Agricultural Extension Service

የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

 

የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ፡-

በገቢያ የሚመራ የግብርና ኤክስቴንሽን ሥርዓት በመዘርጋት በገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ቴክኖሎጂን የሚጠቀምና በእውቀት፣ በክህሎቱና በአመለካከቱ የተለወጠ እና ገቢው ያደገ አምራች ዜጋን ለመፍጠር

 • ግብርናን ሊያዘምን የሚያስችል በገበያ የሚመራ ኤክስቴንሽን ሥርዓት መዘርጋት
 • በአንድ አካባቢ ውጤታማ የሆኑ የግብርና ልማት ሥራዎች ወደ ሁሉም አርሶ አደር እንዲደርሱ የማስፋት ስትራቴጂዎችን መተግበር
 • የተሻሻሉ አሰራሮችና ቴክኖሎጅ ስርጸትን ፈጣንና ውጤታማ ለማድረግ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የኤክስቴንሽን የልማት ቡድኖች፤ ሴቶች እና ወጣቶችን እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውን በመንደርና በማሳ ዙሪያ በማደራጀት የኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት
 • የልማት አጋር አካላት ካውንስል ማቋቋምና የግንኙነት መድረኮችን ማካሄድ
 • ክፍተትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን በመስጠትና የሙያ ብቃት ምዘና በማካሄድ የግብርና ኤክስቴንሽን ተግባራት ለአርሶ አደሩ፤ ሴቶችና ወጣቶች እንዲሁም ለግል ባለሀብቱ ተደራሽ ማድረግ
 • የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት በሁሉም ቀበሌዎች እንዲቋቋሙ በማድረግ የቴክኖሎጂ እና የተሸሻሉ አሰራሮች የሽግግር ማዕከላት እንዲሆኑ ማድረግ
 • የምግብና የስርዓተ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ሥርዓተ ምግብ ተኮር፤ ስርዓተ ጾታ ፤ እና የአካባቢ እንክብካቤና ዘላቂነት ያተኮረ ግብርና ሥራዎች እንዲተገበሩ ማድረግ ዋና ዋና ተግባራቶቹ ናቸው

የኤክስቴንሽን ኮምዩኒኬሽን 

የግብርና  ኤክስቴንሽን ፕርግራምና ፕሮጀክት ዝግጅት ክትትልና ግምግማ ባለሙያ

 

የሴቶች ወጣቶች እና ኤች ኤቪ ኤድስ ጉዳይ ኤክስፐርት

የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሙኑኬሽን ዳይሬክቶሬት አደረጃጀት

 

የግብርና ኮሌጆች  ክትትልና ድጋፍ ባለሙያ 

የምግብና ሥርዓተ ምግብ ቴክኖሎጂ ባለሙያ

ሥልጠና ክትትል  ባለሙያ

የግብርና ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ ቁልፍ መሠረታዊ መርሆዎች

1) ፍላጎትን መሠረት ያደረገና ገበያ መር ኤክስቴንሽን ሲስተም፣

2) መንግስት የሚመራው ሁሉን አቀፍ የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣

3) አሳታፊና የኤክስቴንሽን ዘዴና አቀራረብ፣

4) የእሴት ሰንሰለት ኤክስቴንሽን አቀራረብ ፣

5) ሥነ ምህዳርንና የመሬት አቀማመጥን መሠረት ያደረጉ ማስተካከያ እርምጃዎች፣

6) ሥርዓተ- ጾታ፤ ወጣችና እና ሥርዓተ -ምግብን በዋና ተግባር ውስጥ ማካተት፣

7) ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃና ልማት ተግባራትን በዋና ተግባር ውስጥ ማካተት፣

8) ተወዳዳሪና ክህሎት ያለው የሰው ሀብት፣

9) ስፔሻላይዜሽን እና ዳይቨርስፊኬሽን፣

10) ሂደትን እና ውጤትን መሠረት ያደረገ የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣

11) ሁሉን አቀፍ የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣

12) ከሌሎች ተመሳሳይ አገልግሎቶች ጋር መተባበርና መቀራረብ፣

13) ምርጥ ተሞክሮዎችን ወደ ጎን እና ወደ ላይ ማስፋት፣ እና 

14) ሀላፊነትና ተጠያቂነት  ናቸው፡፡

 

የግብርና ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ  የተገነባባቸው  ምሰሶዎች

ምሰሶ አንድ፡  የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላትን በህብረተሰብ ሙሉ ተሳትፎና አቅም ግንባታ ማጠናከር

ምሰሶ ሁለት፡  የግብርና የዕውቀትና የመረጃ ሥርዓትን ማጠናከር

ምሰሶ ሦስት፡ ደምበኛ ተኮርና የብዙ ተዋናዮች የኤክስቴንሽን ምክር አገልግሎትን ማሳደግ

ምሰሶ አራት፡ የገበያ ትስስር ማመቻቸትና የእሴት ሰንሰለት ልማትን ማሳደግ

ምሰሶ አምስት፡ የሥርዓተ ፆታ፣ ወጣት እና የሥርዓተ ምግብ አስፈላጊነት

ምሰሶ ስድስት፡  የአካባቢ እንክብካቤና ዘላቂነት  

ምሰሶ ሰባት፡ በቁልፍ የግብርና ተዋናዮች መካከል ተቋማዊ አደረጃጀት፤ ትብብር እና ትስስርን ማጠናከር

ምሰሶ ስምንት፡ ለውጤታማ ኤክስቴንሽን አገልግሎት  የሰው ሀብት ልማትና አጠቃቀም

ምሰሶ ዘጠኝ፡ ቀጣይነት ያለው የኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ጠንካራ፤ ፈጣን ወጤትን መሠረት ያደረገ ክትትል፤ግምገማና መማማርን መመስረት

 

በግብርና ኤክስቴንሽን ኮሙኑኬሽን ዳይሬክቶሬት ያሉ ክፍሎች ዋና ዋና ተግባራት

 

 1. የግብርና ኤክስቴንሽን ኮሙኑኬሽን
 • ለአርሶ አደሩ ገበያ መር የኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የኤክስቴንሽን ሥርዓት መዘርጋት
 • አርሶ አደር፤ ሴቶችና ወጣቶች የሽጦ ማምረት (የኮንትራት እርሻ) የሚያጠናክር አሰራር መዘርጋት
 • የአካባቢን የማምረት አቅምና ሀብት መሰረት ያደረገ የግብርና ክላስተር ኤክስቴንሽን አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ፤
 • ምርጥ ተሞክሮዎችን በማሰባሰብ ይለያል፤በፓኬጅ መልክ ይቀምራል ወደሌሎች አካባቢዎች እንዲስፋፉ አስፈላጊውን ስልት ይቀይሳል፤
 • አዳዲስ አሰራሮችና ቴክኖሎጅዎችን ሰርቶ ማሳያዎችን በማካሄድና የአርሶ አደሮችን በዓላት በተደጋጋሚ በማካሄድ ሌሎች ያልተደረሱ አርሶ አደሮችን መድረስ፤
 • የቴክኖሎጂ ስርፀትን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የአርሶ አደር፤ ሴቶችና ወጣቶች እንዲሁም በተለያዩ እሴት በሚጨምሩ የግብርና ምርቶች ያደራጃል፤
 • በሁሉም ቀበሌ የአርሶ  አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት እንዲቋቋሙና በየጊዜው የውስጥና የውጭ ቁሳቁስ እንዲሟሉ በማድረግ በደረጃ እንዲለዩ በማድረግ ደረጃቸው እንዲሻሻል ማድረግ፤
 • በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት በተግባር የተደገፈ የብቃት እና የደረጃ ሥልጠና እንዲሰጥ፤ሰርቶ ማሳያ እንዲካሄዱ እና የመረጃና የኤግዝቢሽን ማዕከል እንዲሆኑ ማድረግ
 • ቪዲዮንና ሞባይል መሰረት ያደረገ (ICT based) ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ያደርጋል
 • በየደረጃው  የልማት አጋር አካላት እንዲቋቋሙና እንዲጠናከሩ ያደርጋል
 1. ሥልጠና ክትትል  ባለሙያ
 • አርሶ አደሮች እና ባለሙያዎች በመሰረታዊ የግብርና ሙያዎች እንዲሰለጥኑ የሚያስችል የተለያዩ የሥልጠና ካሪኩለም ማንዋሎችን ማዘጋጀትና ሥልጠና እንዲሰጥ ማስተባበር፣
 • ከሙያ ብቃት ምዘና የማካሄድ ስልጣን ከተሰጣቸው ተቋማት ጋር በጋራ የግብርና ሴክተር የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓት እንዲዘረጋና ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል
 • ሥልጠና የወሰዱ ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ሥልጠና በወሰዱበት የሙያ ዓይነትና ደረጃ የሙያ ብቃት ምዘና እንዲወስዱ በማድረግ ብቃታቸው እንዲረጋገጥና ማድረግ፤
 • በንድፈ-ሀሳብም ሆነ በተግባር የተሰጠውን የቴክኖሎጂ ሥልጠና ተግባራዊነቱን በመስክ በመገኘት ውጤታማነቱን ይከታተላል
 • በእያንዳንዱ የግብርና ስራ ምዕራፎች ግንዛቤ ለመፍጠር የሚረዱ የንቅንቄና የማነሳሳት መድረኮች ያመቻቻል
 1. የግብርና  ኤክስቴንሽን ፕርግራምና ፕሮጀክት ዝግጅት ክትትልና ግምግማ ባለሙያ
 • የኤክስቴንሽን ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ለማሻሻል እና ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ጥናቶችን ያጠናል የምርጥ ተሞክሮዎች ፓኬጅ የአሰራር ማሻሻያ ሃሳቦች ለውሳኔ ማቅረብ
 • ለፕሮግራምና ፕሮጀክት አስፈላጊ የሆኑ ጥናቶችን እንዲሁም የኤክስቴንሽን ፓኬጅ ዝግጅት የሚውል የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል
 • የግብርና ኤክስቴንሽን ተጠቃሚዎች የህብረተሰብ እርካታ በጥናት በመለየት የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ሃሳቦች ለውሳኔ ማቅረብ
 • የሀገሪቱን የልማት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ተቋሙ ችግር ፈች የሆነ በረዥም፣ በመካከለኛና አጭር ጊዜ ተግባራዊ የሚሆኑ  የፕሮጀክት ሰነዶችን ማዘጋጀት
 • የፕሮግራምና ፕሮጀክት ሥራዎች በታቀደላቸውና በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት እየተከናወኑ መሆኑን መከታተል፤
 • በፕሮጅክትና ፓኬጅ ዝግጅት፤ክትትልና ግምገማ ሥራዎች ዙሪያ አቅም ለማጎልበት የተሰጡ ሥልጠናዎች ያመጡትን ለውጥ መከታተል፣
 1. የምግብና ሥርዓተ ምግብ ቴክኖሎጂ ባለሙያ
 • የአርሶ አደሮች፤ሴቶች፤ ወጣቶችና የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎች የሥርዓተ ምግብ ችግሮችና የቴክኖሎጂ ፍላጎት በጥናት መለየትና፣ችግሮቹ በምርምር ተቋማትና በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ፡፡
 • በምግብ ንጥረ ይዘታቸው የበለጸጉ ሰብሎች እና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያላቸው በስፋት ጥቅም ላይ  ያልዋሉትን በጥናት በመለየት፤ ጥቅም ላይ የሚውሉበትን የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት፤
 • በአካባቢ የሚመረተው የግብርና ምርትና ምግብ ብክነትን የሚቀንሱ አማራጭ የአመጋገብ ዘዴዎችንና የድህረ ምርት ቴክኖሎጂዎችን መረጃ በማደራጀት ሥልጠና መስጥት
 • አርሶ አደር በተለይ ሴቶች በምርት አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል አቅም፤የእውቀትና ክህሎት ሥልጠና መስጠት
 • በጓሮ ስብጥር አመራረትና አመጋገብ ላይ ተመስርተው በቤተሰብና በአካባቢ ደረጃ የተሰሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማስፋት፤
 • በሥርዓተ ምግብ ተኮር ግብርና ላይ የባለሙያዎችን ብቃት ለማሳደግ የሚያስችል የሥልጠና ፍላጎት ልየታ እና የተለየውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ሥልጠና ይሠጣል፤
 • በተካሄዱ የአመራረትና የምግብ ዝግጅት ሰርቶ ማሳያዎች ላይ ተደጋጋሚ የሆነ የአርሶ አደር በዓል በማዘጋጀት፤ልምድ ልውውጥ ማካሄድ
 • የሥርዓተ ምግብ መጓደል ችግርን ለመቅረፍ በሚደረገው ርብርብ ያለውን ጉልህ ሚና ሊያሳዩና ሊያፋጥኑ የሚችሉ አካባቢን መሰረት ያደረገ የምግብ አውደ ርዕይ (food exhibition) በማዘጋጀት የልምድ ልውውጥ ማካሄድ
 1. የሴቶች ወጣቶች እና ኤች ኤቪ ኤድስ ጉዳይ ኤክስፐርት
 • በሴቶች ወጣቶች ጉዳይ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲሁም ኤችኤቪ ኤድስ ለመከላከል ሀገራ አቀፍ ተሞክሮ በመቅሰም በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፉ ማድረግ
 • በሴክተሩ እቅዶች፣ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የሴቶች ወጣቶች ጉዳይ እንዲሁም ኤችኤቪ ኤድስ ለመከላከል  እንዲካተት ማድረግ
 • ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ድህነት እና ስራ አጥነትን ለመቀነስ የተለያዩ ፓኬጆችን በመቅረጽ ወጣቶቹ ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ
 • ወጣቶች እና ሴቶች ውጤታማ ሆነው ለሌሎች ስራ እድል መፍጥር እንዲችሉ በኢንተር ፕራዝ እንዲደራጁ ከሚመለከተው አካል ጋር በትብብር መስራት
 • የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ወጣቶች እና ሴቶች በሚሰማሩባቸው ዘርፎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እውቀት እና ክህሎት ይዘው ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ
 • ወደ ስራ ከገቡት ወጣቶች እና ሴቶች ውስጥ በተፈጠረላቸው የስራ እድል ውጤታማ የሆኑትን  ተሞክሮ የመቀመር እና የማስፋት ተግባር መስራት
 • ከኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች የተመረቁ ወጣቶችን በትምህርት ቆይታቸው ያገኙትን የንድፈ ሃሳብ  ትምህርት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማሰማራት
 • የሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማጐልበት በዘርፉ የሚሰሩ መንግስታዊ መ/ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶችና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር መፍጠር 
 1. የግብርና ኮሌጆች  ክትትልና ድጋፍ ባለሙያ 
 • በሀገር ደረጃ በቴ/ሙ/ት/ስልጠና ስትራቴጅ የተቀመጠውን ጥራቱን የጠበቀ የመማር ማስተማር፣ የጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎትን መተግበር
 • የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጆቹ የት/ሥ/ የጥራት ማሰጠበቂያ ስታንዳርድን ጠብቀው አገልግሎት መስጠት መቻላቸውን መከታተል፤
 • የግብርና ቴ/ሙ/ት/ ተቋማቱ የሚሰጡት ስልጠና ከክልሉ ፍላጎት ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ማድረግ
 • የለውጥ መሳሪያዎች በተገቢው መንገድ በተቋማቱ መተግበራቸውን መከታተል
 • የመማር ማስተማሩ ተግባር በተዘጋጀለት የትምህርት መርሃ ግብር መሰረት እየተካሄደ መሆኑን በክትትልና በግምገማ ማረጋገጥ፤
 • ተማሪዎች በስነ ስርዓት የታነጹ፣ መልካም እሴቶችና ባህልን የተላበሱ፣አካባቢን የመንከባከብ ሃላፊነት እና ሃገራዊ ስሜት የሚሰማቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ፤