``የአርሶ አደሩ ተመራማሪ ጥሪ``

``የአርሶ አደሩ ተመራማሪ ጥሪ``

ወጣት አርሶ አደር ሞገስ አለሙ ፈረደ ይባላል
ተወልዶ ያደገው በሰሜን ጎንደር ዞን በቀድሞው ወገራ ባሁኑ ኪንፋዝ በገላ ወረዳ በአዲስጌ ጊዮረጊስ ቀበሌ ወረዳ ሲሆን አሁን የሚገኙትና የስራ ቦታቸው ቋራ ወረዳ ነው::
በልጅነቱ እናቱን በሞት በማጣቱ ከብት እየጠበቀ ነው ያደገው በዚያን ወቅት ይርበው ስለነበር የተለያዩ የዕጽዋት ዝርያዎችን እየዘነጠፈ ይቀምስ ነበር፡፡ ከቀመሳቸው ዕፅዋቶች ሶስቱ ለየት ያሉና የሚመች ጣዕም ያላቸው ሆኖ ያገኛቸዋል፡፡በመሆኑም የርሃብ ማስታገሻና የዘወትር ምግብ ያደርጋቸውና ሱስ ይሆኑበታል::
ያኔ የ12 ዓመት ልጅ ነበርና እያደገ ሲሄድ ለምን የሻይ ቅጠል ቅመም አይሆኑም የሚል ሃሳብ መጥቶለት ወደ መንግስት ቤት ቋራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ጎራ በማለት ሃሳቡን ያስረዳል፡፡ የቋራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤትም ወደ ሚመለከተው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ይጽፍለትና ትግሉን ይጀምራል:: አጠቃላይ ሂደቱን ለማስረዳት የቦታና የጊዜ ጥበት ስላለ ወደ ዋናው መዳረሻ እንውሰዳችሁ፡፡
.የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ሰጥቶታል::
.የኢትዮጵያ ጤናና ስነ-ምግብ ኢንስቲቲዩት ከመርዝነት ነፃ መሆናቸውን አረጋግጦለታል::
.የወንዶ ገነት ግብርና ምርምር ማእከል ለወጣቱ ተመራማሪ የተመራማሪነትን ስልጣን አጎናጽፎታል::
.የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት የክልሉ ግብርና ቢሮ እና ሌሎችም የድጋፍና የእውቅና ደብዳቤዎች ሰጥተውታል
.ለምርት ስራው የሚሆን 100 ሄክታር መሬት የሚስፈለገው ቢሆንም እስካሁን 69 ሄክታር መሬት የወረዳው መሬት አስተዳደር ያስረከበው መሆኑንና ቀሪው በሂደት ላይ እንዳለ ገለጾልናል::
.የዕፅዋቶች ስም ጌሽታ አባጢማራና ጡመር ይባላሉ::
.በቋራ፣በጉባና ወልቃይት ወረዳዎች ኩታ ገጠም በሆነ መልኩ በስፋት ይገኛሉ::
.በዓመት እስከ 20,000 ኩንታል የሻይ ቅጠልን የሚተካ ምርት መሰብሰብ እንደሚችል ይናገራል ወጣቱ ተመራማሪ አደር ሞገስ አለሙ ፈረደ
ትብብር የሚጠይቀው
.የ1.4 ሚሊየን ብር ፕሮጀክት አስጠንቷል
.ከዚህ ውስጥ 10% የሚሆነውን ብቻ እሱ መሸፈን እንደሚችልና ቀሪውን ግን ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በመጋራት ፕሮጀክቱን ዕውን ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት እንዲታገዘ ጥሪውን ያስተላልፋል ወጣት ተመራማሪ አርሶ አደር ሞገስ አለሙ፡፡
.ሻይ ቅጠል ቅመም በአረንጓዴ እና በቀይ መልኩ እያዘጋጀ የአካባቢው ማህበረሰብ እየተጠቀመበት እንደሆነ ገልፆልናል፡፡
.በመሆኑም በሀገራችን እንዲህ ያልታዩና ያልተፈተሹ በርካታ ሀብቶች ስላሉ ትኩረት ለአካባቢያችን ያልተጠቀምንባቸው ሀብቶች እንስጥ እያልን ተመራማሪ አርሶ አደር ሞገስ አለሙን በ 0918 26 07 50 ወይም የግብርና ቢሮን ህዝብ ግንኙነት ክፍል በ0913 48 31 37, ወይም 058 226 55 01 በመደወል ዝርዝር መረጃ ማግኘት የሚቻል መሆኑን የግብርና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ይገልፃል፡፡
ከተለያዩ ተቋማት ያገኛቸው ማስረጃዎች በርካታ ሲሆኑ የተወሰኑት እነዚህ ናቸው

publicrelation