠን የሚገልጽ መገጣጠሚያ ደብዳቤ ይዛችሁ እንድትመጡ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

publicrelation