Best Practices

በሲያደብር ዋዩ  ወረዳ በሲያ ደብር ቀበሌ የስንዴ ክላስተር

በስንዴ ሰብል  ምርጥ ተሞክሮ አሰራር

1.   መግቢያ

 መግቢያ፡-

በአማራ ክልል በመጀመሪያው አምስት ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ምርት ዘመን (2002/03 -2006/07) በክልሉ ከፍተኛ የሰብል ምርት ዕድገት ተመዝግቧል፡፡ ለዚህ የሰብል ምርት ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ ካላቸው ዋና ዋና ሰብሎች አንዱ የሰንዴ ሰብል ሲሆንድርሻም 13.6% ነዉ፡፡ ክልላችን በስንዴ ሰብል የተደረሰበት አማካኝ ምርታማነት 2008/09 ምርት ዘመን(CSA,) 23.8 ኩንታል በሄክታር ነው፡፡ አሁን ደግሞ ከዚህ በፊት የተገኘውን ምርታማነት በተሻለ ሁኔታ ለማሳደግ በክልላችን ከ2007/08 ምርት ዘመን ጀምሮ ኮሞዲቲን መሰረት ያደረገ የዋና ዋና ሰብሎች የአመራርት አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ተግባር ስራ ተገብቷል፡፡ በዚህም መሰረት የስንዴ ኮሞዲቲ የፓኬጅ አጠቃቀም መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡ የተዘጋጀውን የፓኬጅ ምክረ-ሃሳብና የራሣቸውን ዕውቀት በመጨመር ተግባራዊ አድርገው የተሻለ ምርታማነት ያስመዘገቡ አርሶ አደሮችን ተሞክሮ በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢዎች የማስፋት (Scalling up) ስራ በተጠናከረ መንገድ ለመፈፀም ታስቧል፡፡

በ2ዐ10/11 ምርት ዘመን መልካም ተሞክሮዎችን በይበልጥ በማስፋት ለምግብ ፍጆታና ለኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ አቅርቦት ለማምረት የምንረባረብበት ወቅት ይሆናል፡፡ በ2009/10 ምርት ዘመን የተገኘውን ምርጥ ተሞክሮ የተገኘበትን አግባብ፣ ቴክኖሎጂውን ለማስፋት መከናወን ያለባችው ስራዎችና ቴክኖሎጂውን ለማስፋት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተዘርዝረው ቀርበዋል፡፡ ስለሆነም በየደረጃው ያሉ የግብርና አካላት ይህንን ሰነድ የሚመለከተዉ አካል ካረጋገጠዉ በኋላ  እንደ አንድ የሰብል ልማት መመሪያ በመጠቀም ተሞክሮዎችን እንደአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ በማየት ማስፋትና መላው የክልሉ አርሶ አደሮች የሰብል ምርታቸውን እንዲያሳድጉ በማድረግ ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማሣካት አስፈላጊ ይሆናል።          

2. የምርጥ ተሞክሮው ቅመራው ዓላማ

ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ እና በተለያዩ ጊዜያት ወደ አርሶ አደሩ የተሰራጩ የቴክኖሎጂ ፓኬጆች በትግበራ ሂደት አርሶ አደሩ የራሱን ልምድና ተሞክሮ በማካተት ከምክረ ሃሳቡ በተሻለ ውጤት ያስመዘገበባቸው የስንዴ ሰብል  ልማት ቴክኖሎጂዎችን፣ አሠራሮችና  ተሞክሮዎችን በመለየት ወደ ሌሎች አ/አደሮችና አካባባዎች ለማሰፋት እንዲቻል አርሶ አደሩ እንዴት በተግባር እንደተገበራቸው ከመነሻ እስከ መድረሻ በሚያሳይ ሁኔታ በመቀመርና በሚመለከተዉ ክፍል የማረጋጋጫ(Validation) ሥራ ከተሰራ በኋላ  በፓኬጅ መልክ በማዘጋጀት እንደየአካባቢው ሁኔታ ሌሎች አርሶ አደሮች እንዲተገብሩት ለማድረግ ነዉ፡፡

3. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራው አሠራር ስልት

 • ቴክኖሎጅው በተሻለ ሁኔታ የተፈጸመበትን ወረዳ ዞኖች እንዲመርጡ ማድረግና ወረዳዎች ደግሞ ቀበሌውን እንዲመርጡ ማድረግ፣ የቀበሌ ባለሙያዎች ደግሞ የሚቀመርበትን አ/አደር እንዲመርጡ ተደርጓል
 • የልማት ጣቢያ ሙያተኞችን በማነጋገር ውጤቱ የተገኘበትን ዝርዝር ሂደት መረጃ ማሰባሰብ፣ በአካል ተገኝቶ መመልከት፤
 • በተመረጠው ቀበሌ በመገኘት አርሶ አደሩ ተግባሩን እንዴት እንደፈጸመው የቅመራ ስራውን መስራት፣ በአካል ተገኝቶ መመልከትና አ/አደሩን ቃለመጠየቅ ማድረግ፤
 • መስክ ላይ ያሉ ስራዎችን በፎቶግራፍ ማንሳት መስክ ላይ ያልተገኙትን ደግሞ ቀደም ብለው የተነሱትን መውሰድ፣
 • በተዘጋጀው መጠይቅ መሠረት የተሰበሰበውን መረጃ ልምዱን ለመቅሰም በሚያስችል መልኩ በጽሁፍ ማስፈር  ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

4.  የተገኘ ዉጤት

የአ/አደሩ ስም ተካ ለማ ሲሆን በ0.25 ሄ/ር ያገኘዉ የስንዴ ምርት 16 ኩ/ል  ሲሆን 64ኩ/ል በሄ/ር ማለት ነዉ፡፡ ከዚህ በተጫማሪ  በአካባዉ መስፈሪያ 12 ቁርበት ገለባ አግኝቷል

5. ዉጤቱ ተገኘበት አካባቢ

በሰ/ሸዋ ዞን በሲያደብርዋዩ ወረዳ  ሲያደብር  ቀበሌ በደጋ አግሮኢኮሎጅ ዉጤቱ የተገኘ ሲሆን ከፍታዉም ቀበሌዉ ጽ/ቤት አካባቢ 2631  ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ሲሆን   በዚህ ቀበሌ  የስንዴ  ሰብል በስፋት በመመረት ላይ ይገኛል፡፡ የተለያዩ ሰብሎችን በስፋት ለማምረት ተሳማሚ የሆነ ሰነ-ምህዳር ቢኖረዉም አካባቢዉ ጥቀር አፈር በመሆኑና ዉኃ ሰሊሚያቆር ዉኃዉን ከማሰዉ በሰብል ላይ ጉዳት ሳያስከትል ለማስወጣት ዝቅቆሽ የባህላዊ አሠራር ይጠቀማሉ፡፡

የአቶ ለማ ተካ የስንዴ ማሳ ከአካባቢዉ ከአለ አ/አደሮች የተሸለ ምርት የሰጠበት ምክንያት   

 • ሠዉ ሰራሽ ማዳበሪያ
 • ም/ዘር
 • በዝቆሽ ትርፍ ዉኃን  ከማሳ ማስወጣት
 • በወቅቱ ማረስና ማረም
 • ተስማሚ የዝና መጠንና ስርጭት መኖር

በአቶ ለማ ተካ ማሳ በተለያየ ጊዜ የገበሬ በዓል በፌደራል፣ በክልል፣ በዞን፣በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ተከሄዶ በርካታ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና አ/አደሮች ት/ወስደዉበታል፡፡

6. ዉጤቱ የተገኘበት አካባቢ አፈጻጸም

6.1 ማሳ ዝግጀት   

የአቶ ተካ ለማ  ማሳ አራት ጊዜ የታረሰ  ሲሆን የመጀመሪያ እርሻ ግንቦት 3፣ ሁለተኛ እርሻ ሰኔ 2፣ሦስተኛ እርሻ ሀምሌ 4 ፣ አራተኛ እርሻ  ሀምሌ 14 ከዘር ጋር ተከሄዷል፡፡  

      6.2. የማሳዉ ቅድመ ታሪክ    

በ2008//09ምርት ዘመን የአ/አደር ተካ ለማ   NPSB እና UREA ማዳበሪያ በመጠቀም ጤፍ ዘርቶት ነበር፡፡ ማሳዉ ላይ ፊዚካል አፈርና ዉኃ ጥበቃ ሥራ የማያስፈልገዉ ሲሆን ነገር ግን ዉኃ ሰለሚተኛበት በዝቅቆሽ ትረፉን ዉኃ እንዲወጣ ተድርጓል፡፡

       6.3 የዘር ወቅት፣ የአዘራር ሁኔታ፣ የተጠቀመዉ የዘር መጠንና የዘር አይነት

አ/አደር ለማ ተካ ሐምሌ 14/2009 ዓ.ም 37.5 ኪግ/ 150 ኪ/ግ ሄ/ር ደንዳአ የተባለ የሰንዴ ም/ር በብትና ከዘራ በኋላ ትርፉን ዉኃ ለማስወጣት ዝቆሽ ተጠቅሟል፡፡ የዝቆሽ መደብ አሠራር 80 ሲሜ ስት ያለዉ ሲሆን የቦዩ ጥልቀት 20 ሲ ሜትር ነዉ፡፡

      6.4 የማዳበሪያ አጠቃቀም

አ/አደሩ ከዚህ በፊት ማዳበሪያ የመጠቀም ልምድ የነበረዉ ሲሆን ለአካበባዉ በግብርና ምርምር ለስንዴ ሰብል 2.25 ነፒስና 2.75 ኩ/ል/ ዩሪያ በሄ/ር እንዲጠቀሙ  ምክረሀሳብ የወጣላት ሲሆን አ/አደር ለማ ተካ ግን  4ኩ/ል ነፐስና 4 ኩ/ል ዩሪያ በሄ/ር ሂሳብ ተጠቅሟል፡፡የማዳበሪያ አደረራረጉ 1ኩ/ል ነፒስና 50 ኪ.ግ ዩሪያ ለ0.25 ሄ/ር መሬት  በዘር ወቅት ተጠቅሟል፡፡ ከ20-22 ቀን ባለዉ አንደኛ አረም ካረመ በኋላ 50ኪ.ግ ዩረያ Side dress አድርጓል ፡፡  

        6.5. አረምና ኩትኳቶ

 አንደኛ አረም በተዘራ በ20-22 ባለዉ ቀን ሲካሄድ ሁለተኛ አረም ነሀሴ 7/2009 ፓላስ 45 ኦዲ  ፀረ-አረም 60 ሲሲ  በአንድ ኖዝል መርጫ ጫፍ ብቻ  አንድ ጊዜ ብቻ ረጭቷል ፡፡

       6.6 ተባይና በሽታ

በ2009/10 ምርት ዘመን  የአ/አደር ለማ ተካ ማሳ  ቢጫ ዋግ ተከስቶ Rexdo  የተባለ ፀረ-አረም 125 ሲሲ/0.25 ሄ/ር ላይ  ርጭት አካሄዷል  ፡፡

       6.7 ምርት ማሳባሰብ

 የአቶ ለማ ተካ የስዴ ሰብል   በእጅ በማጨድ ሲሆን ከተሰበሰበ በኋላ ተከምሯል፡፡ ከዚያም  በእህል መዉቂያ ትራክተር ተወቅቷል፡፡  የተወቃዉ ስንዴ ከገበያ የተረፈዉ በጆንያ ይከማቻል፡፡

7. የተገኘ ት/ት

  8. የቤተሰብ ጉልበት አጠቃቀም

  ለሥራ የደረሱ የቤተሰብ አባላት በሙሉ በዚህ  ከማሳ ዝግጅት እሰከ አረም ሥራ የተሳተፉ ሲሆን በሰብል ሰብሰባ ወቅት የጉልበት ሠራታኛ  በመቅጠር ተጠቅሟል ፡፡

  9. የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት

  ከእርሻ ጀምሮ ሰብሉ እኪወቃና ወደቤት እስኪገባ ድረስ በየደረጃዉ ያሉ የቀበሌ፣ የወረዳ  የዞን ባለሙያዎች ዕገዛ አድረገዋል፡፡ የተደረገዉ የድጋፍ አይነት ማዳበሪያ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሠረት እንዲጠቀሙ፣ በወቅቱ እንዲታረም፣ የተባይ አሳሳ እንዲካሄድ፣ በወቅቱ እንዲሰበሰብ ክትትልና ድጋፍ ይደረግ ነበር፡፡ በተጨማሪም በየደረጃው ላሉ ባለሙያዎችና ለአ/አደሩ በቂ የሆነ የአቅም ግንባታ ስልጠና፣የልምድ ልዉዉጥ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡  በተጨማሪም የገበሬ በዓል በየደረጃዉ ከፌደራል እሰከ ቀበሌ ድረስ ተካሄዷል ፡፡

  10. የትርፋማነት አዋጭነት ስሌት አሰራር

  ተ/ቁ

  ዝርዝር ተግባራት

  መለኪያ

  በሙሉ ፓኬጅ የተከናወኑ ተግባራት

  ለ0.25ሄ/ር የሚያስፈልግ

  የአንዱ ዋጋ

  ጠቅላላ ዋጋ

  1

  1ኛ እርሻ

  ሰው/በሬ/ቀን

  1

  250

  250

   

  2ኛ እርሻ

  ሰው/በሬ/ቀን

  1

  250

  250

   

  3ኛ እርሻ

  ሰው/በሬ/ቀን

  1

  250

  250

   

  ማዳበሪያ፣ ዘር መዝራትና ዝቆሽ መሥራት

  ሰው/ቀን

  3

  100

  300

   

  የዘር መጠን

  ኪ/ግ

  37.5

  12

  450

   

  ኤን.ፒ.ኤስ

  ኪ/ግ

  100

  11.82

  1182

   

  ዩሪያ

  ኪ/ግ

  100

  9.09

  909.0

   

  1ኛ ዙር አረም

  ሰ/ቀን

  3

  60

  180

   

  ፀረ.አረም

  ሊትር

  0.06

  2.060

  123.60

   

  ፀረ-ፈንገስ

  ሊተር

  0.125

  1056

  132

  16

  አጨዳና ሰብሰባ

  ሰው/ቀን

  7

  140

  980

  17

  ውቂያ

  ሰው/ቀን

  2

  100

  200

   

  የትራክተር ዉቂያ

  ኩ/ብር

  16

  80

  1280

  18

  የሰብል ምርታማነት

  ኩ/ሄር

  64

   

  የተገኘ ምርት

  ኩ/ል በ0.25

  16

  20

  ገቢ ከሰብል ሸያጭ 

  ብር

  16*1050= 16,800.00

  21

  ገቢ ከተረፈ ምርት

  ብር

  12*80= 960

  22

  ጠቅላላ ወጪ

  ብር

  6487.10

  23

  ጠቅላላ ገቢ

  ብር

  17760.00

  24

  የተጣራ ትርፍ

  ብር

  11272.00

  አዋጭነት

   

  2.7

   

  • አዋጭነት 2 እንዲሆን የተመረጠው አርሶአደሩ ላወጣው ወጪ ተመጣጣኝ ገንዘብ ካላገኘ ለቀጣይ አዝመራ ወቅት ሊጠቀምበት የሚችለው ሌላ ገንዘብ ምንጭ ስለማይኖረው የግድ ለእየአንዳንዱ ላወጣው ብር ሌላ ተጨማሪ አንድ ብር ማግኘት ስለአለበት ነው፡፡
  • በዚሁ መሰረት የሰንዴ የተሸሻለ አሠራር ሲዘራ አዋጭነቱ አርሶ አደሩ 1ብር ወጪ ሲያወጣ 2.70 ብር አድርጎ ይመልሳል ወይም 1ብር ባወጣ ቁጥር 1.70 ብር የተጣራ ትርፍ እንደሚያገኝ ያሳያል ማለት ነው፡፡
  •             11.   ቴክኖሎጂውን ለማስፋት መሰራት ያለባቸው ስራዎች፣
  • የተጠናከረ የባለሙያ ምክር አገልግሎት መስጠት
  • ለተጠቃሚ አ/አደሮችና በየደረጃዉ ለሚገኙ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት
  • ተከታታይነት ያለዉ የገበሬ በዓልና የልምድ ልዉዉጥ ማካሄድ
  • መረጃዎችን ተከታትሎና አደራጅቶ መያዝ
  • የቤተሰብን ጉልበት በአግባቡ መጠቀም
  • ለአካባቢ ተስማሚ የሆነውን እና ትክክለኛውን የዘር መረጣ፣ የዘር ወቅት፣ የዘር መጠንና የአዘራር ዘዴ መጠቀም (ስንዴን በመስመር መዝራት)
  • ለግብዓት አጠቃቀሙ ትኩረት በመስጠት ትክክለኛውን የግብአት አጠቃቀም ዘዴ በመከተል በትኩረት በምክረ ሀሳቡ መሰረት የማዳበሪያ አይነትና መጠን መጠቀም
  • በወቅቱ የሰብል ጥበቃ ስራ (አረም፣ተባይና በሽታን) ማከናወን የመሳሰሉትን ጥንቅሮች ማሟላት ያስፈልጋል፡፡                                                                                                                                                        12.  ቴክኖሎጂውን ለማስፋት የሚያስፈልጉ ግብአቶች፣
  • የተሸሻለ መዝሪያና መወቂያ መሣሪያ ቢቀርብ
  • የተሸሻለ ድህረ-ምርት አያያዝ ቴክኖሎጅ ቢቀርብ
  • የጥራቱን የጠበቀ ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ በወቅቱ ማቅረብ

   

  አዘጋጆች

  1. ወርቁ አዉዴ

  2. ጌታቸዉ ምስክር             

             ታህሳስ/2010