በአማራ ክልል በምርት ዘመኑ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ይቀርባል ተባለ

በአማራ ክልል በምርት ዘመኑ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ይቀርባል ተባለ

በአማራ ክልል በ2011/12 የምርት ዘመን ለመኸር እርሻ የሚውል ስድስት ሚሊዮን ኩንታል ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እንደሚቀርብ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ ፡፡

በክልሉ የመኸር እርሻ የሚውል ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት በተመለከተ ቢሮው በምዕራብ አማራ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የካቲት 11ቀን 2011 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ምክክር አካሂዷል ፡፡ በመድረኩ ላይ የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት የሚመለከታቸ ከ400 በላይ የዞን ፣የወረዳ ፣የግብርና ተቋማት፤ህብረት ስራ ማህበራት፤ ዩኒዬኖች ፣የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ፣የብድርና ቁጠባ ተቋማት ወ.ዘ.ተ ባለሙያዎችና ሐላፊዎች ተሳትፈውበታል ፡፡

እንጅባራ የተካሄደውን የምክክር መድረክ የግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ተስፋሁን መንግስቴ በንግግር ከፍተውታል ፤ መድረኩንም መርተውታል ፡፡ አቶ ተስፋሁን በመክፈቻ ንግግራቸው የምክክር መድረኩን አስፈላጊነት አስመልክተው ‹‹ በ2011/12 ምርት ዘመን ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ የሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በአንድ አይነት አስተሳሰብ በመመራት የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭትን በተሳለጠ መንገድ መምራ ት ለማስቻል ነው›› ብለዋል ፡፡ ምክትል ቢሮ ሀላፊው በምርት ዘመኑ ከውጭ ግዥ ተፈፅሞበት መግባት የጀመረው አምስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ኩንታል እና ባለፈው አመት ከመጣው የተረፈው ሰባት መቶ ሺ ኩንታል ጋር በአጠቃላይ በአማራ ክልል ስድስት ሚሊዮን ኩንታል የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ እንደሚቀርብ ጠቅሰው ከውጭ ግዥ ከተፈፀመበት አምስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ኩንታል ውስጥ ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ ኩንታል በአሁኑ ጊዜ ወደክልሉ መጓጓዝ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ለመኸር ሰብል የሚውል ማዳበሪያ በየካቲት ወር ወደ ክልሉ መግባት መጀመሩ ባለፉት አመታት ማዳበሪያ በወቅቱ ባለመድረስ ይፈጠር የነበረውን ችግር መቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ም/ቢሮ ሀላፊው ‹‹በአሁኑ ወቅት ማዳበሪያ በእጃችን መግባቱ ‹ የአርሶ አደሩን ስጋት መቅረፍ የሚያስችል ነው፡፡›› ብለዋል ፡፡ በዚህ አመት በየካቲት ወር ማዳበሪያ መጓጓዝና ወደ ክልሉ መግባት መጀመሩ በመልካም አጋጣሚነት የጠቀሱት

publicrelation