የአነስተኛ መስኖ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ

I- መግቢያ

የአማራ ክልል ሰፊ የገፀ ምድርና ከርሰ ምድር ውሃ ሃብት የሚገኝበት አካባቢ ነው፡፡ የተለያዩ መረጃዎችን በመጠቀም በተደረገዉ የገፀ ምድር ውሃ የፖቴንሻል ግመታ ጥናት መሰረት ብቻ የአማራ ክልል 1.2 ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት በመስኖ ሊያለማ የሚችል የውሃ ሀብት ክምችት ያለው መሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ 

ስለዚህ ግብርናውን  አስተማማኝና ቀጣይ ለማድረግ በዝናብ ላይ የተመሰረተው የሰብል ልማት በመስኖ ልማት እንዲታገዝ የክልሉ መንግስት ሰፊ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት በርካታ ጊዜያዊና ቋሚ ወንዞች፣ ምንጮችና ሃይቆች ላይ የመስኖ አውታር ግንባታ ስራዎችን በማከናወን ለመስኖ ልማት ሊውል የሚችል ውሀ ማቅረብ ተችሎል፡፡

በምዕራብ አማራ አካባቢዎች በዝቅተኛ ወጭ ሰፋ ያለ የመስኖ መሬትን ማልማት የሚያስችል እድሉ ስላለ በርካታ የመስኖ መሰረተ ልማት አውታሮች ሲሰሩ በምስራቅ አማራ ግን ከመሬቱ ወጣ ገባነትና ከውሀ ሀብት ማነስ በተያያዘ የመስኖ አውታር ግንባታ ወጭውን ከፍ ሲያደርገው የሚያለማው መሬት ዝቅተኛ ስለሚሆን ከፕሮጀክት አዋጭነት ጋር ተያይዞም ተመራጭነቱ አናሳ ስለሆነ በዚህ የክልሉ ክፍል የተፈለገውን ያህል የመስኖ መሰረተ ልማት ስራውን ማስፋፋት አልተቻለም፡፡

ነግር ግን በ2008 አመት የተከሰተው የድርቅ ችግር በምስራቅ አማራ ውስን በሆኑ የምዕራብ አማራ አካባቢ ያደረሰው ጉዳት ከመቼውም ጊዜ በላይ በሰብልና በእንስሳት ላይ የከበደ ስለነበር በምንከተለው የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታ አማራጮቻችን ላይ ጊዜ ወስደን በማሰብ ከፕሮጀክት አዋጭነት ባሻገር በዚህ አካባቢ ያሉ እንስሳትን በህይወት ለማቆዬትና ሰው በአካባቢው ተረጋግቶ እንዲኖር ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ በመስኖ መሰረተ ልማትና ውሀ ማሰባሰብ ስራዎች እንዲቃኙ በማድረግ ወደ ስራ ለመግባት ተችሎል፡፡

ይህን የትኩረት መስክ መሰረት በማድረግም ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው በድርቅ በሚጠቁ አካባቢዎች ላይ ወደ ስራ የተገባባቸው ስራዎች ስንመለከት ለጎርፍ ውሀ ለማሰባሰብ የማሶኖሪ ግድብ ስራ፣ በወንዞች ላይ ያለውን ውሀ ለመጠቀም ዘመናዊ ወንዝ ጠለፋ ፣ በምንጮች ላይ ያለውን የውሀ ሀብት ለመጠቀም ምንጭ ማጎልበትና የካናል ስራ ናቸው ፡፡ እነዚህም ስራዎች በዚህ አመት የቀጠሉ ሲሆን በ2009 ዓ.ም ላልተጠናቀቁት እሰከ መጋቢት 30 እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በ 2010 ዓ.ም አዲስ የሚሰሩ ስራዎች ደግሞ የጥናትና ዲዛይን ስራቸው ተጠናቆና ተገምግሞ ወደ ግንባታ ምዕራፍ ተሸጋግሮ ይገኛል፡፡

በ2009 ዓ.ም  61 ወንዝ ጠለፋዎች፣ 74 የማሶነሪ ግድቦች፣ 13 የቦይ ማራዘም ስራዎች፣ 2 ምንጭ ማጎለበት በድምሩ 150 ፕሮጀክቶች ተጀምረው አባዛኞቹ በመጠናቀቃቸው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ በእነዚህም ፕሮጀክቶች ወንድ 21463 ሴት 11435 በድምሩ 34611 ሰዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡  የግድብ ፕሮጀክቶቹ የተሰሩት ውሃ አጠር አካባቢ በመሆኑ ከሚያለሙት መስኖ በተጨማሪ ለ 62208 የቤት እንሰሶች የመጠጥ ውሃ ምንጭ ሆነዋል፡፡ ፕሮጀክቶቹን ለማስፈፀም 92 ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ለ 460 የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን መኃንዲሶች የስራ እድል አግኝተውበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በግንበኝነት በአናፂነት እና በቀን ሰራተኝነት 8870 ሰዎች ጊዜያዊ የስራ እድል አግኝተውበታል፡፡

በተመሳሳይ መንገድ በ2010 ዓ.ም ለሚሰሩ የግንባታ ስራዎች የጥናትና ዲዛይን ስራ የተሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰአትም 481 የመስኖ አውታርና የውሃ ማሰባሰቢያ ስትራክቸሮች የቦታ ልየታ ተደርጎ 204 በሚሆኑት ቦታዎች የዲዛይን ዳታ ተሰብስቧል፡፡ የጥናት እና ዲዛይን ዶክመንት ዝግጅትን በተመለከተ 173 ፕሮጀክቶች የዲዛይን ዶክመንታቸው ተዘጋጅቶ በዞን ደረጃ ግምገማ ተደርጓል፡፡ የ 30 ፕሮጀክቶች የዲዛይን ዶክመንቱ ዝግጅት በሂደት ላይ ነው፡፡

በ2010 ዓ.ም በግብርና እድገት ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ ከሚሰሩ የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታዎች አንፃር የእጅ ዉሃ ጉድጋድ ጨምሮ 142 ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን የተሰራላቸው ቢሆንም የግንባታ ዉል የተሰጠባቸዉ 98 ፕሮጀክቶች ናቸዉ፡፡ ከዚህ ዉስጥ 51 ፕሮጀክቶች የመሰረት ቁፋሮ ስራቸው በመጠናቀቅ ላይ ሲሆኑ 13 ፕሮጀክቶች የግንባታ ስራ ጀምረዋል፡፡ በመደበኛ በጀት ከሚሰሩ የመስኖ መሰረተ ልማት የግንባታ ስራዎች አንፃር 35 ፕሮጀክቶች የዲዛይን ስራቸው ተጠናቆ 29 ፕሮጀክቶች ወደስራ ገብተዋል፡፡ቀሪዎች በውል ሂደት ላይ ናቸው፡፡

በሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ከሚሰሩ ስራዎች ጥናታቸዉ የተጠነናቀቁ ፕሮጅክቶች ብዛት 103 ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ ወል የተያዘላቸው ፕሮጅክቶች ብዛት 90  ናቸው፡፡ ዉል ከተያዘላቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ስራ ጀምረው በመስራት ላይ ያሉ 68 ፕሮጅክቶች ሲሆኑ ስራ ያልጀመሩ ደግሞ 22 ፕሮጅክቶች ናቸው፡፡

 

በ2010 ዓ.ም የተከናወኑ ባህላዊ እና ዘመናዊ የመስኖ አውታሮችን ወደ ስራ ከማስገባት አንፃር ብዙ መንግድ የተሄደ ሲሆን በሪፖርት አደራረግ እጥረት የሁሉም ዞኖች ስራ በእዚህ ሪፖርት ያልተካተተ ቢሆንም በቢሮ ደረጃ የደረሰው መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 ተ.ቁ

ዝርዝር ተግባራት

መለኪያ

የዓመቱ  ዕቅድ

 እስከዚህ ሩብ ዓመት

አፈፃፀም በ%

5.1

ወደ ስራ የገባ ባህላዊ ወንዝ 

 

30537

13692

44.83741

 

ነባር

ቁጥር

28153

18882

67.06923

 

አዲስ

ቁጥር

2384

3045

127.7265

5.2

ባህላዊ ምንጭ ጠለፋ

 

36646

29819

81.37041

 

ነባር

ቁጥር

34111

27942

81.91492

 

አዲስ

ቁጥር

2535

1877

74.04339

5.3

ዘመናዊ ወንዝ ጠለፋ

 

1030

717

69.61165

 

ነባር

ቁጥር

891

661

74.18631

 

አዲስ

ቁጥር

139

56

40.28777

5.4

ዘመናዊ ምንጭ ጠለፋ

 

659

412

62.51897

 

ነባር

ቁጥር

618

407

65.85761

 

አዲስ

ቁጥር

41

5

12.19512

5.6

የእጅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ

 

566325

341397.8

60.28302

 

  ነባር

ቁጥር

450165

327220

72.68899

 

  አዲስ

ቁጥር

116160

14177

12.20506

                                                                                                                                                                                ሚያዝያ 9 2010

Undefined