በምርት ዘመኑ በአማራ ክልል ከፍተኛ መጠን ያለው ሰሊጥ እንደሚሰበሰብ ተገለፀ

በምርት ዘመኑ በአማራ ክልል ከፍተኛ መጠን ያለው ሰሊጥ እንደሚሰበሰብ ተገለፀ

በአማራ  ክልል  በሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎረሜሽን ዕቅድ ዘመን የሰሊጥ ምርትና፤ምርታማነትን እና ጥራት ለማሳደግ የቀረጸውን አቅጣጫ በመከተል፤ ቴክኖሎጂ በመጠቀም እና በዘመናዊ የግብርና አሰራር የተካሄደው ልማት በተያዘው  የ2009 /2010  የምርት  ዘመን  ከፍተኛ  መጠን  ያለው  ሰሊጥ ማምረት  ማስቻሉን    የክልሉ  ግብርና  ቢሮ  ገለጸ፡፡ 

   የክልሉ  ግብርና  ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ መልኬ ታደሰ  በተያዘው የምርት ዘመን ለሰሊጥ ልማት እና ዕድገት በምክኒያትነት ከሚጠቀሱት ውስጥ በተለይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን  ቀበሌ ድረስ በመውረድ ለአርሶአደሮች እና ለባለሀብቶች  የንድፍ  ሀሳብና   በተግባር    የተደገፈ  ስልጠና ከመሰጠቱ ባሻገር ያልተቆራረጠ ምክር ክትትል እና ድጋፍ መሰጠቱ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም በመመራት በርካታ አርሶአደሮች እና ባለሀብቶች ከዚህ በፊት የነበሩባቸውን ውስንነቶች በመሻገር ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ከመጠቀማቸው ባሻገር እንደሌላው ሰብል በኩታገጠም ማሳ ማልማታቸውን እና በቀረበላቸው የመስመር መዝሪያ ማሽን በመዝራታቸው የሰሊጥ ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ እንዳስቻለ አቶ መልኬ አብራርተዋል፡፡

ምክትል ሀላፊው አክለውም የክልሉ ግብርና ምርመር ተቁዋም ለአካባቢው ተስማሚ የሰሊጥ ዝርያ ከማዉጣቱ በተጨማሪ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎችን እና ዘመናዊ አሰራሮችን በሰርቶ ማሳያ ማሳ ደረጃ ሳይሆን  በአርሶአደሮች እና በግል ባለሀብቶች ሰፋፊ ማሳዎች ላይ  ጭምር ማካሄዱ ለክልሉ የሰሊጥ ምርት  እና  ምርታማነት ላበረከተው አስተዋጽኦ በቢሮው ስም ምሰጋናቸውን አቅርበዋል፡፡   

በምዕራብ  ጎንደር  ዞን   የመተማ  ወረዳ  ግብርና  ጽ/ቤት    ኃላፊ  አቶ እንዳለው አርቃቸው በበኩላቸው የመተማ ወረዳ ከስልሳ ሺ ሄክታር በላይ (60፣000) በሰሊጥ የሚሸፈን መሆኑን ጠቅሰው ይሁን እንጂ ምርታማነት የሚጨምሩ ቴክኖሎጂዎች ካለመጠቀም የተነሳ በወረዳው የሚገኘው ምርት አነስተኛ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ይህን አሰራር ለማሻሻል ከጥቂት አመታት ወዲህ የተጀመረው እንቅስቃሴ መጀመሩን የጠቀሱት የወረዳው ግብርና ጽ;ቤት ሐላፊ በተለይ በተያዘው የ2009/2010 ምርት ወረዳቸው  ከክልሉ   ግብርና  ቢሮ   ፣ከሰሊጥ  ልማት    አጋር  አካላትና   በተለይም  ከጎንደር  ምርምር  ተቋማት   ጋር  በመቀናጀት   የሰሊጥ   ምርታማነትን   ለማሳደግ  በልዩ  ትኩረት  መስራታቸውን በአሁኑ ወቅት በመሰብሰብ ላይ ያለው የሰሊጥ ሰብል ከቀደሙቱ አመታት የበለጠ ምርት የሚያሰገኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 በግብርና  ኢንቨስትመንት  ስራ   የተሰማራው  ወጣት  ማርዬ  ተፈራ  በሰሊጥ  ካለማው  ሀያ  ሁለት  ሄ/ር  መሬት  ውስጥ  አስሩን  ሄክታር   ማዳበሪያ  ተጠቅሞ    በመስመር   መዝራቱን እና አስራ ሁለቱን ሄክታር  ደግሞ   ካለማዳበረያ በብተና የተዘራ መሆኑን ተናግሩዋል ፡፡  እንደ ወጣቱ ማብራሪያ ማዳበሪያ   የተጨመረበትና    በመስመር   ከተዘራው   ሰሊጥ   የአንዷን  ተክል  ቁመና  ከእሱ  ቁመና    ጋር  እኩያ መሆኑን  እያሳየተያየ  በዚያ  ቁመናው ልክ  ፍሬ  የያዘ  በመሆኑ  ከፍተኛ  ምርት  እንደሚያገኝበት    እምነቱን  ገልፃል  ፡፡  በመስመር  መዝራት   ለአረም  ስራ  ምቹ  መሆኑንና   እንደልብ ተንቀሳቅሶ   ፍሬው   ሳይፈስና    ሳይባክን   ለማጨድ  ምቹ  መሆኑን   ገልጻል  ፡፡  ከሁለቱ  ማሳዎች   የሚገኘውን  ምርት  አስመልክቶም  በብተና  እና ካለማዳበሪያ  ካለማው  መሬት  በሄ/ር  ከሶስት  ኩ/ል የበለጠ   እንደማይጠብቅ   ጠቅሶ  በፓኬጁ  የተቀመጠውን  አሰራር  በማሟላት   ምርጥ  ዘርና  ፣ማዳበሪያ  ተጠቅሞ  በመስመር  ከተዘራው   የሰሊጥ ማሳው ግን አነሰ  ቢባል  በሄ/ር  ዘጠኝ  ኩንታል   ፣አለበዚያ   በሄ/ር  አስር  ኩንታል   እንደሚያመረት ወጣቱ ባለሀብት  በእርግጠኛነት   ተናግሯል  ፡፡

በኮኪት ቀበሌ በአጨዳ  ስራ   እየተጣደፉ  ባሉበት ወቅት   ያገኘናቸው  አርሶ  አደር  አበበ  ፀጋ  ሶስት  ሄ/ር  መሬታቸውን  በሙሉ  በፓኬጅ  ተጠቅመው  ሰሊጥ  ማልማታቸውን   ገልጸው  በተለይ  እያጨዱት ያሉት    ማሳ  መሬቱ  ምንም  ጥቅም   አይሰጥም  የሚባል  እንደነበረ  አስታውሰው  ነገር  ግን  ዘመናዊ  ቴክኖሎጅ   አሰራር   ተከትለው  በማልማታቸው   በሄ/ር   ሁለት  ኩ/ል አይመረትበትም   ተብሎ  ከተፈረጀው  መሬት  ላይ  እሳቸው  ግን  ቢያንስ  ሰባት  ኩ/ል  እንደሚያገኙበት    ገልፀዋል  ፡፡ በሙሉ ፓኬጅ የሚካሄድ የሰሊጥ ልማት ከፍተኛ ምርት ማስገኘቱ እንዳለ ሁኖ ረዣዥም መኆኑ በቁም ለማጨድ ምቹ ነው፤ለአጫጆችም ጉልበት ይቆጥባል በቀን የሚያጭዱትን መጠንም  በመጨመር ገቢያቸውን ያሳድጋል ፤በመሆኑም አኛንም እነሱንም ጠቅሞናል ብለዋል፡፡

  አርሶ  አደር  አበበ  ፀጋ አክለውም የእርሳቸውን  ተሞክሮ  በመመልከት  ሌላው  የአካባቢው    አርሶ  አደሮች  ምርታማነትን    የሚያሳድጉ    ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው  በማልማት   ከፍተኛ  ምርትና ገቢ  አግኝተው  ህይወትና ኑሮዋቸውን  እንዲለውጡ  መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል  ፡፡

 

 

webAdmin