የተፈጥሮ ሃብት ልማትባ ጥበቃ አጠቃቀም ዳይሮክትሬት

በ2009 ዓ.ም የታቀዱ የተፈጥሮ ሀብት ልማት፤ ጥበቃ እና አጠቃቀም እቅዶችን ከምንጊዜዉም በላይ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ ለመተግበር በየደረጃዉ የሚገኙ ፈጻሚ አካላትን በአመለካከት በክህሎት እና እዉቀት ለማብቃት ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል:: በተከታታይ ዓመታት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር እና በማስፋት እጥረቶች ደግመዉ እንዳይከሰቱ ለማድረግ ግብ ተቀምጧል፡፡ ባለፉት ዓመታት በደን ልማት የታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የደን ልማት ስራን በተሻለ መንገድ አቅጣጫ ተተልሟል፡፡

የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት አዳዲስ አሰራር እና ቴክኖሎጅዎችን አቀናጅቶ ለመተግበር ፈፃሚ አካላትን በአመለካትና በክህሎት ማብቃት ቁልፍ ተግባር ተደርጎ ተከናዉኗል፡፡ከክልል እስከ ቀበሌ ያለው አመራርና ባለሙያ በ2009 በጀት ዓመትበተቀናጀ የተፋሰስ ልማት አፈጻጸም ተፈጥሮ ሀብትን በዘላቂነት ከመጠበቅ ባሻገር የህብረተሰቡን በአጭር እና በረጀም ጊዜ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ሰፊ ውይይት አድርጎ የጋራ ድምዳሜ እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ከህብረተሰቡ ጋር ከልብ በመነጨ ሁኔታ ለመግባባት እስከ መንደር የደረሰ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የፊዚካል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ አፈፃፀም ስንመለከትበ2009 የክልላችን የተቀናጀ ተፋሰስ ልማትና ጥበቃ ስራ ለተከታታይ አመታት በተገነባው የልማት ሰራዊት ከተገኘዉ ልምድ፣ እዉቀትና ክህሎትን በተሻለና ባደገ ሁኔታ ለመተግበር ግብ ተቀምጦ ተከናውኗል፡፡

የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ቀጣይት ወዳለው ደረጃ ማሸጋገር፣ የተፋሰስ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ጠንካራ የተፋሰስ ተቋማትን በተከታታይ መገንባት፣ በእንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት መካከል ተደጋጋፊ ስልተምርት መከተል፣ በተመጣጣኝ ጉልበት ተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ተጠቃሽ የተወሰዱ ልምዶች ናቸው፡፡ በተለይ ልቅ ግጦሽ በተፈጥሮ ሀብቱም ሆነ በእንስሳቱ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተጽእኖ በመገንዘብ ከነውስነነቱም ቢሆን አበረታች ውጤትተመዝግቧል፡፡

በተደረገው እርብርብ በ146 ወረዳዎች፣በ3,178 ቀበሌዎች እና በ6,515 ተፋሰስ የማልማት ስራው ተከናወኗል፡፡ በስራው ወንድ 2,665,798 ሴት 1,945,584 በድምሩ 4,611,382 የሚሰራ የሰው ሃይል 109,163 ልማት ቡድን 525,006 በ1ለ5 በማደራጀት የንቅናቄ ስራ ሲከናወን ቆይቷል፡፡

የህብረተሰብ ተሳትፎና አደረጃጀት በተመለከተ የተደራጀው የልማት ሰራዊት በተፈጥሮ ሃብት ስራበተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ከተደራጀው 4,611,382 ህዝብ በተከታታይ ቀናት የተሳተፈው በአማካኝ 3,693,256 ወይም 80.09% ነው፡፡ በአመቱ  በድግግሞሽ ወንድ 51 ሚሊዮን፣ ሴት 34 ሚሊዮን በድምሩ 85 ሚሊዮን ሰው ቀን በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ተሳትፏል፡፡ ይህ ተሳትፎ በገንዘብ ሲተመን 3.08 ቢሊዮን ብር ይሆናል፡፡

 

ይህ ሰፊ ጉልበት የላቀ አፈጻጸም እንዲኖረው በአደረጃት እንዲሰራ፣ እንዲገመግም በማድረግ በኩል በጥብቅ ክትትል እንዲመራ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በአደረጃጀቶች መካከል የውድድር መንፈስ ለመፍጠር ተከታታይ የደረጃ ምዘና ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በዚህም መሰረት በአመቱ በወረዳ፣ በቀበሌና በልማት ቡድን የተሳትፎ አፈጻጸሙ ከ 84 እስከ 85 በመቶ ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ ይህም ህብረተሰቡ ለተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ፣ እንክብካቤ እና ተጠቃሚነት የሰጠው ትኩረት ውጤት ነው፡፡

ዋና ዋና የፊዚካል ስራዎች አፈጻጸም በተመለከተ በአመቱ በተለያዩ የመሬት አጠቃቀሞች ላይ ብዙ ጉልበት የሚጠይቁና በሽፋን የሚለኩ ዋና ዋና የፊዚካል ስራዎች 334,785 ሄ/ር ለመስራት ታቅዶየተፈጸመው 325,076 ሄ/ር ወይም 97% ነው፡፡

በማሳ ላይ የተሰራ የፊዚካል የአፈርና ውሃ ጥበቃስራ247,509 ሄ/ር መሬት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ለመስራት ታቅዶ የተከናወነ 260,024 ሄ/ር ወይም 105% ነው፡፡ እንዲሁም የቦረቦር ማዳን ስራ እቅድ 9,497 ሄ/ር ሲሆን ክንውን 10,900 ሄ/ር (115%) ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀጣይ በክረምቱ በዋናነት የሚፈጸም ሆኖ በ 60,032 ሄ/ር የእርሻ መሬት የሳር ሰርጥ ስራ ለመስራት ታቅዶ እስከ አሁን የተከናወነ 29,281 ሄ/ር ወይም 49% ነው፡፡

 

የተራራ ልማት ስረዎችን በተመለከተ 346,744 ሄ/ር ተራራማ መሬት ለመከለልና ለመጠበቅ ታቅዶ የተከናወነ 175,497 (50.61%) ሄ/ር ፤ በ7,000 ሄ/ር መሬት የጠረጴዛማ እርከን ለመስራት ታቅዶ የተከናወነ 2,152 ሄ/ር ወይም 30%፤ የጋራ ላይ እርከን ከትሬንች ጋር 70,799 ለማከናወን ታቅዶ 52,999 (75%) ተከናውኗል፡፡በተዳፋታማ መሬት የውኃ ስርገትን በመጨመር የአፈር ክለትን ለመከላከል፣ የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውኃ ለማበልጸግ የሚያግዙ የውኃ ማስረጊያ አነስተኛ ጉድጓዶች 11.25 ሚሊዮን ለማስራት ታቅዶ የተከናወነው 9.11 ሚሊየን (81%) ነው፡፡

የስነ-ህይወታዊ አፈር ጥበቃ ስራዎችከበጋው የህዝብ ንቅናቄ ወቅት የስነ-ህይወታዊ የአፈር ጥበቃ ስራዎች ተቀናጅተው ተተግብረዋል፡፡ በተለይ ሰሜን ወሎ እና ደቡብ ወሎ የጎላ ድርሻ ነበራቸው፡፡ በአጠቃላይ እርከን ላይ በእጽዋት ማጠናከር 10,559 ሄ/ር መሬት ላይ እና በቦረቦር 26.9 ሄ/ር መሬት ላይ  በድምሩ 10,585.9 ሄ/ር በመተከል ተከናውኗል፡፡

የክረምት ወራት የእርጥበት እቀባ እስትራክቸር በተጠናከረ መንገድ ለመስራት በመታሰቡ በክልል ደረጃ የመነሻ እቅድ በማዘጋጀት በምስራቅ አማራ ለአመራሩና ለባለሙያው በወቅታዊ የተፈጥሮ ሃብት ተግባራት ላይ ኦሬቴሽን በመስጠት ወደ ስራ ተግበቶል፡፡በመሆኑም በክልል ደረጃ የተዘጋጀውን የመነሻ እቅድ መሰረት በማድረግ ዞኖች ተመሳሳይ መድረክ ከወረዳዎች ጋር በመፍጠርና የጋራ መግባበት በመድረስ  የክልሉን እቅድ መነሻ በማድረግ የአካባቢውን ፖቴንሻያል መሰረት ያደረገ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ እንዲገባ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ስራ ለመግባት ተቸሎል፡፡

 

የደን ልማት እና አግሮፎረስትሪ ልማት ስራዎች መካከል የተከላ ቦታ ልየታአንዱ ሲሆን የክልሉን የደን ልማት ሽፍን  ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት የተለያዩ እቅዶች ታቅደዉ እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡በዚህ የተከላ ዓመትም በመጀመርያ የተከላ ቦታ መለየት በቅድሚያ የሚስራ ሲሆን በአመቱ ለመለየት ከተያዘው 325,266 ሄ/ር መሬት ውስጥ እስካሁን ባለው ጊዜ ማከናወን የተቻለው 261,064 (80.26%) ሄ/ርነው፡፡

 

የችግኝማፍላትእንቅስቃሴበአመቱ 2.318240 ቢ/ንቁጥርለማፍላትታቅዶእስካሁንየተፈላችግኝ2.12503 ቢ/ን (91.6%) ነው፡፡ ሁለገብ ጠቀሜታ ባላቸው የሳርና የመኖ ችግኞች እስካሁን ባለው 0.6157 ቢ/ን (76.74%) ያህል ድርሻ ሲኖረው ቀሪው 1.5093 ቢ/ን (99.5%) የደን ችግኝ የተፈላነው፡፡

 

የችግኝጉድጓድዝግጅትየችግኝመጽደቅንሊያሻሽሉከሚችሉትስራዎችአንዱችግኝከመተከሉበፊትደረጃዉንየጠበቀየችግኝጉድጎድአስቀድሞ መቆፈርእናማዘጋጀትአስፈላጊመሆኑይታወቃል፡፡በያዝነዉየተከላዘመንም1.806ቢ/ቁየችግኝጉድጎድለመቆፍርእቅድተይዞእሰከአሁንያለዉአፈጻጸም 0.9285ቢ/ቁነዉ፡፡ስለዚህበቀሪጊዚያትለችግኝጉድጓድዝግጅትትኩረትበመስጠትመስራትይጠይቃል፡፡

Undefined