ዜና ቢራ ገብስ ልማት

ዜና ቢራ ገብስ ልማት

ከታህሳስ 8 እስከ 9/2009 ዓም በደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ ላይ በተካሄደው የቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የሰብል ልማት ባለሙያዎች የማትጊያ እና ስለወደፊቱ የግብይት ስርዓት አስመልክቶ  ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በቢሮው የቢራ ገብስ ልማት እና ግብይት ማስተባበሪያ ዩኒት አስተባባሪ አቶ አብዮት በላይ በሰጡት አስተያየት ቢሮው  ከዳሸን ቢራ ፋብሪካ ጋር  በመቀናጀት በሰሜን ጎንደር ዞን ለሚገኙ ወገራ ፤ ዳባት እና ደባርቅ ወረዳ ባለሙያዎች እና የቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንደ ስራ አፈጻፀማቸው አይነት እና ደረጃ የማበረታቻ ማትጊያ እንደሚሰጣቸው ገልፀው አንድ ባለሙያ 25ሄክታር ቢራ ገብስ ቢያስለማ በወር 100 ብር ወይም ደግሞ 250ሄ/ር ቢያስለማ 1000ብር በወር ያገኛል ማለት ነው፡፡ ለተከታታይ 8 ወራት፡፡

በተያያዘ ዜናም ብቅል ፋብሪካዎች  ከባህር ማዶ ያስመጡት የነበረውን የቢራ ገብስ ጥሬ ዕቃ በዚሁ በክልላችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን  ለማዳን ጭምር የግብርና ቢሮው እየሰራ መሆኑን አቶ አብዮት በላይ አክለው ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ በአጠቃላይ 95 ሰዎች የተሳተፉበት ሲሆን ቢሮው "የኛ ገብስ ለኛ ቢራ" በሚል መሪ ቃል  በክልሉ በሚገኙ 34 ደጋማ ወረዳዎች እና 196 ቀበሌዎች የቢራ ገብስ ልማት እያለማ ነው ተብሏል፡፡

በመጨረሻም አቶ በሪሁን ጥሩ የጎንደር ብቅል ፋብሪካ የምርት አቅርቦት ስራ አስኪያጅ እንዳሉት... የክልሉ ግብርና ቢሮ ለቢራ ገብስ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ለሰብሉ  ተስማሚ የአየር ንብረት ያላቸው   ወረዳዎችን በመምረጥ  የአሰራር ማንዋል በማዘጋጅት በጉድኝት/ክላስተር የቢራ ገብስ ልማት እያካሄደ መሆኑ ለድርጅታችን ስራ መቃናት ትልቅ ቦታ የሚሠጠው ነው ብለዋል፡፡ለዋል፡፡

 

በአምሳሉ ጎባው

ታህሳስ 10/2009 ዓም

 

webAdmin