የሰቆጣ የቃል ኪዳን ስምምነት ማለት ምን ማለት ነው?

የሰቆጣ የቃል ኪዳን ስምምነት ማለት ምን ማለት ነው?

የሰቆጣ የቃል ኪዳን ስምምነት ፕሮግራም ማለት ለሰቆጣና ሰቆጣ አካባቢ ብቻ የሚሰራ ፕሮግራም ማለት አይደለም :: በሁሉም በኢትዬጵያ ክፍሎች የህፃናት መቀንጨርና መቀጨጭ በንጥረ ነገር የበለፀገ ምግብ ህፃናት ሳያገኙ ሲቀሩ በህፃናት የወደፊት ህይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደገኛ መዘዝ አስመልክቶ በሀገራችን በሁሉም ክልሎች በፕሮግራሙ በተካተቱ አካባቢዎችና እና ጉዳዩ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በቅንጅትና በጋራ በመተባበር የሚሰራ ፕሮግራም ሲሆን ከተካተቱት ተቋማት መካከል ግብርና ፣ጤና ፣ትምህርት ውኃና ሌሎችም የተካተቱበት የጋራ ስራ ሲሆን ፕሮግራሙም የመንግስት ቁርጠኛነት የገባበትና ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ፕሮግራም ነው፡፡ የሰቆጣ ዲክላሬሽን ለህፃነት የተመጣጠነ ምግብ መስጠትና በተለይም ህፃናት እስከ ሁለት ዓመት ድረስ የእናት ጡት ወተት እንደሚያስፈልጓቸው እና ከዚያም በኋላ ደግሞ በንጥረ ነገር የበለፀጉ ምግቦችን መመዝገብ አስፈላጊነቱን አጥብቆ ይመከራል፡፡ታዲያ ለዚህ በንጥረ ነገር የበለፀገ ምግብ ለህፃናትና ለእናቶች በተገቢው ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ ከግብርናው ልማት ዘርፍ ምን ይጠበቃል? ብለን ስንመለከት የሀገራችን ግብርና በእርግጥ ገበያ መርን መሰረት ያደረገ ፕሮግራም ይዞ እየሰራ ያለ ቢሆንም አርሶ አደሩ ‹‹ የሚባለውን የሚገዛ የሚያመርተውን የሚሸጥ ›› መሆን አለበት ስንል አርሶ አደሮች ለገበያ ተፈላጊ ምርቶችን አምርተው ለሂወታቸውና ለጤናቸው አስፈላጊ የሆኑ ምግቦችን እየገዙ መመገብ አለባቸው፡፡ አርሶ አደሮች በአሁኑ ስዓት ከገበያ ስኳር፣ ዘይት ወ.ዘ.ተ የፍጆታ ሸቀጦችን ይገዛሉ ፡፡ ይጠቀማሉ ፡፡ ግን ተመጣጣኝ ምግብ ይዘት ያላቸውን የምግብ አይነቶች እንደ አትክልትና ፍራፍሬ ፣ ወተት ፣ስጋና በንጥረ ነገር የበለፀጉ እንዲሁም የአገዳና የብዕር ሰብሎችን በአይነታቸው እየገዙ እየተጠቀሙ ነው ለማለት አይቻልም ፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ አርሶ አደሮቹ የግንዛቤ እጥረት ስላለባቸው እንጅ የሚጠቅማቸው መሆኑን በግብርና ኤክስቴንሽን ፣በጤና ኤክስቴንሽን ፣በህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ስራችን ግንዛቤ ፈጥረንላቸው ቢሆን ኑሮ ልክ እንደ ዘይትና ስኳር ገበያ ላይ ገዝተው መጠቀም ይችሉ ነበር ፡፡ ሌላው አነጋጋሪ ነገር ሊሆን የሚችለው ደግሞ አርሶ አደሮቹ የተመጣጠነ እና በንጥረ ነገር የበለፀገ ምግብ ህፃናቶቻቸውን ለመመገብ የግብርና ምርቶች በአይነት በሁሉም አካባቢዎች እንዴት ሊገኝ ይችላል ? የሚለው ሲሆን ይህ ችግር ግብርናው ከዚህ የበለጠ እዬዘመነ ካልሄደ በእርግጥ በአንዳንድ አካባቢዎች ችግሩ ሊኖር ይችላል ፡፡ ሆኖም ግን ወደፊት የግብርናው ዘርፍ የበለጠ ጠንክሮ መስራትና የመልማቱ ጉዳይ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ግብርናው በተለይም የአማራ ክልል ግብርና ክልሉ የሚያመረተው የሰብል ምርት ለሀገራችን ኢትዬጵያ ጭምር 33% የምግብ ሰብል ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚያቀርብ ሰፊ እና ትልቅ አቅም ያለው ክልል በመሆኑ በአሁኑ ስዓት በሁሉም አካባቢዎች ለማለት ይቻላል አትክልትና ፍራፍሬ ፣ ሙዝ ፣ ፓፓያ ፣ ጥቅል ጎመን ፣ ብርቱካን ወ.ዘ.ተ በገቢያ ላይ ክረምት ከበጋ ይገኛሉ ፡፡ ሆኖም ግን አርሶ አደሮች በተለይም ትርፍ አምራች አካባቢዎች ለህፃናት ወይም ለቤታቸው ፍጆታ የሚሆን ጠቃሚ አትክልትና ፍራፍሬ ገዝቶ ከመሄድ ለመዝናኛና መሰል ወጭዎች ቅድሚያ ቦታ እየሰጡ ይታያል ፡፡ ስለሆነም የሚመለከተን ሁሉ የአርሶ አደሮችን ግንዛቤ በማሳደግ የህፃናት መቀጨጭና መቀንጨር በህፃናት የወደፊት እድገትና ስኬት የሚያመጣውን አደጋ በመገንዘብ ስርተ ምግብ ተኮር መረጃን መሰረት ያደረገ ስራ መስራት ይገባል፡፡ ከአብክመ ግብርና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

publicrelation