አነስተኛ የመስኖ ውሃ መሰረተ ልማት

ከላይ እንድተገለጸው ከመኸር እና በልግ በተጨማሪ በመስኖ በመጠቀም የሚገኘው ምርት መጠን ከፍተኛ ነው፡፡ ይህንን የማምረት ዘዴ ለማሳከት ደግሞ የመስኖ ውሃ ማሰባሰቡ ቀዳሚ ተግባር ስለሆነ ግብርና ቢሮ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ከአርሶ አደሩ ጋር በመቀናጀት የገጸ-ምድር እና የከርሰ-ምደር ውሃን በማሰባሰብ እየሰራ ነው፡፡ በክልላችን በርካታ ዎንዞች፣ምንጮች የእጅ ውሃ ጉድጓዶች እንዲሁም ኩሬዎች  ለመስኖ አርሻ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን በ2008 ዓ.ም እና በ2009 ዓ.ም የምርት ዘመን የተከናዎኑ ዋና ዋና አዲስ እና ነባር  የውሃ ማሰባሰብ ስራዎች በሚከተለው ሠንጠረዥ ቀርበዋል፡፡

የ2008 ዓ.ም የመስኖ ልማት ስራ እንቅስቃሴ ተሳታፊ አርሶ አደሮች

በአማራ ክልል በመስኖ ዘዴ የተሸፈነውን የመሬት መጠን እና የተገኘ ምርት መጠን ከላይ በዝርዝር አይተናል፡፡ ባጠቃላይ በመስኖ የአስተራረስ ዘዴ በ2008 ዓ.ም 2,418,826 አርሶ አደሮች በነባር እና በአዲስ የተሳተፉ ሲሆን የየዞኑ አፈጻጸም በሚቀጥለው ሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡

ግብርና የሀገራችን 85 በመቶ የሚሆነው የሀብት ምንጭ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኛው የአትዮጵያ ግብርና ዘዴ በተለመደው እና በባህላዊ የአመራረት ስልት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሲመረትበት የቆየ በመሆኑ ለበርካታ አመታት ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የድህነት ቀንበር ስር ቆይተናል፡፡ ይሁን እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ምርትን እና ምርታማንትን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ እና ፈጣን የሆነ እድገት ለማምጣት ተችሏል፡፡ ይህም በተለመደው እና በዓመት አንድ ጊዜ የተፈጥሮ ዝናብ ተጠብቆ በመኸር ወቅት ብቻ ይመረት የነበረው አሁን በመስኖ እና በበልግ የሚገኘው ምርት አስደሳች የሆነ ለውጥ  አሳይቷል፡፡ ግብርና ቢሮ የስብል ምርትን ለማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የሰብልን ምርት ለማሰደግ ከተለመደው የመኸር ወቅት ምርት በተጨማሪ በበልግ እና በመስኖ እየተመረተ ያለው ምርት መጠን ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም፡፡ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ2008/9 ዓ.ም በመኸር ወቅት የተመረተው ምርት 95 ሚሊዮን ሲሆን ይህም የሀገሪቱን 33 በመቶ ይሸፍናል፡፡

በመኸር ወቅት የታረሰ መሬት እና የተገኘ ምርት

በ2007/8 ዓ.ም በመኸር ወቅት የታረሰ መሬት እና የተገኘ ምርት መጠን

ከላይ እንደተገለጸው ሰፊውን ድርሻ የሚይዘው የግብርና ማምረቻ ወቅት መኸር ሲሆን እንደ ማእከላዊ ሰታቲስቲከስ ኤጀንሲ ሪፖርት በ2007/8 ዓ.ም በመኸር ወቅት የታረሰው መሬት 4,424,474.71 ሄ/ር ሲሆን የተገኘው የምርት መጠን ደግሞ 87,464,267.66 ኩንታል ነው፡፡  ይህም በክልላችን በ2006/7 ዓ.ም የነበረው የማሳ ስፋት እና ምርት መጠን ከ4,442,036.25 ሄ/ር ወደ 4,424,474.71 ሄ/ር  እና  87,637,545.27 ኩንታል ወደ 87,464,267.66 ኩንታል በቅደም ተከተል ዝቅ ያለ መሆኑን እናያለን ፡፡ ከዚህ ለማየት እንደሚቻለው በማሳ በ17,561.54 ሄ/ር እና በምርት ድግሞ በ 173,277.61 ኩንታል ቅናሽ እንዳለ ነው፡፡በ2008/9 ዓ.ም መኸር ወቅት ደግሞ 4,443,390.47  ሄ/ር መሬት ታርሶ 95,282,955.56 ኩ/ል ምርት ተገኝቷል፡፡ ከዚህም በ2007/8 ዓ.ም ከነበረው ምርት መጠን በ7,818,687.90 ኩ/ል ከፍ ብሏል፡፡

Undefined