በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ ዞናዊ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራ የማስጀመሪያ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ ዞናዊ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራ የማስጀመሪያ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ ዞናዊ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራ የማስጀመሪያ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ
የዘንድሮ ዓመት የተፈጥሮ ሀብትና ጥበቃ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች በደማቅ ስነ -ስርዓት በንቅናቄ ተጀምሯል ፡፡ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ መንግስት ሰራተኞች ፣ተማሪዎችና አርሶ አደሮች የተፋሰስ ልማት በሚሰራበት ቦታ ተገኝተው ስራውን በይፋ አስጀምረዋል ፡፡ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳም ታጋ ቀበሌ ጥር 17/2011 ዓ.ም ዞናዊ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ስራ ተጀምሯል ፡፡
በስፍራው ተገኝተን ያነጋገርናቸው አርሶ አደር ጎበዜ ብርሀን እንዳሉት አካባቢው እርጥበት አጥር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለከፋ ችግር ተጋልጠን የቆየን ሲሆን ባለፉት አመታት በሰራነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተራሮች ማገገም ፣ምንጮች መጎልበት ጀምረዋል እንዲሁም አካባቢውን ከእንስሳት ንክኪ በመጠበቃችን ከተፋሰስ ልማት ተጠቃሚ መሆን ጀምረናል ሲሉ ገልፀውልናል ፡፡ "እኔ እራሴ ተጠቃሚ መሆን ጀምሪያለሁ" ያሉት አርሶ አደሩ የቢራ ገብስ አምራች እንደመሆናቸው በሄ/ር ከዚህ ቀደም ከሚያገኙት 7 ኩንታል ወደ 15 ኩንታል ምርት እያገኙ እንደሆነ በመግለጽ ለዚህ ተጠቃሚነት ያበቃን የተፈጥሮ ሀብታችንን መጠበቅ በመቻላችን ነው ብለዋል ፡፡
ተፋሰስን በማልናትና በመጠበቅ ከዘርፉ የላቀ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጠን እየሰራን ነው ያሉት ደግሞ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አቤ አስፋው ተፋሰስ ልማት ያለ ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ትርጉም የለውም ያሉት ሀላፊው በወረዳው ወጣቶችን በማደራጀት በንብ ማነብ ፤ በአትክልትና ፍራፍሬ ፤ በከብት ማድለብ ተሰማርተው ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል ያሉ ሲሆን አርሶ አደሩም ጥቅሙን ማጣጣም ስለጀመረ በዚህ ዓመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አንዱዓለም ሙሉ እንዳሉት ደግሞ በዘንድሮ አመት የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ 302,000 ህብረተሰብ የሚሳተፍ ሲሆን ወደ 30,124 ሄ/ር መሬት ይለማል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል ፡፡መምሪያ ሀላፊው አክለውም በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች ባጋጠመ የፀጥታ ችግር የቅድመ ዝግጅት ስራ የተጓተተበት ወረዳዎች ያሉ ቢሆንም በዚህ አመት የህብረተሰቡን ቀልብ ወደ ልማት ለማዞር የተፋሰስ ልማት ከፍተኛ አስተዋጾኦ ስላለው ሙሉ አቅማችን ተጠቅመን ርብርብ እናደርጋለን ብለዋል ፡፡
በዞናዊ ንቅናቄ የማስጀመሪያ ስነ -ስርዓት ላይ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ የኮሚኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ጎባው እንደገለፁት ከድህነት መውጫ መንገድ የግብርና ልማት ዘርፉን በማዘመን በዚህም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ገቢና ኑሮ በማሻሻል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለ ሲሆን ይህንን ለማሳካት ግን የተፈጥሮ ሀብታችንን ስንጠብቅና ስንከባከብ ነው ብለዋል ፡፡ አቶ አምሳሉ አክለውም የሌሎች ወረዳዎችን ልምድና ተሞክሮ አንስተው ያጋሩ ሲሆን ዛሬ ላይ የታየው የተደራጀ የህዝብ ንቅናቄ ሳይቀዘቅዝ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
የግብርና ቢሮ ኮሚኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክቶሬት

publicrelation