መስኖ ውሃ አጠቃቀም

 

ማጠቃለያ

 • በክልሉ ውስጥ በመስኖ 980,700 ሄር ለማልማት ታቅዶ ።868427 ሄ/ር ታርሶ 840,498 ሄ/ር (85.7%) በሰብል ተሸፍኗል፡፡ ከ2008 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር 21,708 ሄ/ር ብልጫ አለው፡፡
 • አፈጻጸሙ በነባር 801,203 ሄ/ር 97.9% በአዲስ 39,295 ሄ/ር /24.6%/ ማልማት ተችሏል፡፡
 • የመስኖ ልማት ተጠቃሚዎች ቁጥር በነባር 2,256,331 በአዲስ 200,460 በድምሩ 2,456,791 አ/አደሮች ወይም የዕቅዱ 88.1% ተሳታፊዎች ወደ መስኖ ልማት ገብተዋል ፡፡
 • በሁለተኛ ዙር መስኖ 246,681 ሄር መሬት ለማልማት የታቀደ ሲሆን 165,625 ሄ/ር መሬት ታርሶ 141,537 ሄ/ር በዘር ተሸፍኗል፡፡ በዚህም በ 438,324 ወንድና 42,909 ሴት በድምሩ በ 481,233 አርሶ አደሮች ወደ ሁለተኛ ዙር መስኖ ተገብተዋል፡፡
 • የማዳበሪያ አጠቃቀም በ1ኛ ዙር መሰኖ 435,671 ኩ/ል በሁለተኛ ዙር 69,085 ኩ/ል በድምሩ 504,756 ኩ/ል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ ዉሎአል፡፡ የማዳበሪያ አጠቃቀም 52 ኪ/ግ በሄ/ር ማድረስ ተችሏል፡፡ ከ2008 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር የ5 ኪ/ግ በሄ/ር ዕድገት ያሳያል፡፡
 • በመስኖ ምርት ማሰባሰብ በዓመቱ 130,046,244 ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ ፤ የመስኖ ልማት ቀድሞ ከተጀመረባቸዉ ወረዳዎችና ዞኖች በአንደኛው ዙርእስካሁን በድምሩ 103.48 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማሰባሰብ ሲቻል በተጨማሪ ከ4 ዞን በተገኘ መረጃ እስካሁን በ2 ተኛ ዙር 1.22 ሚሊየን ማሰባሰብ በመቻሉ በድምሩ 104.70 ሚሊዮን (80.51%) ኩንታል ተችሏል፡፡

በመኸር የቀይ ሽንኩርት ምርት ልማት ፦

 • ከሁሉም ዞንና 54 ወረዳች ለተዉጣጡ 185ባለሙያች ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠና ላይ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ተደርጎ 7134 ሄ/ር መሬት በማልማት 1.1 ሚሊዮን ኩ/ል ምርት ለማምረት ከስምምነት በመድረስ የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ተልኳል ።
 • የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተጀመረ ሲሆን 3 ዞኖች ደ/ጎንደር፣ ምስ/ጎጃምና ምዕ/ጎጃም 18 ወረዳዎች፣ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን 32 ክላስተርያካተተ 2752 አርሶ አደሮች 315 ሄ/ር መሬት የመለየትና የችግኝ መደብ ማዘጋጀትና ችግኝ ማፍላት፣ ወዘተ) እየተካሄደ ነው፡፡
 • 2.የቡናና ፍራፍሬ ችግኝ ዝግጅትና ተያያዥ ተግባራት
 • በፕሮጀክት 7.095 ሚሊዮን (96.53 %) በመደበኛ 3.044 ሚሊዮን (103.2 %)በድምሩ 10.139 ሚሊዮን (98.26 %) የቡና ችግኝ ተዘጋጅቷል።
 • በቆላ ፍራፍሬ በፕሮጀክት 3.6 ሚሊዮን (153 %) በመደበኛ 2.04 ሚሊዮን (3.8 %) በድምሩ 5.646 ሚሊዮን (64.53 %) ችግኝ ተዛምቶ የእንክብካቤ እየተሰራለት ነው።
 • የደጋ ፍራፍሬ 802,804 የተከተበ 603,206 ያልተከተበ በድምሩ 1.406ሚሊየን (37.5 %) ችግኝ ተዘጋጅቷል።ቡናና ፍራፍሬ ተከላ

 

በመኸር ቡናና ፍራፍሬ ተከላ

 • የቡና ተከላ አፈፃፀም
 • በተከላው በ11 ወረዳዎች 115 ወረዳዎች 643 ቀበሌዎች ወደ ተከላ የገቡ ሲሆንየተለየ 611 ተፋሰስ፣ 964 ክላስተር ፣2013 ሄ/ር መሬት ፣አርሶ አደር 37721 /10%ሴቶች/ በመለየት 2.975 ሚሊዬን ጉድጓድበማዘጋጀትና ለተከላ ዝግጁ በማድረግ 501 ሽህ በማጓጓዝ 333ሽህ የቡና ችግኝ በ124 ሄ/ር ላይ ተከላ ተካሂዷል ።
 • በተከላው 8027 አርሶ አደሮች ሲሳተፉ ከነዚህ ውስጥ 12.98 % ሴቶች ናቸው።።
 • የቆላ ፍራፍሬ ተከላአፈፃፀም
 • በ11 ወረዳዎች 115 ወረዳዎች ፣582 ቀበሌዎች፣ 684 ተፋሰስ ፣ 982 ክላተር፣  6770  ሄ/ር መሬትና 54328 /12.29%ሴቶች/ አርሶ አደር ተለይተው ።
 • በተለየው መሬት 1.621 ሚሊየን ጉድጓድ የመቆፈር ሥራ ተካሂዷል ከዚሁ ጎን ለጎን በ6 ዞኖች የተከላ ስራ የተጀመረ ሲሆን 287857 የፍራፍሬ ችግኝ በማጓጓዝ 195017 በ1167 ሄ/ር መሬት ላይ በ 6377 አርሶ አደሮች /12.29%ሴቶች/ ተሳታፊ ሆነዋል።
 • የደጋ ፍራፍሬ ተከላ አፈፃፀም
 • ቅድመ ዝግጅት ተግባር ላይ ሲሆን በ74 ወረዳዎች 337 ቀበሌዎች በ210 ተፋሰስ 485 ክላስተር 16288 አርሶ አደር ሲመለመሉ የተከላው ወቅት እስከሚደርስ ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን እንዲያጠናቅቁ ክትትል እየተደረገ ነው ።
 • ጉድጓድ ቁፋሮ የተጀመረ ሲሆን እስካሁን በ8 ወረዳዎች 137539 ጉድጓድ ተቆፍሯል።

በአጠቃላይ ተከላው በሚጠበቀው መንገድ እየተከናወነ ባለመሆኑያለውን እርጥበት በመጠቀም ቀድሞ በመትከል የመፅደቅ ዕድልን ማስፋት እንደሚቻል በማሳሰብ ከክረምት ስራዎች ጎን ለጎን መስራት ይጠይቃል።

2.ቁልፍ ተግባር፦

2.1 በዝግጅት ምዕራፍ፦

 • የመነሻ እቅድ ተዘጋጅቶ ለዞኖች ተልኳል።በክልለ በተዘጋጀ መድረክ በ2009 ዓ.ም ዕቅድ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
 • የእቅድ ሰነዱም በመስኖ ልማት የሚለሙ ሰብሎች ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ለሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ ተሰራጭቷል።
 • ለቀበሌ ባለሙያዎች ስልጠና 7.5 ሚሊዮን ብር ተፈቅዶ ለወረዳዎች ተልኳል።
 • የስልጠና አፈጻጸም ድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ለዞኖች ተላልፏል።

ለ 83 ወረዳዎች(ለ46 የቡናና ቆላ ፍራፍሬ ለ27 የደጋ ፍራፍሬ ለ 12 በመደበኛ ) 57.46 ሚሊዮን ብር ለቡናና ፍራፍሬ ልማት ተጠቃሚ ዞኖችና ወረዳዎች ድልድል ተሰርቶ ተልኳል።  

 

3.ዋና ተግባራት

3.1 የአቅም ግንባታ ተግባር፦

 • በኢትዮ ናይል በጀት በመስኖ ሰብል ልማት ፓኬጅ አተገባበር ዙሪያ ለ53 ወንድ ለ19 ሴት በድምሩ ለ72 ተሳታፊወች ለ3 ቀን ያህል በተከታታይ ስልጠና ተሰጥቷል፤
 • ለችግኝ ጣቢያ ፎርማኖች በቡና ችግኝ ዝግጅትና ተከላ፣ ሙዝና ቆላ ፍራፍሬ ልማት፣ የተባይ መከላከል ዘዴ እና በስራስር ሰብሎች ልማት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በዚህም ወንድ 56 ሴት 9 በድምሩ 65 ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
 • በክልል በኩል መስኖ ውሃ አጠቃቀምአት/ፍራፍሬ ፓኬጅ ከ160 የገጠርና የከተማ ወረዳዎች 484 የወረዳና ዞን ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ታቅዶ 468 ሰልጣኞች (96.69%) ስልጠና ተሰጥቷል፤ 63 (13.46) ሴቶች ናቸው ።
 • በወረዳ ደረጃ 4603 ለቀበሌ ባለሙያዎች (1340 ሴቶች) 937 የወረዳ ባለሙያዎች (225 ሴቶች) በድምሩ ለ 5567 ባለሙያዎች (1565 ሴቶች) ስልጠና ተሰጥቷል።
 • የቡና ምርት አሰባሰብ ላይ ያተኮረ 146 ከቡና አምራችና ግብይት ማህበራትና አጋር አካላት ጋር በ2009 ዓ.ም የአንድ ቀን የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡
 • በፌዴራል ቡናና ሻይ ባለስልጣን ትብብር ከ50 ዞንና ከ23 ወረዳዎች ከቡና ልማት ክላስተር ለተውጣጡ 3 የክልል10 የዞን48 የወረዳ እና እንዲሁም 23 ሞዴል አርሶ አደሮች በአጠቃላይ 85 ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ለ7 ተከታታይ ቀናት ስልጠና በቡናና ቅመማ ቅመም ላይ ስልጠና ሲሰጥ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአየሁ የቡና እርሻና በአንከሻና ጓንጓ ወረዳዎች የመስክ ልምድ ልውውጥ ተካሂዷል፡፡

3.2 በመስኖ ሰርቶ ማሳያ ማካሄድ

 • በአ/አር ማሳ 858 ሰርቶ ማሳያ በ292 ሄ/ር በ963 ወንድና በ204 ሴት በድምሩ በ1003 ተሳታፊዎች እንዲሁም በአ/አደር ማሰልጠኛ 222 ሰርቶ ማሳያ በ14.5 ሄ/ር ሲከናዎን እንደ አጠቃላይ 1080 ሰርቶ ማሳያ በ306.5 ሄ/ር በ963 ወንድ በ204 ሴት በድምሩ በ1003 ተሳታፊዎች ማከናዎን ተችሏል፡፡

3.3 የመስኖ ተጠቃሚ አ/አደሮችን ማነሳሳትና ወደ መስኖ ልማት የማሰገባት እንቅስቃሴ

 • የዞኖች የተሳታፊ አ/አደሮች አፈጻጸም ሲታይ ደቡብ ጎንደር 116.1% ሰ/ወሎ 104.9%፣ ደ/ወሎ 101.1% ምዕራብ ጎጃም 91%፣ አዊ 96.7%፣ እቅዳቸዉን ያሳተፉ ሲሆን ሌሎች ከክልል አማካይ (88.1%) በታች በመሆናቸዉ አ/አደሮችን ማነሳሳትና በወቅቱ ወደ መስኖ ልማት እንዲገቡ የማሰተባበር ክፍተት ታይቷል::
 • በሁለተኛ ዙር መስኖ 246,681 ሄ/ር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን 165,625 ሄ/ር (67%) ታርሶ 141,537 (57.4%) በሰብል ተሸፍኗል በዚህም 481,233 አርሶ አደሮች ወደ መስኖ ልማት ገብተዋል፣

3.4 ማዳበሪያ አጠቃቀም

በመስኖ ልማት 1 ኩ/ል በሄ/ር ለመጠቀም በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት 980 ሺ ኩ/ል ለመጠቀም ታቅዶ አሰካሁን

በአንደኛ ዙር 5,153 ኩ/ል ዳፕ፣ 253,142 ኩ/ልኤን.ፒ.ኤስ እና ዩሪያ 177,376 ኩ/ል በድምሩ 435,671 ኩ/ል እና በሁለተኛ ዙር 42,053 ኩ/ል ኤንፒኤስ 27,032 ኩ/ል ዩሪያበድምሩ 69,085 ኩ/ል በአጠቃላይ በአንደኛና ሁለተኛ ዙር 504,756 ኩል ማዳበሪያ ለመስኖ ጥቅም ላይ ሲውል ከ2008 ዓም አፈፃጸም ጋር ሲታይ 47756 ኩ/ል (13.5%) እድገት ያሳያል።

3.6የምርጥ ዘር አጠቃቀም

 • በበጀት ዘመኑ 173,440 ኩል የአዝርዕት፣የአትክልት እና ስራስር ሰብሎች ዘር ለመጠቀም ታቅዶል።
 • የድንች ኮረት ዘር 73128 ኩ/ል፣ የሽንኩርት ኩረት ዘር 16151 ኩ/ል፣ የአዝርዕት 7840 ዘር እና 1911.9 ኩንታል የአትክልት ዘር በአጠቃላይ 99061.1 ኩ/ል (57.9% ) ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ ውሏል።

3.7 የቴክኖሎጂ አጠቃቀም

 • በአጠቃላይ 1114 ዘመናዊ የመስኖ አዉታሮች ፣ 19850 ባህላዊ የወንዝ ጠለፋዎች፣ 26045 ባህላዊ ምንጮች፣ 22875 የዉሃ መሳቢያ ሞተር፣ 2410 ፔዳል ፓምፕ፣ 5454 ሮፕ ፓምፕ፣ 18238 ጂኦመምብሬን፣ 328236 የዕጅ ውሃ ጉድጋዶችወደ መስኖ ልማት ብተዋል፡፡
 • የዉሃ አጠጣጥ በተመለከት በዚህ አመት 63.2% በትልም፣ በቋት 14.8%፣ በድንበር 15.5% የማጠጣት ዘድ ተግባራዊ በማደርግ በድምሩ 93.5% በተሻሻለ የአጠቃቀም ዘዴን ተግባረዊ ማድረግ ተችሏል፡፡

4. በመስኖ ልማት የሚታዩ ጥንካሬዎችና እጥረቶች

4.1 ጥንካሬዎች

 • የመስኖ አመራረት ቀድሞ በመጀመሩ በዚህ ዓመት የመስኖ ምርት ግብይት የተሻለና አርሶደሩን ተጠቃሚ ማድረጉ
 • የአንደኛ ዙር መስኖ ቀድሞ መጀመሩና በመስመር መዝራት፣ በዉሃ አጠቃቀ፣ በማዳበሪና ምርጥ ዘር አጠቃቀም እያደገና እየተሸሻለ መምጣት፣
 • ገበያ ተኮር የሆኑ ሰብሎችን ለይቶ በመስራት የአርሶአደሩ ትኩረትና ዝንባሌ እያደገ መምጣት፣
 • ለመስኖ ከአለፉት አመታት በተሻለየማዳበሪያ አቅርቦት መመቻቸትና ወረዳዎች ከማህበራት ወደ ማህበራት የማዟዟር ስራ መሰራቱ፣
 • የአርሶ አደሩ መስኖን የማልማት ፍላጎት ማደግ፣ በየደረጃዉ የሚሰጠዉ ድጋፍና ክትትል /የዞንና ወረዳ ድጋፍ ትኩረት እያደገ መምጣት እና በተቋቋም መመራ/

 

4.2 በእጥረት

 • በመኸር እርሻ እንቅስቃሴ ምክንያት ለሁለተኛ ዙር መስኖ የተደረዉ ደግፍ የተጠናከረ አለመሆን፤
 • የመስኖ ዉሃ ተጠቃሚ ማህበራትበዉሃ አጠቃቀም ስርዓት ላይ ሊኖር ሚገባቸዉን ሚና አለመወጣት፤
 • በበርካት ወረዳዎች የተገነቡ የመስኖ አዉታሮች በተለያዩ ምክንያቶች (በደለል መሞላት፣ በመስኖ አዉታር ብልሽት፣ ግንባታ አለመጠናቀቅ፣ የህብረተሰቡ በባለቤትነት አለመጠበቅ ወዘተ ምክንያት መበላሸትና ወደ ስራ አለመግባት፤
 • የቡና ምርት ግብይት አለመጀመር / የአጋር አካላት ተሳተፎና ደግፍ ወደ ኋላ መጓተት/፤
 • በአንዳንድ ወረዳዎች የዉሃ እጥረት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት ወደ ሁለተኛ ዙር መስኖ ፈጥኖ አለመግባት፤
 • ከገበያ ጋር ለማስተሳሰር የሚደረገዉ ጥረት ከአለፉት አመታት የተሻለ ቢሆንም ዘግይተዉ በሚደርሱ የመስኖ ሰብሎች ላይ መቀዛቀዝ ይታያል /ዉስንነት/ የማህበራትና የአጋር አካላት ተሳተፎ አለመጠናከር፤
 • ለአትክልትና ፍራፍሬ የምርት ማቆያ ቴክኖሎጂዎችና የግብይት ማዕከላት አለመስፋፋት፤

5. ቡናና ፍራፍሬ ልማት

 5.1 ቡና ልማት

 • 2009 ዓም በፕሮጀክት 7.35 ሚሊዮን በመደበኛ 2.95 ሚሊዮን በድምሩ 10.3 ሚሊዮን የቡና ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ።
 • 37.79 ኩ/ል (12.94 ሚሊዮን ዘር) ፈሷል።
 • 6.953 ሚሊዮን (65.35 %) የቡና ፕላስቲክ ተጠቅጥቋል።
 • በፕሮጀክት 7.095 ሚሊዮን (96.53 %) በመደበኛ 3.044 ሚሊዮን (103.2 %)

በድምሩ 10.139 ሚሊዮን (98.26 %) የቡና ችግኝ ተዘጋጅቷል።

 • ከፕሮጀክት ዞኖችበችግኝ ዝግጅት በአብዛኛው ዞኖችአዊ 98.9 %፣ ደ/ጎንደር 99.72 %፣ ምዕ/ጎጃም 91.8 %የተሻለ አፈፃፀም ላይ ሲሆኑ ባህር ዳር ከተማ 27.65 % ዝቅተኛ አፈፃፀም ይዟል ።

 

 

 

 

 

የቡና ምርት አሰባሰብ

በክልሉ ውስጥ 23 ወረዳዎች በ 28 የቡና ማህበር በመታገዝ የቡና ምርት ለመሰብሰብ ጥረት እየተደረገ ሲሆን እስካሁን በቅድመ ዝግጅት፦ 

 • 9297 ካ/ሜ ላይ በቁጥር 1673 የቡና ማድረቂያ አልጋ የተሰራ ተሰርቷል፤
 • የተለቀመ እሸት ቡና መጠን 9309 ኩ/ል፤
 • 4903 ኩ/ል ቡና ደርቆ ወደ መጋዘን ገብቷል፡፡
 • ከተሰበሰበው ጀንፈል ቡና ውስጥ በህብረት ስራ ማህበራት 172 ኩ/ል ብቻ ተገዝቷል፡፡

5.2 ቆላ ፍራፍሬ ልማት

በፕሮጀክት 2.32 ሚሊዮን በመደበኛ 6.42 ሚሊዮን በድምሩ 8.75 ሚሊዮን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ።491.8 ኩ/ል የተለያዩ ፍራፍሬ ዘር ፈሷል።

 • 3.133 ሚሊዮን (35.81%) ፕላስቲክ ተጠቅጥቋል።
 • በፕሮጀክት 3.6 ሚሊዮን (153 %) በመደበኛ 2.04 ሚሊዮን (3.8 %) በድምሩ 5.646 ሚሊዮን (64.53 %) ችግኝ ተዛምቶ የእንክብካቤ እየተሰራለት ነው።

የሙዝ ክላስተር ሳከር ማባዛት

በበጀት ዓመቱ 1.75 ሚሊዮን የሙዝ ችግኝ ለማባዛት ታቅዶ 398594 (22.7%) ችግኝ ተዘጋጅቷል። ለዚህም ውርጭ በመከሰቱ የማባዛቱ ስራ መግባት አለመቻላቸውን እንደ ምክንያት ያቀርባሉ።

5. 3 የዘር ግዥና አቅርቦት

የቡና ዘር ዝግጅትና አቅርቦት

ለቀጣይ አመት የቡና ዘር ፍላጎትን ለሟሟላት ክልል ከጅማ ግብርና ምርምር 6 ኩ/ል ግዥ ፈፅሞ በመምጣት ለወረዳዎች ድልድል ተሰርቶ ተሰራጭቷል በአዊ፣ በምዕ/ጎጃም፣ሰ/ጎንደር፣ዋግና ምስ/ጎጃም ካሉ እናት ዛፎችና ሰ/ሸዋ በግዥ 27.3 ኩ/ል ተለቅሞ ተዘጋጅቷል ።

የፍራፍሬ ዘር አቅርቦት

አሁን ያለውን የችግኝ ዝግጅት ለማሻሻል ዞኖች የፍራፍሬ ዘር ግዥና አቅርቦት እንዲገቡ በተከታይ በተደረገ ክትትል አዊና ደ/ወሎ ወደ ግዥ ሲገቡ ሌሎች ዞኖች ወደ ግዥ እንዲገቡ ክትትል እየተደረገ ይገኛል ፤ በዚህም  ማንጎ 1375 ኩ/ል፣ አቮካዶ 568.75 ኩ/ል  ፣ፓፓየ 20.26 ኩ/ል በድምሩ 1684.86 ኩ/ል ግዥ ተፈፅሞ  የተዘራና በብቅለት ደረጃ ላይ ሲሆን በዋግ ክምራ ዞን ከ50000 ችግኝ በላይ በውሃ ዕጥረት በመድረቁ  ይህንን ለማካካስ ሌሎች አማራጮችን እያታየ ነው።

 

 

5.4 የደጋ ፍራፍሬ ችግኝ ዝግጅት

በምርት ዘመኑ 2.1 ሚሊዮን የተከተበ፣ 1.61 ሚሊዮን መሰረተ ግንድ በድምሩ 3.7 ሚሊዮን ችግኝ ለማዘጋጀት ታቅዶ። እስካሁን 802‚804 የተከተበና 603‚206 ያልተከተበ በድምሩ 1.406 ሚሊዮን (37.5 %) ችግኝ ተዘጋጅቷል።

በደጋ ፍራፍሬ ችግኝ ዝግጅት ምስራቅ ጎጃም 363 %፣ አዊ 69.4%፣ ሰ/ጎንደር 72.1%እና ምዕራብ ጎጃም 64.2 % የተሻለ እቅድ አፈጻጸም ደረጃ ላይ ሲሆኑ ከክልል ድጎማ የሚደረግላቸው ዞኖችና ወረዳዎች /ደቡብ ጎንደር 48.1 %፣ ሰሜን ሸዋ 7.4%፣ ሰ/ወሎ 20.4 %፣ደ/ወሎ 24.1 / ዝቅተኛ አፈፃፀም ላይ ናቸው። 

የከተባ ስራ በተከታተይ ሁኔታ የጀመረና 59.1 % ሲሆን አዊ 93.5%፣ ደ/ወሎ 58.9 %  በመከተብ የተሻለ አፈፀፃም ላይ ሲሆን ምዕ/ ጎጃም 17.68 %፣ ሰ/ ሸዋ 28.1 %ና ሰ/ወሎ 16.12 %ዝቅተኛ አፈፃፀም ላይ ሲሆኑ ከፍተኛ ስራ እንዲሰሩ ክትትል ማድረግ ይገባል።

5.5 ቡናና ፍራፍሬ ተከላ

5.5.1 በመስኖ ቡናና ፍራፍሬ ተከላ

 • 11 ዞን  በ36 ወረዳዎች 405162 /17.4 %/  የቡና ችግኝ በ 152 ሄ/ር መሬት በ4408 /524 ሴቶች/ አ/አደሮች ማሳ ተከላ ተካሂዷል። በዚህ ተግባር ደ/ጎንደር /37%)ና ምዕ/ጎጃም/98.6%/ በተሻለ ወደ ስራ የገቡ ቢሆንም ክፍተኛ የችግኝ ቁጥር ያላቸው ሌሎች ዞኖች አፈፃም ከ10% በታች ሲሆኑ ባህር ዳር ከተማ ወደ ስራ አልገቡም፡፡

 

 • በ9 ዞንበ33 ወረዳዎች 133690 /18%/የቆላ ፍራፍሬ ችግኝ በ630 ሄ/ር መሬት በ4233 አ/አደሮች /456 ሴቶች/ማሳተከላ ተካሂዷል። በዚህ ተግባር ደ/ጎንደርና ምዕ/ጎጃም በተሻለ ሲሆኑ ሰ/ወሎ ፣ሰ/ጎንደርና ኦሮሞ ብሄና አዊ/ ከ10 % በታች ሲሆኑ ደ/ወሎ፣እና ባህር ዳር ከተማ ተከላ አላካሄዱም።

 

5.5.2 በመኸር ቡናና ፍራፍሬ ተከላ

የተከላ ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ዝናቡን ለመጠቀም ቀደም ብሎ ወደ ተከላ ተገብቷል ።

 • የቡና ተከላ አፈፃፀም
 • በተከላው በ11 ወረዳዎች 115 ወረዳዎች 643 ቀበሌዎች ወደ ተከላ የገቡ ሲሆንየተለየ 611 ተፋሰስ፣ 964 ክላስተር ፣2013 ሄ/ር መሬት ፣አርሶ አደር 37721 /10%ሴቶች/ መለየት ተችሏል፤
 • በምርት ዘመኑ ከተዘጋጀው 10.162 ሚሊዬን የቡና ችግኝ ውስጥ 7.5 ሚሊዬን የቡና ችግኝ ለተከላ እንደደረሰ በማረጋገጥና በመለየት ፣ 2.975 ሚሊዬን ጉድጓድበማዘጋጀትና ለተከላ ዝግጁ ተደርጓል።
 • 501 ሽህ በማጓጓዝ 333ሽህ የቡና ችግኝ በ124 ሄ/ር ተከላ ተካሂዷል ።
 • በተከላው 8027 አርሶ አደሮች ሲሳተፉ ከነዚህ ውስጥ 12.98 % ሴቶች ናቸው።።
 • የቆላ ፍራፍሬ ተከላአፈፃፀም
 • በ11 ወረዳዎች 115 ወረዳዎች ፣582 ቀበሌዎች፣ 684 ተፋሰስ ፣ 982 ክላተር፣  6770  ሄ/ር መሬትና 54328 /12.29%ሴቶች/ አርሶ አደር ተለይተው ።
 • በምርት ዘመኑ ከተዘጋጀው 5.681 ሚሊየን ችግኝ የተለያዩ አይነቶች የፍራፍሬ ችግኝ ውስጥ 3.387 ሚሊየን ችግኝ ለተከላ ዝግጁ መሆኑ በመለየትና ማረጋገጥተችሏል።
 • በተለየው መሬት 1.621 ሚሊየን ጉድጓድ የመቆፈር ሥራ ተካሂዷል ከዚሁ ጎን ለጎን በ6 ዞኖች የተከላ ስራ የተጀመረ ሲሆን 287857 የፍራፍሬ ችግኝ በማጓጓዝ 195017 በ1167 ሄ/ር መሬት ላይ በ 6377 አርሶ አደሮች /12.29%ሴቶች/ ተሳታፊ ሆነዋል።
 • የደጋ ፍራፍሬ ተከላ አፈፃፀም
 • ቅድመ ዝግጅት ተግባር ላይ ሲሆን በ74 ወረዳዎች 337 ቀበሌዎች በ210 ተፋሰስ 485 ክላስተር 16288 አርሶ አደር ሲመለመሉ የተከላው ወቅት እስከሚደርስ ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን እንዲያጠናቅቁ ክትትል እየተደረገ ነው ።
 • በዚህ መሰረት ከተሀጋጀው 1.998 ሚሊየን የደጋ ፍራፍሬ ውስጥ 1.473 ሚሊየን ችግኝ ለተከላ ዝግጅ መሆኑ ተረጋግጦ ወረ ጉድጓድ ቁፋሮ የተጀመረ ሲሆን እስካሁን በ8 ወረዳዎች 137539 ጉድጓድ ተቆፍሯል።

በአጠቃላይ ተከላው በሚጠበቀው መንገድ እየተከናወነ ባለመሆኑ ከዞን አመራሮች ጋር በቅርብ መስራት ሲጠይቅ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ቀድሞ በመትከል የመፅደቅ ዕድልን ማስፋት እንደሚቻል በማሳሰብ ከክረምት ስራዎች ጎን ለጎን የአርሶአደር ምልመላና ጉድጓድ ቁፋሮ ተከላ በዋናነት አካባቢን የመልማት አቅምና በልማት ቀጠና ላይ አተኩረው እንዲሰሩ የበላይ አመራሩ ድጋፍ ይጠይቃል።

5.6. ወጣት ስራ ዕድል ፈጠራ

 • በመስኖ ሰብል ልማት፤-  21138 ወንድ፤ 21138 ሴት ፤በድምሩ 42276 ወጣቶችን ለማሳተፍ  ታቅደ ወንድ 10173 ሴት 1581 በድምር 11855 /28%/ ወደ ተግባር ገብተዋል።
 • በቆላ ፍራፍሬ በ10 ዞንና 3 የከተማ አስተዳደር  9959 ወንድ፤9958 ሴት ፤ድምሩ 19917 ወጣቶችን ለማሳተፍ ታቅደ ወንድ 4278 ሴት 704 በድምር 4982 /25.01%/ ወደ ተግባር ገብተዋል፣
 • በደጋ ፍራፍሬ  3545 ወንድ፤3545 ሴት ፤በድምሩ 7090 ወጣቶችን ለማሳተፍ ታቅዶ ወንድ 4093 ሴት 615 በድምር 4708 /66.4%/ ወጣቶች ወደ ተግባር ገብተዋል፣
 • 149025 ችግኝ፣ 59060 የቆላ ፍራፍሬ ፣ ደጋ ፍራፍሬ 48331 ችግኝ ተዘጋጅቷል።
 • ስራ ገብተዋል።

5.7 በስኳር ድንች ልማት

በ2009 በመስኖ  ልማት 1,416,199  ቁርጥራጭ  በ7 ዞኖች ተዘጋጅቶ  344,584 ቁርጥራጭ በ6.7ሄ/ር የለማ ሲሆን 5465 አ/አደሮች (1591ሴቶች) ተሳትፈዋል:: 

6. ሰብል ጥበቃ/በመስኖ/

 • መደበኛና መጤ የአረም ቁጥጥር ማካሄድ
 • በመደበኛ አረም ቁጥጥር 1ኛ ዙር የታረመበሄ/ር 492025 እስከ4ተኛ ዙር አረም ስራ እየተከናወነ በድምር 533638 አ/አደር አ/አደር ሲሳተፉ 11.71 % ሴት ናቸው።
 • መጤና አደገኛ አረም ቁጥጥር 434835 በሄ/ር ማሳ አሰሳ የተደረገበት258217 በሄ/ር አረምየተከሰተበት መሆኑንበመረጋገጡ 48048 በሄ/ር በባህላዊ 48043 በሄ/ርና 5ሄ/ር በኬሚካል በመጠቀም መከላከል ሲቻል 380460 አ/አደር ሲሳተፉ 16.4 % ሴት ናቸው።
 • ተባይ መከላከል
 • ተባይ አሰሳ ማካሄድ በሄ/ር 94113
 • ተባይ አሰሳ የተደረገበት ማሳ ስፋት በሄ/ር 148630
 • ተባይ የተከሰተበት ማሳ ስፋት በሄ/ር 104245
 • መከላከል የተደረገበት ማሳ ስፋት በሄ/ር 48820 በባህላዊ 19168ሄ/ርበኬሚካል 29652 ሄ/ር ለዚህም ፈሳሽ 28386ሊትር ዱቄት3739 ኪ/ግ ጥቅም ላይ ሲውል በመከላከሉ ወንድ 33207 ሴት 4335 ድምር 37542አ/አደር ተሳታፊ ሆነዋል።
Undefined