የአማራ ክልል የ2011 ዓ.ም የመስኖ ልማት አጀማመር በአል የተዘጋጀ የመረጃ ህዳር 6 ቀን 2011 ዓ›ም

የአማራ ክልል የ2011 ዓ.ም የመስኖ ልማት አጀማመር በአል የተዘጋጀ የመረጃ ህዳር 6 ቀን 2011 ዓ›ም

የአማራ ክልል የመስኖ ልማት እንቅስቃሴ በርካታ አርሶ አደሮችን በልማቱ በማሳተፍ ተጠቃሚ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ባህላዊ መስኖ ልማት በክልሉ በመስኖ ከሚለማው የመሬት ሸፋን ውስጥ ከ 61.2 በመቶ በላይ ሸፋን ያለው ሲሆን የዘመናዊ መስኖ አውታር 10.6 ድርሻ በመቶ ሆኖ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች የሚለማው የመስኖ መሬት 28.2 በመቶ ይሸፍናል፡፡መንግስት ለመስኖ ልማቱ በሰጠው ትኩረት ባለፉት አስርታት አመታት ውስጥ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች 1,773 የሚሆኑ ዘመናዊ የመስኖ አውታሮች፣ 124 ግድቦች ሲገነቡ 416 ጥልቅ የመስኖ ጉድጎዶች ተቆፍረው አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ ባለፉት አስራ ሦስት ዓመታት በተደረገው ሰፊ የመስኖ ውሀ የማቅረብ እንቅስቃሴ የሚለማው መሬት በ1997 ዓ.ም ከነበረበት 232,650 ሄ/ር ወደ 893,400 ሄ/ር ወይም በሶስት ዕጥፍ ዕድገት ማሳዬት ችሎል፡፡ በዚህም 2.25 ሚሊዮን የአርሶ አደር ቤተሰቦች ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የመስኖ ውሀ አቅርቦት ላይ የደረስን ሲሆን ይህን ከፍተኛ የመስኖ ሽፋን ለማምጣት፡- • 1,099 ዘመናዊ የወንዝ ጠለፋ ስራዎች ተከናዉነዋል፤ • 674 ዘመናዊ የምንጭ ማጎልበት ስራዎች ተሰርተዋል፤ • 123 አነስተኛ ግድቦችና 1 መካከለኛ ግድብ ተገንብቶል፤ • 416 የመስኖ ጥልቅ ውሀ ጉድጎዶች ተቆፍረዋል፤ • 458,800 የእጅ ጉድጓዶች በመቆፈር ለመስኖ አገልግሎት ዉለዋል፤ • 35,119 የዉሃ መሳቢያ ሞተሮች በመንግስት ተሰራጭተዉና በአርሶ አደሩ ተገዝተው ለመስኖ አገልግሎት ዉለዋል፤ • 62,874 የጂኦሜንብሬን ገንዳዎች ጥቅም ላይ ዉለዋል፡፡ ከላይ ከምናየው ዋና ዋና የመስኖ መሰረተ ልማት ክንውን አንጻር እድገቱ ፈጣን ሆኖ ቢታይም ክልሉ ካለው የውሃ ሃብት፣ የመሬት ስፋት እና አምራች ሃይል እንዲሁም በአየር ንብረት መለዋወጥ ሳቢያ ከሚከሰተው ድርቅ አንፃር የመስኖ ልማቱ በአስተማማኝ መሰረት ላይ ለማቆም ገና ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ መመልከት ይቻላል፡፡
በመስኖመሰረተልማቱያሉምቹሁኔታዎች
መጠነ ሰፊ የከርሰ ምድር፤ ገፀ ምድርና የዝናብ ውሃ ሃብት መኖሩ ፣  በክልሉ ሰፊ የሚታረስና በመስኖ የሚለማ መሬት መኖሩ፣  ክልሉ መስኖ ሊያለማ የሚችል ሰፊ የሰው ሃይል ያለው በመሆኑ፣  ውሃን ማዕከል ባደረጉ የልማት ተግባራት የመንግስት ቁርጠኛ አቋም መኖር፣  በመስኖ ልማት የአርሶ አደሩ ተሣትፎዉና ግንዛቤው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ መምጣቱ፣  በርካታ የመስኖ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሃብት በማፍራት ኑሮአቸዉን ማሻሻል መቻላቸዉና ተሸላሚ መሆናቸው የብዙ አርሶ አደሮችን ስሜት በመቀስቀስ ወደ ልማቱ እየሳበ መምጣቱ፣  በርካታ በአነስተኛ የመሰኖ መሰረተ ልማት ማስፋፋት ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች መኖራቸው ይገኝበታል፡፡
በ2010 ዓ.ም. እቅድ አፈጻፀም የነበሩ ዋና ዋና ጥንካሬዎች • ለሁሉም የግብርና ልማት ተግባራት መፈፀም ዋናውና ቁልፉ መሳሪያ የማስፈፀም አቅም ግንባታ በመሆኑ በ2010 ዓ.ም ለወረዳና ለዞን ባለሙያዎች ክፍተትን በለዬ መልኩ ለነባርና ጀማሪ ባለሙያዎችን መሰረታዊ ክህሎት ላይ ያተኮረ (በግንባታ ነክ ስራዎች ላይ) የተሻለ ስልጠና መሰጠቱ፣ • ባለፈው ሦስት አመት በተከሰተው የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍ በርካታ የአመካከት ለውጥ ማምጣት የሚችሉ በአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ዙሪያ የተገኙ ተሞክሮዎች ለ2010 ዓ.ም የመስኖ አውታር ግንባታ ስራ ከቦታ መረጣ ጀምሮ አስከ ጥናትና ዲዛይን ስራ ውጤታማ እንዲሆን መሰራት መቻሉ፤
በዘርፉ የተስተዋሉ ዋና ዋና እጥረቶች 1. በአዲስ ግንባታዎች • የተሟላ ዲዛይን በወቅቱ ሰርቶ አለማጠናቀቅ፡፡ በዲዛይን ሙሉነት ግምገማ ጊዜም የተሰጡ አስተያየቶችንና የማሻሻያ ሀሳቦችን አካቶ ጥናቱን ሙሉ የማድረግ በወቅቱ ለሚመለከተው አካል አስተካክሎ በማቅረብ በኩል ክፍተቶች መኖራቸው፣ • የጥናቱን ሰነድ ጨረታ እንዲወጣለት በወቅቱ ለፋይናንስ አለመላክ፡፡ ከተላከም በኋላ ተከታትሎ ከማስጨረስ ይልቅ ከጨረታ እስከ ቅድመ ክፍያ ድረስ ያለዉን ስራ የአጋር አካላት ድርሻ ብቻ አድርጎ በመቁጠር ስራ ማጓተት፣ • አመራሩ የግንባታውን ስራ አፈፃፀሙን በየወቅቱ አለመገምገምና ለሚከሰቱ አስተዳደራዊ ችግሮች ወቅታዊ ምላሽ አለመስጠት፣ • የዞንና የወረዳ ባለሙያዎች ክትትል ማነስ፣ • የኢንተርፕራይዞች የስራ አፈፃፀም እንደተፈለገው አለመሆንና ከፍተኛ ትርፍ ከመፈለግ ጋር ተያያዞ ችግር መኖሩ፡፡ በ2011 ዓ.ም የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የመስኖ ልማት ዕቅድ ዋና ዋና ተግባራት በጠቅላላ የሚለማ መሬት 945,588 ሔክታር ነባር መስኖ 837,693 አዲስ መስኖ 107,895 ሔክታር የሚጠበቅ ምርት 144,329,276 ኩንታል - ተሳታፊ አርሶ አደር 2,252,426 የኮሞዲቲ እቅድና አሰራርን በተመለከተ የአትክልት ኮሚዲቲ ልማት እቅድ 4 ሰብሎች በኮሞዲቲ ለማልማት እቅድ ተይዟል፤እነሱም ሀ. ቀይ ሽንኩርት ለ. ነጭ ሽንኩርት ሐ. ቲማቲም መ. ድንች ሲሆኑ በእነዚህ ሰብሎች ፡- 228,560 ሔ/ር ይለማል ፡- የሚጠበቅ ምርት 45,474,896 ኩ/ል ፡- ምርታማነት 198 ኩ/ል በሔክታር ፣- ተጠቃሚ አርሶ አደር 255,446 በፍራፍሬ ኮሚዲቲ ልማት ክላስተር የሚለሙት ሀ. ማንጐ ለ. አቡካዶ ሐ. ሙዝ መ. ቡና አፕልና ብርቱካን ናቸው፡• 14 ሚሊዩን ችግኝ በቁጥር ለማልማት እቅድ ተይዟል 14,806 ሔ/ር መሬት ይለማል 121,568 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ፡ በመቀጠል የሚሰሩ ተግባራት • የሙዝ ማብሰያ ቴክኖሎጅ በጎንደር ከተማ ግንባታ እንዲካሔድ ማድረግ፡፡ • የቆቦና የቆጋ መቀዝቃዥ መጋዝን ወደ ስራ ማስገባት • የደሴ ቲሹ ካልቸር ወደ ስራ ማስገባት እና ሙዝ እና ድንች ላይ ስራ ማስጀመር፡፡ • የቢኮሎ አትክልትና ፍራፍሬ ማቋቋሚያ ማጸደቅና ወደ ስራ ማስገባት፡፡ * የምንከተላቸው አሰራሮች • በጫት የተሸፈነው ምርት ቀስ በቀስ ወደ ፍራፍሬ መቀየር፡፡ • ድጋፍ እና ክትትላችን ጠንካራና ተደራሽ ማድረግ፡፡ • በግብርና ቢሮ ያሉ አትክልትና ፍራፍሬ ድጋፍ የሚያደረጉ ኘሮጀክቶች ጋር ተባብሮ መስራት፡፡ • ከ500 ሄክታር በላይ የሚያለሙ 17 የመስኖ አውታሮች ላይ ርብርብ ማድረግ፡፡ • የተጀመረውን የውጭ Export ምርት ማለት አቡካዶና የቡና ልማት በስፋት ማጠናከር፡፡ • የገበያ ችግር ያለባቸው ሰብሎች የገብያ ትስስር መፍጠር * እነዚህ ተግባሮችን ለመፈጸም • የአመራሩና የባለሙያ ክትትልና ድጋፍ ጥብቅ መሆን • አርሶ አደሩ በወሰደው ስልጠናና የባለሙያ ምክር በመቀበል ቢያንስ በአመት ሁለት ጊዜ እንዲያመርት ማድረግ ናቸው ፡፡ የመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ዳይሬክቶሬት
ደንበጫ ፤ ምእራብ ጎጃም

publicrelation