የአማራ ክልል የአንስተኛ የመስኖ ተቋማት ግንባታና የመስኖ ልማት አሰራርን ማስፋት አስፈላጊ ነው ተባለ

የአማራ ክልል የአንስተኛ የመስኖ ተቋማት ግንባታና የመስኖ ልማት አሰራርን ማስፋት አስፈላጊ ነው ተባለ

ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች የሚከሰተውን ድርቅ በዘላቂነት ለመቅረፍ ቢሮው የሚያስገነባቸው አነስተኛ የመስኖ ተቋማትና ልማት የአስራር ተሞክሮው በሌሎችም ክልሎች ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር አሰታወቀ፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ያስገነባቸውና ወደ ልማት የገቡ አራት አንሰተኛ የመስኖ ተቋማትን በክብር እንግድነት ተገኝተው የመረቁት የእርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ሚኒስተሩ ዶ/ር እያሱ አብርሃ ተቋማቱን ተዘዋውርው ከጎበኙ በኋላ ከፌደራል፡ ክረጂ ድርጅቱ፤ ከሌሎች ክልሎችና ከአማራ ክልል ፣ ዞንና ወረዳ ወክለው ለተገኙ አመራርና ባለሙያዎች ባደረጉት ንግግር  ተፈጥሮ የምትለግሰውን ዝናብ በመጠበቅ ብቻ የሚካሂድ የግብርና ስራ የትም ሊያድረስን አይችልም፡፡ ቀደም ሲልም የዝናብ እጥረትና መስተጓገል የዘወትር በሆነባቸው አካባቢዎች በ2007/08 የደረሰው ችግር የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡፡ ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ያስገነባናቸው አንሰተኛ የመስኖ ተቋማት በክረምት ወራት የሚከስት የዝናብ እጥረትና መቆራረጥን በደጋፊ መስኖ ለማገዝ እና በበጋም ተጨማሪ ልማት በማካሄድ ችግሩን በዛላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ናቸው፡፡እንደ ሚኒስተሩ ዶ/ር ኢያሱ ማብራራያ፡፡

 የአነስተኛ የመስኖ ተቋማቱ ግንባታ አስራር የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ለሕብረተሰቡ ችግር ፈጣን ምላሽ መስጠት ያስቻለ ከመሆኑ ባሻገር አጠቃላይ የግንባታ ስራው ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ  ባለሙያዎች መስራቱ ሕብረተሰቡን የሰራው ባለቤት አድርጎ ማሳተፉ በአጭር ግዜ እና በአነስተኛ የገንዘብ ወጨ ስራው በጥራት ተጠናቆ ወደ ልማት ማስገባት የቻለበት የአሰራር ስልት በሌሎችም ክልሎች ተሞክሮው ሊቀስምና ሊሰፋ እንደሚገባ ሚኒስተሩ በአፅኖት ገልፀዋል፡፡

የሚካሂደው የመስኖ ልማት ዘመናዊ አስራርን የተከተለና ገበያ ተኮር እንዲሆን ሚኒስተሩ ዶ/ር ኢያሱ አሳስበዋል፡፡

webAdmin