Duties and responsibilities

  የግብርና ቢሮ ዝርዝር  ስልጣንና ተግባር

  በሌሎች ሕጎች አስቀድሞ የተደነገገው ወይም ወደፊት የሚደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሉ ግብርና ቢሮ በዚህ አዋጅ መሰረት የሚከተሉት ዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል

  1. የአገሪቱን የግብርና መር ፓሊሲና ስትራቴጂ መሰረት ያደረጉ የክልሉን የአጭር፤ የመካከለኛና የረዥም ግዜ ስትራቴጃዊ ዕቅዶች ኘሮግራሞች ያዘጋጃል፤ ይፈጽማል፤ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የግብርና ልማት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
  2. ለአርሶ አደሩ የኤክስቴንሽን አገልግሎትና የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፤ ለምርምር አገልግሎት የመነሻ ሀሳብ ይሰጣል፤ ውጤታማነቱን ይከታተላል፤
  3. የሰብልና የእንሰሳት በሽታዎችን፤ ፀረ-ሰብል ተባዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የማቴርያልና የቴክኒክ እገዛ ይሰጣል፤
  4. የተገኙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ያቀርባል፤ ያላምዳል፤ ኘሮቶታፓችን ያመርታል ለሚያመርቱትም ያሰራጫል፤
  5. በግብርናዉ ዘርፍ መዋእለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚፈልጉ የድል ባለሀብቶች ተገቢውን መረጃና የምክር አገልግሎት ይሰጣል
  6. በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ መስክ፤ ለአርሶአደሩና በግብርናው ዘርፍ ለተሰማሩ የግል ባለሀብቶችን ስለአጠባበቅ፤ አያያዝና አጠቃቀሙ የትምህርት የስልጠናና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል፤የልማቱን የጥበቃዉንና አጠቃሙን ሁኔታ ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤
  7. አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ለአርሶ አደሩ የብድር አግልግሎት የሚቀርብበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
  8. የውሃ እቀባ ስራዎችን ያከናውናል እንዲያከናውነኑ ያደርጋል በመለስተኛ የመስኖ አውታሮች ላይ የጥገና የባህላዎዊ ወንዝ ጠለፋና የአነስተኛ መስኖ ልማት ስራዎችን ያካሂዳል እንዲስፋፋ ያበረታታል ድጋፍ ይሰጣል
  9. ወደ ክልሉ በሚገቡና ከክልሉ በሚወጡ እጽዋት አዝርእት እንሰሳትና የእንሰሳት ተዋጽኦ ላይ ተገቢውን የኳራንቲን ቁጥጥር ያደርል
  10. የግብራና ግብዓቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ለተጠቃሚዎች መሰራጨታቸውን ይከታተላል የቆጣተራል፤
  11. የግብርና ልማቱን ለማፋጠንና የገጠር ቴክኖሎጂዎችን ለማሻሻል የሚረዱ የማሰልጠኛተቋማትንና ማዕከላትን ያቋቁማል፤ይመራል፤
  12. በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የሰብል የእንሰሳትና የገጠር ቴክኖሎጂ ብዜት ማዕከላትን ያስፋፋል ያስተዳድራል አዳዲሶች እንዲቋቋሙ ያደርጋል፤
  13. አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በክልሉ ውስጥ የደንና የዱር እንሰሳት ጥበቃና አጠቃቀም ተግባራትን በበላይነት ይመራል፤
  14. በግብርና ልማቱ ላይ ተፅዕኖ የሚኖራቸውን ወቅታዊ ሁኔታዎች ይከታተላል የቅድሚያ ማስጠንቀቅያ ስርአት ይዘረጋል የምግብ ዋስትና ስራውን ይከታተላል፤ የቆጣጠራል፤
  15. የሰፈራ ኘሮግራሞችን በማስፈጸም ረገድ ወረዳዎችን ያስተባብራል፤ ድጋፍ ይሰጣል፡፡