ማዳበሪያ መጫንና ማውረድ የሰማኒያ ሚሊዮን ብር ስራ ይዞ መጥቷል

ማዳበሪያ መጫንና ማውረድ የሰማኒያ ሚሊዮን ብር ስራ ይዞ መጥቷል

በአማራ ክልል ለ2011/2012 ምርት ዘመን ለመኸር ሰብል ልማት ግልጋሎት የሚውለው ማዳበሪያ ለጫኝና አውራጆች ሰማኒያ ሚሊዮን ብር እንደሚያስገኝ ተገለጸ፡፡

የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ.ም የክልሉ ግብርና ቢሮ ከምዕራብ አማራ ዞን እና ወረዳ የግብርና ተቋማት፣ የህብረት ስራ ማህበራት፣ የቴክኒክና ሙያ መምሪያዎች፤ ዩኒየኖች፣ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወዘተ ከ400 በላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሀላፊና ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው የምክክር መድረክ በምርት ዘመኑ ከፍተኛ መጠን ያለው ማዳበሪያ መቅርቡ በዋነኛነት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከማስቻሉ ጎን ለጎን በተለያዩ አግባቦች በተለይ ለወጣቶች የስራ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል፡፡

የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ባለድርሻ አካላት ባሳተፈው በእንጅባራው የምክክር መድረክ በምርት ዘመኑ ግዥ ከተፈጸመበት ወደ ክልሉ እየገባ አምስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺ ኩንትል ማዳበሪያ በክልሉ በተለያዩ ዮኒየኖች እና በህብረት ስራ ማህበራት መጋዝን ከመኪና ላይ ለማውረድና እንደገና በመጫንና ማውረድ ሂደት ለጉልበት ሰራተኞች ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያስገኝ የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

የማዳበሪያ መጫንና ማውረድ ስራ ሀላፊነትና ተጠያቂነት አካትቶ ህግና ስርዓትን ተከትሎ ለማስኬድ የማደራጀት፣ የማዋዋልና የክትትል ስራው ለቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሃላፊነት ተሰጥቷል፡፡
የምክክር መድረኩ የመሩት የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋሁን መንግስቴ የጫኝና አውራጅ ስራ ማደራጀትና የመምራት ስራ ለቴክኒክና ሙያ መስጠቱ ጥሩ አጋዥ አግኝተናል፤ ማዳበሪያችንን ለአርሶ አደራችን በበቂ መጠን እና በተፈለገው ጊዜ ለማድረስ ዕድል ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡

publicrelation