Background of BoA

1. መግቢያ

የረጅም ዘመናት ታሪክ ያለው ግብርና ለክልላችንና ለሀገራችን ህዝቦች የህይወት መሠረት፤ የኢኮኖሚያችን ዋነኛ አንቀሳቃሽ ሀይልና አብዛኛውን የህዝባችንን ቁጥር የሚሸከም ዘርፍ ነው፡፡ ግብርና ባለፉት አስራ አንድ ዓመታት የማያቋርጥ ዕድገት በማስመዝገቡ ሀገራችን እጅዋን ለምግብ ሰብል ርዳታ የምትዘረጋ ሳይሆን በራሷ የምትተማመን፣ ጠንክረን ከሠራን ደግሞ ዘርፉ አንገት የሚደፋበት ሳይሆን ህይወት የሚለወጠበት እንደሆነ  ያሣለፍናቸው ዓመታት በግልፅ አሳይተውናል፡

 የግብርናው ዘርፍ በተለይም ባለፉት አምስት  የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዓመታት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ በመሠራቱ በክልላችን ከየትኛውም አካባቢ በተሻለ መልኩ የምርት ዕድገት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

 የምርት ዕድገቱ ሊመዘገብ የቻለው ደግሞ አ/አደሩ፣ ባለሙያውና አመራሩ የልማት አንድነት ፈጥረው እንደ ሠራዊት መንቀሳቀስ በመቻላቸው ነው፡፡በአጠቃላይ የግብርና ልማታችን እና የግብርና ተቋም ያለበትን  ሁኔታ በምናይበት ጊዜ የማንኛውንም አይነት  ልማት ዘላቂነትና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ  በሲስተም መምራት ያስፈልጋል፡፡ ሲስተም ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ደግሞ ራሱን ችሎ መፈፀም የሚችል አካል (ተቋም) መኖር ሲችል ብቻ ነው፡፡ የግብርናው ሴክተር ባልጐለበተበት  እና እንዲሁም የዳበረ ልምድና ዕውቀት አናሳ በነበረበት ወቅት በሰፊ ድጋፍ የማይናቅ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ ይህ የዘመቻ ባህሪ የነበረው የድጋፍ አሰጣጥ ደግሞ በዘላቂነት ሊቀጥል አይችልም፡፡ በመሆኑም ግብርና የክልሉ የኢኮኖሚ መሠረት መሆኑን የተረዳውና በየደረጃው የሚገኘው አመራር እና ባለሙያ በሚያደርገው ሰፊ ድጋፍ ሴክተሩ በእግሩ ለመቆም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የግብርና ልማት በባህሪው  ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ መጠን በተደራጀ አግባብ መንቀሳቀስ ካልቻለ ውጤቱ አንዱን ጥሎ ሌላውን እንደ ማንሳት ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት ሁሉንም ተግባራት በተማዘነ መልኩ ይዞ ለመጓዝ  ሴክተሩ ከላይ እስከታች እንደ ሠራዊት መንቀሳቀስ ጀምሯል፡፡  ስለሆንም ሁሉን አቀፍ ለውጥ እየመጣ ነው፤ በሠብል ምርትና ምርታማነት አድጓል፣ በመስኖና በተፈጥሮ ሀብት የክልላችንን ገፅታ የሚቀይር በርካታ ስራ እየተሠራ ነው፡፡ በእንስሳት ሀብት ልማትም ዘርፉን የሚያሻሽሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ አበረታች የግብርና ስራዎች በገጠር የአ/አደሩን ህይወት በመቀየር ላይ ሲሆኑ በከተሞችም የምግብ አቅርቦትን ከማሟላት ባለፈ ለዜጐች የስራ ዕድል ምንጭ ሆነዋል፡፡ የግብርና ምርት ከመንደር ገበያ እየወጣ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት መዋል ጀምሯል፡፡ በዚህም ከሚበላው የሚተርፈውን የሚሸጥ ሳይሆን ከሚሸጠው የሚተርፈውን የሚበላ ኮመርሻል አ/አደር መፍጠር እየቻልን ነው፡፡ በክልላችን መሠረታቸውን ግብርና ያደረጉ ባለ ሚሊዬን ብር አ/አደሮች መፍጠር ችለናል፡፡  በአጠቃላይ ሲታይ ግብርና የለውጥ ተቋም መሆን ጀምሯል፡፡ የዚህ ለውጥ ባለቤት ደግሞ አመራሩ ባለሙያውና አ/አደሩ  ናቸው፡፡ ይሁንና ግን ሁሉም አርሶ አደሮች በአንድ አይነት የለውጥ የእድገት ደረጃ ላይ ናቸው ለማለት አይቻልም፡፡ ሁሉንም አርሶ አደሮች ወደ ተቀራረበ የእድገት ደረጃ ላይ ለማድረስ ደግሞ ሰፊ የግብርና ልማት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡እንዲሁም የሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ታቅዶ ክልሉ ሰፊ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

የአማራ  ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት ካርታ

1. የክልሉ አጠቃላይ ገጽታዎች

1.1 የአማራ ክልል የሚያዋስናቸው

       - ከትግራይ

       - ከአፋር

     - ከኦሮሚያ

    -ምዕራብ - ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

   - ከሱዳን ሪፐብሊክ መንግስት ጋር ይዋሰናል፡፡

ቢሮ የሚያስተባብራቸው:-

5 ሴክተር መ/ቤቶች እና 2 ኢንተርፕራይዞች አሉ

 • መከ/ም/ዋ/ፕሮግራም ማስተ/ ጽ/ቤት
 • ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
 • ሀ/ል/ማስፋፊያ ኤጀንሲ
 • ሥራ ማህበራት ማስፈፊያ ኤጀንሲ
 • ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
 • ደን ኢንተርፕራይዝ
 • ሌሎች የግብ/ግብዓቶች ኳራንቲን ባለስልጣን
 • 10 ዞኖች፣
 • 167 ወረዳዎች እና
 • 3198 ቀበሌዎች
 • 13 ማዕከላት
 • የግብርና ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አሉ
 •  
 • በቀበሌ ደረጃ የተደራጁ የግብርና ልማት ጽ/ቤት ብዛት-
 • በክልሉ የልማት ጣቢያ ሰራተኞችብዛት-ወንድ- ሴት-
 • በክልሉ የሰው ኃይል እና ቁሳቁስ ተሟልቶላቸው ወደ ስራ የገቡ የቀበሌ አርሶአደር ማሰልጠኛዎች ( FTC) ብዛት-
 • በ 5 ዋና ዋና የአየር ንብረት ቀጠናዎች  የተከፋፈለ ሲሆን
 • 3.14 በመቶ በረሀማ /ደረቅ ቆላ/
 • 28.11 በመቶ ቆላ
 • 44.3 በመቶ ወይና ደጋ
 • 20.52 በመቶ ደጋማ
 • 3.93 በመቶ ውርጭ የአየር ንብረት አለው
 • የሙቀት መጠን >26
 •    < 11ዲ/ሴ/ግሬድ  ነው ፡፡
 • የዝናብ መጠን ዝቅተኛው ከ500-700ሚ.ሜ እና
 • > 1400ሚ.ሜ ይደርሳል
 • የቆዳ  ስፋት 170,152  ስኩዌር ኪ/ሜ  (የሀገሪቱ 15% )ሲሆን ፡-
  • መሬት የተያዘ ..... 31%
  • መሬት የተያዘ...... 28%
  • ቡሽ ለበስ መሬት...... 14.7%
  • አካል የተያዘ .................... 3.8%
  • ውጭ የሆነ መሬት...... 16.2%
  • የተያዘ............. 6.3 % ይሆናል ተብሎ ይገመታል
 •   ቦታ  (2500-4620m)

                =  21%

 •   (1500-2500m)     

                 =  44.7%

 • ቦታዎች  (500-1500m)         

                =  34.3%

1.1 የክልሉ ዋና ዋና  የግብርና ጸጋዎች

 • ዳሸንን ጨምሮ በርካታ ተራሮች  እና
 • እና የአዋሽ ገባር የሆኑና ለመስኖ ልማት አገልግሎት የሚውሉ  ብዛት ያላቸው ወንዞች አሉ
 • ትልቅ የሚባለው  ጣና ሀይቅ  እና ሌሎች መለስተኛ 8 ሀይቆች ይገኛሉ
 • በክልሉ
 • 52% የሚሠራ ህዝብ/ እድሜያቸው ከ15 -64 ዓመት የደረሱ/
 • ለእንስሳት እርባታ ተስማሚ የሆነ መሬትና የውሀ ሀብት
 • ሆነ በመስኖ ለምተው ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የብርዕ፣የጥራጥሬ፣የቅባት፣የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎች ይመረታሉ

የክልሉ የእንስሳት ሀብት ልማት ጠቀሜታና ለኢኮኖሚ ልማት ያለውድርሻ፤

እንስሳት ሀብት ልማት የአንድን ሀገር የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሣደግ፣ ድህነትን ለመቀነስና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ በጣም ከፍተኛ ነው።የአማራ ክልል የእንስሳት ሀብት ኢትዮጵያ ካላት ቁጥር አንጻር ሲታይ 1/3ኛውን እንደሚሸፍን የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ15። የክልሉ የእንስሳት ሀብት ብዛት በእንስሳት ዓይነት እና ከአገሪቱ አንጻር የሚኖረውን ድርሻ ቀጥሎ በተመለከተው ሠንጠረዥ ለማየት ይቻላል።

የእንስሳት ሃብት

ኢትዮጽያ

አማራ ክልል

ዳልጋ ከብት

53.9

  13.37(24.8%)

በግ

25.4

8.7(34.25%)

ፍየል

24

5.2(21.6%)

ግመል

915,513

   51475(5.6%)

ዶሮ

50.3

14.1(28.03%)

ጋማ ከብት

8.95

2.75(30.72%)

ንብ

5.2

911,986(17.5)

ምንጭ፦ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለሥልጣን /2005 ዓ.ም

በወተት ምርታማነታቸው የታወቁ የፎገራ የዳልጋ ከብት ዝርያዎች

     - በፀጉር ምርት የታወቁት የመንዝ በግ ዝርያዎች

     - በስጋ ምርታቸው የታወቁ የቲሊሊ ዶሮ ዝርያዎች ይገኛሉ

1.2 የክልሉ አንጻራዊ አዋጭ የግብርና መስኮች

 • ክልሉ የተለያዩ ስነ-ምህዳር ቀጠናዎች ባለቤት በመሆኑ በዋናነት በሰብል፣በእንስሳትና በተፈጥሮ ሀብት የልማት ዘርፎች 85 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በግብርና ሥራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል
 • እንደ ደቡብ ጎንደር ዞንፎገራ ወረዳ ባሉ ውሀ አዘል በሆኑት (Wetland Areas) ሩዝበሰፊውእየተመረተ ነው
 • በቆላማው የሰሜን ምዕራብ አካባቢ ሰሊጥ ይመረታል
 • በሰሜን ጎንደር ቆላማው አካባቢ የእጣንና ሙጫ ምርት አለ
 • በአዊ ዞንየቀርቅሀ ምርት እየተስፋፋ ይገኛል
 • Specialization & Diversification መሠረት በማድረግ ክልሉን በ 6 የልማት ቀጠናዎች (Growth Corridors) በመለየት ስትራቴጅያዊ የግብርና ልማት ተግባራትን በማከናዎን ገበያን መሠረት ባደረገ መልኩ፡
 •   አትክልትና ፍራፍሬ
 • ፍየል እርባታ
 • የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች
 • ሀብት እና መስኖ ልማት አዋጭ የግብርና መስኮች መሆናቸው ተረጋግጧል
 • ልማት ተግባራት ላይ የተሰማሩ
 • 90 የመያድ(NGOs)
 • 11 የመንግስታትና በይነ መንግስታት (Bilaterals &Multilaterals) በድምሩ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት በማንቀሳቀስ ወደ ተግባር ምዕራፍ የገቡ መሆናቸው

2. የእድ/ትራንስ/እቅድ (GTP) የትኩረት መስኮችና ዋና ዋና ዓላማዎች፡

2.1 በግብርና ልማት ዘርፍ

 • በተፈጥሮ ሀ/ል/ውሀ ማሰባሰብ ስራ
 • የተቀናጀ ተፋሰስ ልማትን በማካሄድ እንዲሁምየተራቆቱ መሬቶችን ከንክኪ ነጻ በማድረግና በመጠበቅ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ዘላቂ ተፈጥሮ ሀብት ልማት በማምጣት የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል
 • በግብርና ኤክስቴንሽን
 • የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጅዎችን በማቅረብ ፣በማስተዋወቅና በማስረጽ እንዲሁም አርሶ አደሩን በማደራጀትና የአመራረት ዘዴን በማሻሻል ገቢውንከፍ ማድረግ
 • በሰብል ልማት
 • የአካባቢውን ሥነ ምህዳር መሠረት ያደረጉ ተስማሚ የሰብል ልማትና ጥበቃ ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ገበያ ተኮር የሆኑ ሰብሎችን በጥራት ማምረትና የክልሉን አርሶ አደር ገቢ በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ
 • ሁሉም የሰብል ዓይነቶች (ጤፍን ጨምሮ) በመስመር እንዲዘሩ በማድረግና ግብዓቶችን በአግባቡ በመጠቀም ምርታማነታቸውን ማሳደግ
 • በግብርና ግብዓት አቅርቦትና ስርጭት
 • የአርሶ አደሩን የግብዓት ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ የግብዓት ፍላጎትን በሚፈለገው መጠንና በወቅቱ በማሟላት ምርትና ምርታማነት ማሳደግ
 • በምግብ ዋስትና አደ/መከ/ጽ/ቤት
 • ሥር በሰደደ የምግብ ዋስትና መታጣት ችግር ውስጥ ያለውን ህዝብ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ
 • የክልሉን የእንስሳት ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከፍ ማድረግና ከክፍለ ኢኮኖሚው የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ
 • በግብርና ምርምር
 • ምርትና ምርታማነትን የሚጨምሩ በሌሎች አካባቢዎች ውጤታማነታቸው የተመሰከረላቸውን ቴክኖሎጅዎች በማላመድና ችግሮችን በማጥናት ምላሽ መስጠትና የመነሻ ቴክኖሎጅዎችን በማውጣት ለአርሶ አደሩ ማሰራጨት
 • በአት/ፍ/ል መስኖ አጠቃቀም

የተሻሻሉ የመስኖ እርሻ ልማት ቴክኖሎጅዎችንና አሠራሮችን መጠቀም የሚችል ተቋም በመገንባት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ

2.3 የማስፈፀሚያ  ስትራቴጅዎች

2.3.1 ምርጥ አርሶ አደሮች የሚጠቀሙበትን ቴክኖሎጅ ወደ ሁሉም አርሶ አደሮች ማስፋት

 • የምርጥ አርሶ አደሮችን ምርት የማሳደግ ልምድ ለሁሉም ማዳረስ

2.3.2 የውሀ አጠቃቀምን በማሻሻል የመስኖ ልማትን ማስፋፋት

 • የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር ውሀን በማበልፀግ
 • የዝናብ ውሀን በማሰባሰብ(ኩሬዎች)
 • በዝናብ አጠር አካባቢዎች በማሳ ውስጥ የውሀ ማስረጊያ ጉድጓድ በማዘጋጀት

2.3.3 ለገበያና ኢንዱስትሪ የሚያመርት ግብርናን ማስፈን

 • መሠረተ ልማትን በማስፋፋት
 • ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት