የአርሶ አደሩን የአመጋገብ ስርዓት ማሻሻል እንደሚገባ ተነገረ

የአርሶ አደሩን የአመጋገብ ስርዓት ማሻሻል እንደሚገባ ተነገረ

አማራ ክልል ከሀገሪቱ አጠቃላይ የሰብል ምርት 35% የሚሸፍን ድርሻ ቢኖረውም የአርሶ አደሩ የአመጋገብ ስርዓት አሁንም ቢሆን የሚፈለገውን ያህል መሻሻል እንዳላሳየ በስርዓተ-ምግብ (nutrition) አተገባበር ዙሪያ በደብረ ታቦር ከተማ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡ በgiz እና በአጋር አካላት ቅንጅት በተመረጡ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እየተተገበረ ያለው የስርዓተ-ምግብ ተግባራት (activities) የ2011 ዓ.ም የ6 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ቦሰና ተገኘ እንዳሉት የስርዓተ ምግብ ተግባራት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ስራ ሊሆን እንደሚገባ በመግለጽ ግብርና ቢሮ ባለው መዋቅር ተጠቅሞ የአርሶ አደሩን የአመጋገብ ስርዓት ለማሻሻል የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ገልጸዋል፡፡ የክልሉ giz - NSAP አስተባባሪ አቶ ሀብቴ ሆነልኝ በውይይት መድረኩ እንደገለጹት በኘሮጀክቱ የታቀፉ 6 ወረዳዎችና 29 ቀበሌዎች ያሉ ሲሆን በነዚህ አካባቢዎች ስርዓተ-ምግብን ለማሻሻል እድሜያቸው ከ15 እስከ 29 ድረስ ባሉ ሴቶች እና ህጻናት ላይ ትኩረት አድርጐ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት አስተባባሪው አክለውም የኘሮጀክቱ ዋና አላማ እርዳታ ላይ ያተኮረ ሳይሆን የህብረተሰቡን አስተሳሰብ በመለወጥ የአመጋገብ ዘዴውን ማሻሻል መሆኑን በመግለጽ አመራሩ፣ ስትሪንግ ኮሚቴውና ፎካል ፐርሰን ባለሙያዎች የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ሲሉ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የምክክር መድረኩ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡

publicrelation