የክልሉ ግብርና ልማት የ6ወር አፈፃፀም ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ

የክልሉ ግብርና ልማት የ6ወር አፈፃፀም ውጤታማ መሆኑ ተገለፀ

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የ12 ዞኖችና የ3ከተማ አስተዳደሮች ግብርና መምሪያዎች የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ከየካቲት 20-21/2010 ዓ/ም በደብረ ታቦር ከተማ የስራ ግምገማ አካሂዷል፡፡ በግምገማውም በተፈጥሮ ሐብት ፣በመስኖ ልማት በስራ እድል ፈጠራና ሌሎች የግብርና ልማት ስራዎች አፈፃፀም ውጤታማ እንደሆነ በግምገማው ስምምነት ላይ ተደርሶበታል፡፡ በተለይም ሁሉንም የግብርና ልማት ስራዎች በለውጥ ሰራዊት የተደራጀ እንቅስቃሴ የመጣ ውጤት እንደሆነ መተማመን ላይ ተደርሷል፡፡ ይሁን እንጅ የሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች አፈፃፀም ተመሳሳይ እንዳልሆነ የታየ ሲሆን እነ ደቡብ ጎንደር ፣ ምዕራብ ጎጃም ፣ ደቡብ ወሎ ፣ ዋግ £ምራ ፣ ከሌሎች በተነፃፃሪ የተሻለ አፈፃፀም ሲኖራቸው እነ ምዕራብ ጎንደር ፣ሰሜን ጎንደርና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖች በዝቅተኛ አፈፃፀም የታዩ ሲሆን ሌሎች መካከለኛ ደረጃ ያሉ መሆናቸውን ተገምግሟል፡፡በዚህ አመት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅትና ከእቅዶቻችን አንፃር ተወስዶ ሲታይ ዞኖችና ወረዳዎች ያስመዘገቡት ውጤት የተሻለ እንደሆነ የግብርና ቢሮ ኃላፊው አቶ ፍስኃ ወ/ሰንበት ገልፀዋል፡፡ የልማት ሰራዊቱን ጉድለቶች ለቅሞ በመለየትና በማስተካከል በዋና ዋና ተግባራት ላይ አተኩሮ እንዲገነባ በማድረግ በመጨረሻ ጥሩ ለሰሩ ከቢሮ ጀምሮ የማበረታቻ ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ እንደሚሆንና የስራ ግምገማውም ሳይቆራርጥ መቀጠል እንዳለበት የቢሮ ሃላፊው የስራ መመሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

webAdmin